Saturday, August 31, 2013

ድምፃችን ይሰማ ግልፅ መልዕክት ለሰልፉ ተሳታፊ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች!


ድምፃችን ይሰማ




#ForcedGovtDemonstration #Nehase26Demonstration


ግልፅ መልዕክት ለሰልፉ ተሳታፊ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች!


ቅዳሜ ነሐሴ 25/2005

አገራችን ኢትዮጵያ ካለባት ውስብስብ የፖለቲካ ችግሮች በተቃራኒ ህዝቦቿ ተቻችለው ለዘመናት 


ዘልቀዋል፡፡ አብዛኛው 

ገዢዎቻችን በአገዛዝ ዘመናቸው ይህን ውስብስብ የፖለቲካ ሰንኮፍ ለህዝብ በሚጠቅም መልኩ መንቀል ሲሳናቸው የህዝብ 

ጥያቂ አቅጣጫ ለማሳት ያልተጠቀሙት እጅግ አደገኛና አገር ያበጣብጣል የተባለ ዘዴ አልነበረም ማለት ይቻላል፡፡ የማታማታ 

ህዝብ እንደ ህዝብ ለዘመናት አቆይቶ በጠበቀው መስተጋብር ራሱን ከገዢዎች ሴራ ሲጠብቅ ቆይቷል፡፡ የገዢዎቹ ሴራ ጥንካሬ 

ቢኖረውም ማህበረሰባችን ታንፆ የሚያድገው በሚከተለው የሃይማኖት ቀኖና በመሆኑና ለተንኮለኞች ሴራ የሚሰጠው ምላሽ 

ግብታዊ ሳይሆን በመንፈሳዊ ስብዕናው ታግሶ በመሆኑ የቀደሙ አገዛዞች ተንኮታኩተው ሲወድቁ ህዝቦች ማንነታቸውን 

ጠብቀው ዛሬም ድረስ ቆይተዋል፡፡ ይህን ታሪክና ማንነት ጠብቀን ልናቆይ የምንችለውና የተንኮል እቅዶችን ማምከን 

የሚቻለውም ህዝቦች ባለን የሃይማኖት ስብእና በመታገዝ እንጂ በርካሽ ፖለቲካ ተጠልፈን በመውደቅ አይደለም፡፡ 

የሃይማኖቶች ጉባኤ ጠርቶታል የተባለው የነገው ሰልፍም ይህ መርህ በተንኮለኞች ሴራ ሳይጠለፉ መስተጋብራችንን ጠብቀን 

ለመቆየታችን ቋሚ ማሳያ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ ሊሆንም ይገባል፡፡


ህዝበ ሙስሊሙ ያነሳቸውን ሰላማዊ የመብት ጥያቄዎች በዴሞክራሲያዊ አግባብ ከመመለስ ይልቅ መንግስት ይከተላቸው 


የነበሩ የስም ማጥፋት አካሄዶች ባለፉት ሁለት አመታት ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሲያቀርብ ነበር፡፡ ውንጀላዎቹ ከሙስሊሙ 

ጥያቄ ጋር ምንም ዝምድና ስለሌላቸው ተቀባይ ሊያገኙም አልቻሉም፡፡ እንደውም ከሙስሊሙ እኩል የሌሎች እምነት 

ተከታዮች የህዝብ ጥያቄ እንዲመለስ ሲሉ በየስብሰባው የሚያምኑበትን እየገለፁ ነው፡፡ ይህም ህዝባዊ ማንነታችንን ጠብቀን 

የማቆየታችን ትልቅ ማሳያ ነው፡፡ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠርቶታል በተባለው በነገው ሰልፍ ህዝበ ሙስሊሙ ሁለት 

አላማን በማንገብ ሰልፉን ይቀላቀላል፡፡

የመጀመሪያው ኢትዮጵያ ሃገራችን በሰላም እና ህዝቦች በተግባቡበት የጋራ ህገ-መንግስት እንድትተዳደር የፖለቲካን ጨምሮ 


ማንኛውም አይነት አክራሪነትን ለማውገዝ ሲሆን ሁለተኛው አላማ ደግሞ ከተቀሩት የሃገር ወንድምና እህቶቻችን ጋር የቆየውን 

መስተጋብራችንን በመከባበርና በመተባበር መንፈስ ለማስጠበቅ ነው፡፡ ዛሬ መንግስት በሙስሊሙ ላይ እያደረገ ያለው ብሄራዊ 

ጭቆና መፍትሄ ሳያገኝ ለሁለት አመት እንዲዘልቅ ያደረገው እንዲሁ በዘፈቀደ ምንም አያመጡም በሚለው ሳይሆን ለተንኮል 

በር ያልከፈተው የህዝብ አንድነት ስላሰጋው ነው፡፡ ይህን የህዝቦች አንድነት ለመናድ ባለ በሌለ ሃይሉ ሙስሊሙን ወደ አመጽ 

ለመምራት እጅግ አስከፊ በደሎችን ሲፈጽም ታዝበናል፡፡ እስካሁን በህዝብ ታጋሽነትና በሰላማዊ አካሄድ ለማምከን የተቻለ 

ቢሆንም፡፡


የነገው ሰልፍ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠራው ቢባልም የሁላችንንም ቤት እያስጨነቁ ያሉ ካድሬዎች ሃይማኖታቸው 


ፖለቲካ የሆኑ ቅጥረኞች አሊያም የእንጀራ ጉዳይ ያስገደዳቸው የመንግስት ሰራተኞች ናቸው፡፡ ይህ እንግዲህ ሌላኛው ምእራፍ 

መሆኑ ነው፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ በሰልፉ ላይ የሚሳተፍበት ሁለተኛው አላማም በቦታው አለመገኘት ማለት መንግስት 

የጀመረውን በህዝብ መሃል የጥላቻ እሳት የማቀጣጠሉን ሂደት መፍቀድና ክፉ ሴራው ነፍስ ዘርቶ ለሃገራችን አደጋ 

የሚሆንበትን በር ለመዝጋት ነው፡፡ በቦታው መገኘት መንግስት እየሰራ ያለውን ታረካዊ ስህተት የማረም አገራዊ ሃላፊነት፤ 

ምንም በግፍ ብንጨቆንም አገሪቷን እንደአገር ቆማ እንድትሄድ ያደረጋትን ሃይማኖታዊ መስተጋብራችንን የምንከፍለውን ዋጋ 

ከፍለን የምናስጠብቅበት ብቸኛ አማራጭ በመሆኑ ነው፡፡ በሚዲያዎች እና በስብሰባዎች የውስጥ አርበኞችን በመጠቀም 

ሃይማኖተኞችን እምነታቸው ከሚያዛቸው አብሮነት ይልቅ ለፖለቲካ ግዳጅ ሲሉ መከፋፈልን እንዲመርጡ እንዳደረገ 

የተሰማው አካል ካለ መላው የአዲስ አበባ ነዋሪ ይህ ሊሆን እንደማይችል ነገ በይፋ ያሳያል፡፡


እኛ ሙስሊሞች የነሐሴ 26ቱ ‹‹አክራሪነትን የማወገዝ ሰልፍ›› ላይ የምንገኝበት አብይ ምክንያት አክራሪነትን በማውገዝ ደረጃ 


ከእምነታችን የተቀዳ የጠነከረ መርህ ተከታዮች በመሆናችን ነው፡፡ እምነታችን የአክራሪነትን ጉዳት በግልፅ ያስተምራል፡፡ 

አጀንዳው አገራዊ ብቻ ሳይሆን ግዙፍም ነው፡፡ ይህን መርህ በመከተል በርካታ ወራትን ያስቆጠረው ሠላማዊ የተቃውሞ ሂደት 

አክራሪነትን ለማውገዝ የሞራልና የህግ ግዴታ አለበት፡፡ የዕለቱን ውሎ ሠላማዊነት አስመልክቶ ያካበትነው ልምድ እጅጉን 

እንደሚጠቅመን ጠንካራ መተማመን አለን፡፡ ሂደቱ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ ተጀምሮ ያልቅ ዘንድ የምናበረክተው የተሰባጠረ 

ሁለንተናዊ አስተዋፅኦ የዕለቱን መልዕክት በሚገባ አድርሰን ለመምጣት እጅጉን ይጠቅመናል፡፡ የሌሎች እምነት ተከታይ ወገኖች 

የተለመደ ሰላማዊ ገፅታችንን በአካል እንዲመሰክሩ እና በቀጣይ ለጥያቄዎቻችን መመለስ እንደቀዳሚው ጊዜ ሁሉ ድጋፋቸውን 

እየለገሱ እንዲቆዩም የሚያደርግ ነው፡፡

አላሁ አክበር!

Norway Partners With World Bank to Support Ethiopia

Norway Partners With World Bank to Support Ethiopia

Ethiopia, a country highly vulnerable to extreme weather events, land degradation, deforestation and food insecurity, is stepping up its efforts to fight climate change, promote sustainable rural development and build resilience.
On Friday, two agreements were signed between the Government of Norway and the World Bank to provide significant financing for sustainable land management, climate-smart agriculture and forest protection in the country.
The first agreement injects an additional US$50 million grant funds from the Government of Norway through a trust fund to co-finance the Sustainable Land Management Program (SLMP II) aimed at reducing land degradation and increasing land productivity of smallholder farmers.
In the second agreement, Norway provides US$13 million through the World Bank's BioCarbon Fund (BioCF) to support Ethiopia's Climate Resilient Green Economy (CRGE) Facility and to promote climate-smart agriculture, forest protection and land rehabilitation at the landscape level.
Norway's contribution complements initial funding of US$5 million from the United Kingdom's Department for International Development (DFID), and ongoing financing from the Forest Carbon Partnership Facility (FCPF).
"Norway is pleased to collaborate with the World Bank in supporting Ethiopia's ambitious efforts to fight land degradation, deforestation and climate change while promoting sustainable development in the land use sector," said Tove Stub, Charge d'affaires a.i., Royal Norwegian Embassy in Addis Ababa.
The two complementary programs have the potential to protect the natural resource endowment and to promote climate-smart land use in order to adapt and mitigate climate change and increase food security and resilience in a vast area of the country."
Under SLMP II, the Government of Ethiopia is building on the remarkable progress achieved during implementation of the program's first phase in reducing land degradation and increasing sustainable land and water productivity.
Under SLMP I, which started in 2008, over 190,000 hectares of degraded communal and individual farmlands have been rehabilitated and agricultural productivity has improved in areas that were hitherto found to be less productive.

በነገው እለት


                     በነገው እለት 

ክርስትና እምነት ተከታዮች ላይም ይሁን ቤተክርስቲያን ላይ አደጋ ቢደርስ፤ 


ሙስሊሞችም ላይ ይሁን መስጊድ ላይ አደጋ ቢደርስ፤

ለአደጋው ብቸኛ ተዋናይና ተጠያቂ ህወሃትና ህሊናቢስ አጅ እባሽ ቀላዋጮቹ 


ናቸው፡አክራሪ አስልምና ተከታዮች አረጉት፤ ወይም አክራሪ የክርስትና እምነት 

ተከታዮች አደረጉት ብሎ እንደተለመደው ሊቀባጥር ይችላል፡ 


ምንም አለ ምን የኢትዮጵያ ህዝብ ከ22 አመት ተሞክሮው በትክክል ህወሀትን 


የተረዳው በመሆኑ። የረጅም ጊዜውን ትተን በትናንትናው እለት ሰማያዊ ፓርቲ 

አባላትና ቢሮ ላይ የፈጸመው አሳፋሪ ተግባር ማንነቱን ፍንትው አድርጎ ያሳየበት 

ጸያፍ ተግባር ነው።

ስለዚህ ለሚፈጠረው ማንኛውም ችግር ሁሉ ተጠያቂው ህወሃትና 

አጨብጫቢዎቹ ብቻ መሆናቸው እስማሙም ሆነ ክርስቲያኑ ምዕመን ልብ 

ሊለው ይገባል። ህዝቡ አያውቀውም ለማለት ሳይሆን ለማስታወስ ብቻ ነው።


እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቅ



ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ~

ውድቀት ለዘረኞችና አምባገነኖች!!!

በረከት ስምኦን በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ እየዶለቱ ነው – (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

በረከት ስምኦን በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ እየዶለቱ ነው – (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

አቶ በረከት
በዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ሊቀመንበርንት ከሚመራው ግንቦት ሰባት ጋር በተያያዘ በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ በረከት ስምኦን የሚመሩት የመንግስት አካል በምስጢር እየዶለተ መሆኑን ምንጮች ጠቆሙ። በቅርቡ በአንድ ድረገፅ ላይ የወጣውን የዶ/ር ብርሃኑን ንግግር በማስረጃነት ይዘው እየተንቀሳቀሱ ያሉት አቶ በረከትና ተከታዮቻቸው በአገር ውስጥ እየተንቀሳቅሰ የሚገኘው ሰማያዊ ፓርቲ « ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አለው፤ ከግንቦት ሰባት የገንዘብ ድጋፍ ይደረግለታል» በሚል እነበረከት ድምዳሜ ላይ መድረሳቸውን የጠቆሙት ምንጮቹ የፓርቲውን አመራሮች «ከሽብረተኛ ቡድን ጋር በመገናኘት» ብለው ለመክሰስ ሴራ እያበጃጁ መሆኑን አስውታውቀዋል። የፓርቲው አመራሮችን ከማሰር ባለፈ «ሰማያዊ ፓርቲ በሽብርተኛ ድርጅት የሚረዳ ነው» በሚል በአገር ውስጥ የሚኖረውን የፓርቲው ቀጣይ ህልውና ለማክሰም ጭምር እየዶለቱ መሆኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል። ከበረከት በተጨማሪ ደብረፂዮን ይህንን ሴራ በበላይነት እየመከሩበት እንደሆነ ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አሜሪካ ለሚገኝ አንድ ጋዜጠኛ ከገዢው ባለስልጣናት ዳጎስ ያለ ገንዘብ እንደተላከለት የቅርብ ምንጮች አጋለጡ። መጀመሪያ 250.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ፣ በማስከተል 50.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ሃዋላ እንደተደረገለትና ባጠቃላይ 300.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) በዶላር ተመንዝሮ በእጁ እንደደረሰው ምንጮቹ ጠቁመዋል። ገንዘቡ ከነበረከት በኩል በምስጢር የተላከ መሆኑን ያጋለጡት ምንጮቹ በዚሁ መሰረት ጋዜጠኛው ለሕወሐት/ኢህአዴግ ማገልገል መቀጠሉንና በተለይ አሁን በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ እየተሸረበ ያለው ሴራ መነሻው ይህ ሰው እንደሆነ አያይዘው ገልፀዋል።

ነሐሴ 26 የመንግስት ድጋፍ ያለው የሀይማኖቶች ጉባኤ በአዲስ አበባ የጠራው ሰልፍ ያልተጠበቁ ነገሮችን ያስተናግዳል ተብሎ ይጠበቃል።

ነሐሴ 26 የመንግስት ድጋፍ ያለው የሀይማኖቶች ጉባኤ በአዲስ አበባ የጠራው ሰልፍ ያልተጠበቁ ነገሮችን ያስተናግዳል ተብሎ ይጠበቃል።

በመንግስት የሚደገፈው የሐማኖቶች ጉባኤ  በመጪው እሁድ አክራሪነት እናወግዛለን በሚል አላማ በጠራው ሰልፍ ላይ የአዲስ አበባ እና እስከ 100 ኪሎሜትር በሚደርስ ርቅት ላይ  በአጎራባች የክልል ከተሞች የሚገኙ ዜጎች በብዛት እንዲገኙ የኢህአዴግ ካድሬዎች ቤት ለቤት እየዞሩ ቅስቀሳ ሲያደርጉ ሰንብተዋል።  የመንግስት ሰራተኞች ፣ በግል ስራ የሚተዳደሩ ነዋሪዎች በሰልፉ ላይ እንዲገኙ ካልተገኙ ግን አክራሪነትን እንደደገፉ እንደሚቆጠርባቸው ሲነገራቸው መሰንበቱን ወኪሎቻችንን ዘግበዋል።
መንግስት ለፖለቲካ ትርፍ ብሎ የጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ፣ መንግስትም ራሱ ያልጠበቀውን ነገር ይዞበት ሊመጣ እንደሚችል ምልክቶች እየታዩ ነው። ድምጻችን ይሰማ የተባለው አካል ከአመት ከመንፈቅ በላይ ያካሄደውን ተቃውሞ ኢህአዴግ በጠራው ሰልፍ ላይ ተገኝቶ ተመሳሳይ ተቃውሞ እንደሚያሰማ መግለጫ ማውጣቱ እሁድ ምን ይፈጠር ይሆን የሚል ጥያቄ አስነስቷል።
ድምጻችን ይሰማ ባወጠው መርሀግብር ሙስሊሙ ማህበረሰብ የሀይማኖት አባቶች ንግግር ካደረጉ በሁዋላ ነጭ ወረቀት ወይም የጨርቅ ማህረም እንዲያውለበልቡ፣  የመጅሊስ ሹሞች ንግግር ሲያደርጉ ጆሮን በመድፈን፣ ያለምንም ድምጽ ሁለት እጅን ወደ ላይ በማንሳትና በማጠላለፍ የታሰሩት የኮሚቴ አባላት እንዲፈቱ እንደሚጠይቁ አስታውቀዋል።
ድምጻችን ይሰማ ይህን መርሀግብሩን በተግባር ካዋለ፣ አንድ መንግስት ለድጋፍ በማለት በጠራው ሰልፍ ላይ ተቃውሞ ሲስተናገድበት በታሪክ የመጀመሪያው ይሆናል። ምናልባትም ለኢህአዴግ ታላቅ የፖለቲካ ክስረት ሊያመታበት እንደሚችል አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።
ኢህአዴግ ከውርደት ለመዳን የጸጥታ ሀይሎችን በብዛት ከማሰማራት ጀምሮ የክልል ደህንነቶች ወደ አዲስ አበባ እንዲገቡ እያደረገ ነው።
ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰልፍ ሊቀጥል እንደሚችል መታወቁ ሌላ ድራማ ሊፈጥር እንደሚችልም ይጠበቃል።
ሰሞኑን በተደረገው የሀይማኖት ጉባኤ አቶ በረከት ችግሩ ጊዜ የማይሰጥ መሆኑን ሲናገሩ አቶ ሀይለማርያም ደግሞ እርምጃ እንደሚወስዱ አስጠንቅቀዋል።

ማስጠንቀቂያ በነገው ሰልፍ ለምትሳተፉ በሙሉ

ማስጠንቀቂያ በነገው ሰልፍ ለምትሳተፉ በሙሉ 


1 ወያኔ የቤተ ክርስቲያን ታቦታትን አስወጥቶ መንገድ ላይ እየሄዱ እያሉ እራሱ 


ባዘጋጀው ሰው ታቦት ላይ ጥቃት እንዲፈጸም እና እንዲረብሽ ሊያደርግ ይችላል


2, አሁንም የወያኔ አቃጣሪ የሆኑ ሙስሊሞች በክርስትና አባቶች ላይ ድንጋይ 

ሊያስወረውር ይችላሉ


3 ወያኔ እራሱ ቦንብ ሊያፈነዳ እና ሙስሊሞች ናቸው ብሎ እንደተለመደው 

ፕሮፖዳንዳ ሊሰራበት ይችላል 

4. የወያኔ ካድሬዎች ንግግር ሲያደርጉ መጥፎ ቃላትን ሊናገሩ ይችላሉ ..

ወያኔዎች ለስልናቸው ማራዘሚያ ሲሉ ይህን ከማድረግ ወደ ሃላ አይሉም 

ለዚህም ምስክር የሚሆን 

ወያኔ በትጥቅ ትግል ወስጥ እያሉ የትግራይን ህዝብ ለፖለቲካ ፍጆታ እንዲህ 


ነበር ሲቀምበት የነበር ለዚህን ገና ከመጀመሪያው ደደቢት በርሃ ውስጥ እያለ 

ጀምሮ

1/ የራሱን የትግል ሰዎችን በሃሳብ ያልተሰማሙትን ገድሉዋል

2 / ከ30 ሺ የሚበልጥ የትግራይን ህዝብ ወደ ሱዳን በማጉዋዝ በርሃብ 

ምክኒያት እና በጦርነት ነው ሃገራቸውን የለቀቁ በማለት በ video እየቀረፀ ለ 

አለም መንግስታት በማሳየት የገንዘብ መለመኛ አድርጎ ተቅሞባችዋል

3/ በሀውዜን የራሱን ወገኖች ለፖለቲካ ፍጆታ ሲል አስጨፈጨፈ

4/ የኢትዮጵያ ባንኮችን እና ቤተ ክርስቲያኖችን ሲዘርፍ እና ሲያቃጥል የነበር 

የባንዳ ስብስብ ድርጅት ነው

ስለዚህ ከዚህ አውሬ ድርጅት ይጠንቀቁ

ትግላችን የህግ የበላይነትን ወደ ማስከበር ተሸጋግሯል! ሰማያዊ ፓርቲ

ትግላችን የህግ የበላይነትን ወደ ማስከበር ተሸጋግሯል!
ሰማያዊ ፓርቲ


ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም. ባካሄደው ታላቅ ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለመንግሥት ያቀረብናቸው ጥያቄዎች መልስ ባለማግኘታቸው ለሕዝብ ቃል በገባነው መሠረት በድጋሚ ተቃውሞ ሰልፍ አቅዶ አስፈላጊውን እንቅስቃሴ እያደረገ ነው፡፡ ለዚህም ሥራ መሳካት ለሚመለከተው የመንግሥት አካል ነሐሴ 13 ቀን 2005 ዓ.ም. በደብዳቤ ያሳወቀ ሲሆን፣ መጀመሪያ ባቀረብነው ደብዳቤ ላይ ያልተካተቱ ጉዳዮችን እንድናካትት ነሐሴ 15 ቀን 2005 ዓ.ም. በተፃፈልን ደብዳቤ ተጠይቀን አስፈላጊውን መልስ አሟልተን ነሐሴ 17 ቀን 2005 ዓ.ም. በተፃፈ ደብዳቤ አሳውቀናል፡፡
በአዋጁ በግልፅ እንደተደነገገው ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ህገ መንግሥታዊ መብት እንደሆነና ማንም ሊከለክለን እንደማይችል በማያሻማ መንገድ ተገልጿል፡፡ ሰልፉን የማሳወቁ ዓላማ የጥበቃ አገልግሎትና አንዳንድ አስተዳደራዊ ድጋፎችን ለማግኘት ነው፡፡ በዚህ አሰራር ውስጥ መንግሥት የጥበቃና የቦታ ችግር ካለ ሰልፉን ለሌላ ጊዜና ቦታ እንዲያደርግ ለሚመለከተው አካል ደብዳቤ በደረሰው በ24 ሰዓት ውስጥ በፅሑፍ መልስ ይሰጣል የሚል ድንጋጌ አለ፡፡ ነገር ግን በመንግሥት በኩል ላቀረብነው የመብት ጥያቄ ምላሽ መሰጠት ሲገባው እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ የመንግሥት መዋቅር ሙሉ በሙሉ በመጠቀምና ዜጐችን አስገድዶ ሰልፍ እንዲወጡ በማስፈረም ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ በጠራበት ቀንና ቦታ ሌላ ሰልፍ በተደራቢ በሃይማኖት መቻቻል ስም ህገ መንግሥቱን በመጣስ የሃይማኖት ተቋማትን ለራሱ የድርጅት ፖለቲካ መጠቀሚያና የሰማያዊ ፓርቲን ህጋዊ እንቅስቃሴ ለመግታት እየተጠቀመበት ነው፡፡ ይህ አሰራር እንዲስተካከል መንግሥትን በመግለጫ ብንጠይቅም የተሰጠን ምላሽ ግን በሚያሳዝን ሁኔታ የሀገሪቱን ህገ መንግሥትና የሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብትን ሙሉ በሙሉ በመጣስ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ዲኤታ እንዲሁም ሰልፍ ጠሩ በተባሉ አካላት ግልፅ የሆነና የተቀነባበረ ህገ ወጥ ሴራ ሆኗል፡፡
ስለሆነም በነገው ዕለት ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም. የምናደርገው ሰላማዊ ሰልፍ ከዚህ ቀደም ያቀረብናቸው ጥያቄዎቻችን እንዲመለሱ ለመንግሥት ጥያቄ ማቅረብ ከመሆን አልፎ የህግ የበላይነትን ወደ ማስከበር አድጓል፡፡ በመሆኑም በመንግሥት የሚደረገው ዓይን ባወጣ ሁኔታ ህግን የመጨፍለቅ ተግባር እንዲቆም ለምናደርገው ትግል የኢትዮጵያ ሕዝብና ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ከጐናችን እንዲቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
ምንጊዜም የተባበረ የሕዝብ ትግል ያሸንፋል!
ነሐሴ 25 ቀን 2005 ዓ.ም.
አዲስ አበባ

Woyane Warning to Somalian's

Woyane Warning to Somalian's

Woyanes gives warning for Somalian's  those who lives & have shops in Addis Abeba,  they must Close all  there shops and  participating the Sunday demonstration other wise they will thrown in prison

Mudaaharadka #AddisAbaba Ee Berito & Soomaalida oo khasab uga qeybgelin !!!

Waxa laga bilaabay maanta magaalada AddisAbaba Ogaysiis lagu ogaysiin dadka Soomaalida ah ee ku dhaqan xaafadaha kala duwan ee magaalada inay berito u soo diyaar garooban Dibax ka dhici doona fagaaraha Maskel Squere kaas oo lagu taageerayo xukuumadda Itoobiya culimo aay dhowaan xirxirtay kuwaas oo ka soo horjeestay go'aan xukuumadu ku mamnuucday Salaadii Tajuudka Ee bishii #Ramadan

Culimada la xiray ayaa dowladu ku sheegtay qas-wadayaal waxana aay ka rabtaa dadka Muslimka ah inay taageeran qorshaha xukuumadda, Soomaalida waxa loo sheegay in beri qofkii aan ka soo qeyb gelin banaanbaxa oo meheradiisu u furnaato ama aqalkiisa hoosta ka gala inu ciqaab la kulmi doono tan oo aad moodo inay tahay cabudhin, waayo dowladu waxay ugu hanjabi qofkii aan ka soo qeyb gelin dibadbaxa inu yahay 

የሰማይዊ ፓርቲ አመራሮች በስብሰባ ላይ እንዳሉ የወያኔ ፌደራል ፖሊስ ቢሮውን በመክበብ ሁሉንም የአመራር አባላትን በመኪና ጭኖ ወደ እስር ወስደዋቸዋል።Semayawi Party headquarters under siege


Semayawi Party headquarters under siege



Semayawi Party headquarters in Addis Ababa has been surrounded by a heavily armed 

Federal Police squad. Over 100 party members and organizers including the party chairman 

Eng. Yilkal Getnet have been put under siege. The party’s head of legal affairs Yidenekachew 

Kebede is reportedly arrested while talking to ESAT.


In a warning broadcast last night on the state-controlled radio and TV, the regime had 

threatened that it would take actions against any protests and agitations.  Yidenakechew told 

ESAT that the siege was illegal as is Semayawi Party was only organizing a peaceful protest. 

“It is a shame and upsetting that the government taking such an illegal measure. He said the 

party was only preparing for a peaceful protest it called for tomorrow

ከምሽቱ 1:00 ላይ የሰማይዊ ፓርቲ አመራሮች አራት ኪሎ 

አካባቢ በሚገኘው ጽ/ቤታቸው በስብሰባ ላይ እንዳሉ የወያኔ 

ፌደራል ፖሊስ ቢሮውን በመክበብ ሊቀ-መንበሩን ጨምሮ 

ሁሉንም የአመራር አባላትን በመኪና ጭኖ ወደ እስር 

ወስደዋቸዋል።በውጭም በውስጥም የሚኖረው መላው 

የኢትዮጵያ ህዝብ ድርጊቱን እንዲያወግዝና ለአለም-አቀፍ 

ተቁማትም ሁኔታውን እንዲያሳውቅ ጥሪ ቀርቧል። ሞት ለወያኔ 

ትግሉ ይቀጥላል።

Semayawi Party office in Addis Ababa is surrounded 

by heavily armed police

Today, 12:45The headquarters of an Ethiopian 


opposition group, Semayawi Party, has been 

surrounded by heavily armed Federal Police troopers 

today following an announcement by the party to call 

another peaceful demonstration. 
                   
                  የሰማያዊ ፓርቲ መግለጫ፤

ትግላችን የህግ የበላይነትን ወደ ማስከበር ተሸጋግሯል!

ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም. ባካሄደው ታላቅ ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለመንግሥት 


ያቀረብናቸው ጥያቄዎች መልስ ባለማግኘታቸው ለሕዝብ ቃል በገባነው መሠረት በድጋሚ ተቃውሞ ሰልፍ አቅዶ 

አስፈላጊውንእንቅስቃሴ እያደረገ ነው፡፡ ለዚህም ሥራ መሳካት ለሚመለከተው የመንግሥት አካል ነሐሴ 13 ቀን

2005ዓ.ም. በደብዳቤ ያሳወቀ ሲሆን፣ መጀመሪያ ባቀረብነው ደብዳቤ ላይ ያልተካተቱ ጉዳዮችን

እንድናካትት ነሐሴ 15 ቀን 2005 ዓ.ም. በተፃፈልን ደብዳቤ ተጠይቀን አስፈላጊውን መልስ አሟልተን ነሐሴ 17 

ቀን 2005 ዓ.ም. በተፃፈ ደብዳቤ አሳውቀናል፡፡

በአዋጁ በግልፅ እንደተደነገገው ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ህገ መንግሥታዊ መብት እንደሆነና ማንም ሊከለክለን 

እንደማይችል በማያሻማ መንገድ ተገልጿል፡፡ ሰልፉን የማሳወቁ ዓላማ የጥበቃ አገልግሎትና አንዳንድ አስተዳደራዊ 

ድጋፎችን ለማግኘት ነው፡፡ በዚህ አሰራር ውስጥ መንግሥት የጥበቃና የቦታ ችግር ካለ ሰልፉን ለሌላ ጊዜና ቦታ 

እንዲያደርግ ለሚመለከተው አካል ደብዳቤ በደረሰው በ24 ሰዓት ውስጥ በፅሑፍ መልስይሰጣል የሚል ድንጋጌ 

አለ፡፡ ነገር ግን በመንግሥትበኩል ላቀረብነው የመብት ጥያቄ ምላሽ መሰጠት ሲገባው እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ 

የመንግሥት መዋቅር ሙሉ በሙሉ በመጠቀምና ዜጐችን አስገድዶ ሰልፍ እንዲወጡ በማስፈረም ሰማያዊ ፓርቲ 

ሰልፍ በጠራበት ቀንና ቦታ ሌላ ሰልፍ በተደራቢ በሃይማኖት መቻቻል ስም ህገ መንግሥቱን በመጣስ የሃይማኖት 

ተቋማትን ለራሱ የድርጅት ፖለቲካ መጠቀሚያና የሰማያዊ ፓርቲን ህጋዊ እንቅስቃሴ ለመግታት እየተጠቀመበት 

ነው፡፡

ይህ አሰራር እንዲስተካከል መንግሥትን በመግለጫ ብንጠይቅም የተሰጠን ምላሽ ግን በሚያሳዝን ሁኔታ የሀገሪቱን 

ህገ መንግሥትና የሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብትን ሙሉ በሙሉ በመጣስ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን 

በኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ዲኤታ እንዲሁም ሰልፍ ጠሩ በተባሉ አካላት ግልፅ የሆነና የተቀነባበረ ህገ ወጥ 

ሴራ ሆኗል፡፡ ስለሆነም በነገው ዕለት ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም.የምናደርገው ሰላማዊ ሰልፍ ከዚህ ቀደም 

ያቀረብናቸው ጥያቄዎቻችን እንዲመለሱ ለመንግሥት ጥያቄ ማቅረብ ከመሆን አልፎ የህግ የበላይነትን ወደ 

ማስከበር አድጓል፡፡ በመሆኑም በመንግሥት የሚደረገው ዓይን ባወጣ ሁኔታ ህግን የመጨፍለቅ ተግባር እንዲቆም 

ለምናደርገው ትግል የኢትዮጵያ ሕዝብና ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ከጐናችን እንዲቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ምንጊዜም የተባበረ የሕዝብ ትግል ያሸንፋል!

ነሐሴ 25 ቀን 2005 ዓ.ም.

አዲስ አበባ

Semayawi Party headquarters under siege

Saturday, August 31, 2013 @ 03:08 PM ed
Semayawi Party headquarters in Addis Ababa has been surrounded by a heavily armed Federal Police squad. Over 100 party members and organizers including the party chairman Eng. Yilkal Getnet have been put under siege. The party’s head of legal affairs Yidenekachew Kebede is reportedly arrested while talking to ESAT.
In a warning broadcast last night on the state-controlled radio and TV, the regime had threatened that it would take actions against any protests and agitations.  Yidenakechew told ESAT that the siege was illegal as is Semayawi Party was only organizing a peaceful protest. “It is a shame and upsetting that the government taking such an illegal measure. He said the party was only preparing for a peaceful protest it called for tomorrow

የሰልፎች ውዝግብ በአዲስ አበባ

የሰልፎች ውዝግብ በአዲስ አበባ

የተለያየ ዓላማ የላቸው ሁለት ሰላማዊ ሰልፎች በተመሣሣይ ቁንና ሰዓት መስቀል 

አደባባይ ላይ ተጠርተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የሰማያዊ ፓርቲ ውዝግብ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የሰማያዊ ፓርቲ ውዝግብ
የሰልፎች ውዝግብ በአዲስ አበባ

የተለያየ ዓላማ የላቸው ሁለት ሰላማዊ ሰልፎች በተመሣሣይ ቁንና ሰዓት መስቀል አደባባይ ላይ ተጠርተዋል፡፡

ይህ የአዲስ አበባ አስተዳደርና ሰማያዊ ፓርቲ እየተወዛገቡበት ያለ ጉዳይ ነው፡፡

በሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የተጠራው አክራሪነትንና ፅንፈኝነትን የማውገዝ ዓላማ ያለው ሰልፍ የፊታችን ዕሁድ ነኀሴ 26/2005 ዓ.ም መስቀል አደባባይ እንዲካሄድ ፍቃድ መሰጠቱን የአዲስ አበባ አስተዳደር አስታውቋል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ በበኩሉ “በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ የተቃውሞ ሰልፍ ለማካሄድ በቅድሚያ የጠየቅነው እኛ ነን፤ በማካሄድም እንገፋበታለን” ብሏል፡፡

“ይህ አባባል ሕገወጥና ዕብሪት ነው” ያለው የአዲስ አበባ አስተዳደር በበኩሉ “ቀድሞ ጥያቄ ያቀረበው የሃይማኖት ጉባዔ ነው” ብሏል፡፡

በምርጫ ያጣነውን የፓርቲዎች ክርክር በ”ፀረ ሽብር ህጉ” አገኘነው!

በምርጫ ያጣነውን የፓርቲዎች ክርክር በ”ፀረ ሽብር ህጉ” አገኘነው!

  • የአንድነት “ጥይት ተናጋሪ” በኢህአዴግ “የተገፋ” ነው ተባለ
  • ዶ/ር` መረራ የኢትዮጵያን ፖለቲካ የበላውን ቡዳ ይጠይቃሉ?
እናንተዬ፤ የሰሞኑን የፖለቲካ ድባብ እንዴት አገኛችሁት? (የአውራው ፓርቲና የተቃዋሚዎችን ማለቴ ነው!) ድንገት ሳናስበው ተሟሟቀ አይደል? (ዕድሜ ለፀረ - ሽብር ህጉ!) በእርግጥ ኢህአዴግና ተቃዋሚዎችም ምስጋና ይገባቸዋል (ልብ ስለገዙ!) እንዴ…ዋናውን ተመስጋኝ ዘነጋሁት እኮ! (ብራቮ ኢቴቪ!) እውነቴን ነው የምላችሁ…ባለፈው ሳምንት በኢቴቪ “የፀረ ሽብር ህጉና የፓርቲዎች አቋም” በሚል ርዕስ የተላለፈው ውይይት ተወዳጅ እንደነበር መረጃዎች ደርሰውኛል (ኤልፓ ግን አሻጥር ሰርቷል!)
በነገራችሁ ላይ ከ97 ምርጫ ወዲህ የታየ ትልቅ የዲሞክራሲ ጭላንጭል እኮ ነው (የሰይጣን ጆሮ አይስማብን!) ግን ደስ አይልም …ገዢው ፓርቲና ተቃዋሚዎች በትልቅ የአገር ጉዳይ (አዋጅ) ላይ ህዝብ ፊት ሲሟገቱ! (Live ባይሆንም አናማርርም)
አንድ ምስጢር ልንገራችሁ፡፡ ለኢህአዴግ እንዳትነግሩብኝ ታዲያ! (promise?) በጣም ጥሩ! ለአንድ ዓመት በጠ/ሚኒስትርነት የመሩን የተከበሩ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ገና ሥልጣን ሲይዙ አስረግጠው እንደተናገሩት “የመለስን ሌጋሲ” በእርግጥም እያስቀጠሉ ነው፡፡ ራዕያቸውንም እያሳኩ ነው፡፡ ይሄውላችሁ… ዝም ብሎ የካድሬ ዲስኩር እንይመስልብን መረጃና ማስረጃ እየጠቀስን ብናወጋስ… (እንደሰሞኑ የፓርቲዎች ውይይት!) በአንደኛ ደረጃ የሚጠቀሰው ምን መሰላችሁ? ጠ/ሚኒስትሩ በሙስና ላይ የወሰዱት ቁርጠኛ እርምጃ ነው፡፡ በአንድ ዓመት ብቻ ስንት ተጠርጣሪ ሙሰኛ እንደተያዘ እስቲ ቁጠሩት… (እኔማ መቶ ከደረስኩ በኋላ መቁጠሩን ትቼዋለሁ!) ጠ/ሚኒስትሩ የገቡትን ቃል የፈፀሙት በሙስናና በሙሰኞች ላይ ብቻ አይደለም፡፡ በፓርላማና በኢቴቪ ያየናቸው በጐ ለውጦችም የመለስን ሌጋሲ ለማስቀጠል በአቶ ኃ/ማርያም አስተዳደር የተከናወኑ ተግባራት አካል ናቸው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተቃዋሚዎች የጨዋታ ሜዳ (እነሱ ምህዳር ይሉታል!) እየሰፋ መምጣቱን ማንም ሊክደው አይችልም፡፡ (ከ97 ምርጫ ወዲህ ሜዳው ጠብቦ ነበር አልተባለም?) አንድነት ፓርቲ ብቻውን በአንድ ወር ያካሄደውን ሰልፍ ብቻ መቁጠር በቂ ነው፡፡ አንዳንድ የ”ከፋፍለህ ግዛ” ስትራቴጂ አቀንቃኞች ምን እንደሚሉ ታውቃላችሁ? እነዚህ ሁሉ በጐ ለውጦች ከኢህአዴግ ሳይሆን ከአዲሱ ጠ/ሚኒስትር የፈለቁ ናቸው ይላሉ (ከፋፋዮች በሏቸው!) እነዚህ ወገኖች ያልገባቸው አንድ ነገር አለ፡፡ ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ሥልጣን እንደያዙ ከውጭ ጋዜጠኛ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፣ ምን ራዕይ እንዳላቸው ተጠይቀው፤ የሳቸው ራዕይ የፓርቲያቸውን ራዕይ ማስፈፀም እንደሆነ በማያሻማ ቋንቋ ተናግረዋል፡፡ ስለዚህ ማናቸውም ለውጦች ከግለሰብ ሳይሆን ከፓርቲው እንደሚመነጩ ማወቅ ብልህነት ነው፡፡ (እኛ ከለውጡ እንጂ ከባለቤቱ ምን አለን?)
እስቲ አሁን ደሞ አንዲት ቁምነገር አዘል ቀልድ ጣል ላድርግላችሁ፡፡ (ዘና እንድትሉ እኮ ነው!)http://andenatethiopia2012.blogspot.no/2013/08/blog-post_8221.html
ዶክተር ጌታቸው ቦሎዲያ የዩኒቨርስቲ የባዮ-ኬምስትሪ አስተማሪ ነበር፡፡ ተጨዋች፣ እንደልቡ የሚናገር፣ በህይወት ሳለ ለመንግሥት ባለስልጣናት ግድ የሌለው፣ በራሱና በእውቀቱ የሚተማመን ሳይንቲስት ነበር፡፡ (እንዲህ ያለ ምሁር እንደ ዳይኖሰር ጠፍቷል ልበል?) አንድ ጊዜ ከስድስት ኪሎ ወደ አራት ኪሎ ሲመጣ አንድ የስድስት ኪሎ ተማሪ ጭኖ (lift ሰጥቶ) ይመጣል፡፡ አራት ኪሎ ወደ ሳይንስ ኮሌጅ እየተቃረቡ ሲመጡ ተማሪውን እንዲህ ሲል ጠየቀው፡፡ ዶ/ር ጌታቸው ወንድንም ቢሆን አንቺ ማለት ይቀናዋል፡፡
“የት ነው የምትማሪው?”
ተማሪው - ስድስት ኪሎ
ቦሎዲያ - ስንተኛ ዓመት ነሽ?
ተማሪው - አራተኛ ዓመት፤ ዘንድሮ እጨርሳለሁ
ሳይንስ ኮሌጅ አጠገብ አቁሞ እያወረደው፡
ቦሎዲያ - ቆይ ቆይ፤ ምንድነው የምታጠኚው ለመሆኑ?
ተማሪው - ፖለቲካል ሳይንስ
ቦሎዲያ - በይ በይ፤ ሳይንሱን ለእኔ ተይና ፖለቲካሽን ይዘሽ ውረጂ! (ምንጭ - አዲስ አድማስ)
ምሁሩ እኮ እውነታቸውን ነው፡፡ ፖለቲካ ብሎ ሳይንስ እኮ የለም - በተለይ በጦቢያ ምድር! ፖለቲካ እኮ እኛ አገር ሃሜትና አሉባልታ ነው፡፡ ፖለቲካ እኮ እኛ አገር ጠብና መጠላለፍ ነው፡፡ ፖለቲካ እኮ እኛ አገር የቀውስና የጥርጣሬ ምንጭ ነው፡፡ ፖለቲካ እኮ እኛ አገር መካካድና መዘላለፍ ነው፡፡
በነገራችሁ ላይ የመድረክ አመራር አባል የሆኑት ዶ/ር መረራ ጉዲና፤ “የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምስቅልቅ ጉዞና የህይወቴ ትዝታዎች” በሚል ርእስ በቅርቡ ለንባብ ያበቁት ጉደኛ መጽሐፍ አላቸው፡፡ እናላችሁ… መፅሃፉን ብታነቡት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከጐጂ ልማዳዊ ድርጊቶች መመደብ እንዳለበት ትገነዘባላችሁ፡፡ (ዶ/ር መረራ ከተቃዋሚ ፓርቲ አመራርነታቸው በተጨማሪም የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ናቸው፡፡) በመፅሃፋቸው ጀርባ ላይ ስለ ዶ/ር መረራ የፖለቲካ ህይወት የቀረበው አጭር መረጃ እንዲህ ይላል ፡- “በፖለቲካው ዓለም፤ ከ1960ዎቹ የኢትዮጵያ ተማሪዎች እንቅስቃሴ እስከ ዛሬ በዘለቀው የኢትዮጵያ ሕዝቦች የመብት ትግል ውስጥ በመሳተፍ ሦስት መንግሥታትን ታግሏል፡፡ በደርግ ዘመን ለሰባት ዓመታት የፖለቲካ እስረኛ ሲሆን፣ ከ1997 እስከ 2002 የሀገሪቱ ፓርላማ አባል ነበር፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ኮንግረስና የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ የሚባሉ ድርጅቶችንና የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ህብረትና መድረክ የሚባሉ ጥምረቶች በሊቀመንበርነት መርቷል”
አያችሁልኝ… ፖለቲካ በእኛ አገር ሙያ (career) ሳይሆን ትግል ነው - ሲከፋ ለሞትና ለዝንተዓለም እስር ይዳርጋል፡፡ ካልከፋ ደግሞ ከአገር ያሰድዳል (ስደት እኮ ሰፊ ወህኒ ቤት ነው!) ዛሬ እንደው ላጓጓችሁ ብዬ እንጂ የዶ/ር መረራን መፅሃፍ የመቃኘት ዓላማ የለኝም፡፡ እንጂማ ስንት አጀብ የሚያሰኙ ታሪኮችና ገጠመኞችን እንደያዘ አልነገራችሁም፡፡ ሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ፡፡ በባዶ ከምንለያይ ግን እስቲ አንዲት ነገር ከመጽሐፉ ላጋራችሁ፡፡ የኢትዮጵያዋና ችግሮች ሦስት ናቸው ይላሉ - ምሁሩ፡፡ አንደኛው - የትግራይ ልሂቃን “ስልጣን ወይም ሞት” ብለው ሥልጣንን የሙጥኝ ማለታቸው (የአባታቸው ርስት አደረጉት ለማለት ይመስላል)፣ ሁለተኛው - የአማራው ልሂቃን የኢትዮጵያዊነት ሰርተፊኬት (ሊቼንሳ) ሰጪ ነን ባይነት (የዜግነት ብቃትና ደረጃ አውጪ ማን አደረጋቸው ማለታቸው ነው) ሦስተኛው - የኦሮሞ ልሂቃን ብዙ ህዝብ ይዞ ልገንጠል ማለት (ግንድ እንዴት ይገነጠላል እያሉ ነው!)… እነዚህ ሦስት ጉዳዮች ካልተለወጡ አደጋው ይቀጥላል ባይ ናቸው - ዶ/ር መረራ፡፡ (የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ስለሆኑ እመኗቸው!)
የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንትና የአሁኑ የአንድነት ፓርቲ ሊ/መንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ስለመፅሃፉ በሰጡት አስተያየት፤ “ዶ/ር መረራ ጉዲና የኦሮሞ ህዝብ የመብት ትግል ከተቀሩት የኢትዮጵያ ህዝቦች የመብት ትግል ጋር በማቀናጀት ሰፊ ሚና በመጫወት ላይ የሚገኝ ታጋይ ምሁር ነው፡፡ በህዝቦች እኩልነት ላይ የተመሰረተች ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንድትፈጠር የሚመኝ ሁሉ ሊያነበው የሚገባ መፅሃፍ ነው” ብለዋል፡፡ ከዶ/ር ነጋሶ ሃሳብ ጋር እስማማለሁ፡፡ ግን የምጨምረውም አለኝ፡፡ ከ1960ዎቹ የተማሪዎች እንቅስቃሴ ጀምሮ እስከዛሬ የዘለቀውን የጦቢያ የመጠላለፍ ፖለቲካ ፍንትው አድርጐ የሚያሳይም መጽሐፍ መሆኑን ልገልጽላችሁ እወዳለሁ፡፡
በዚያ ላይ ዶ/ር መረራ አዋዝተው ስለፃፉት በእርግጥም መነበብ ያለበት የፖለቲካ መፅሃፍ ነው ባይ ነኝ፡፡ (ኮሚሽን የተከፈለኝ እንዳይመስላችሁ!) አንድ የገረመኝ የዶ/ር መረራ አባባል አለ - መጽሐፋቸው መጨረሻ ላይ፡፡ “የኢትዮጵያ ፖለቲካ ቡዳ ማነው” ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡ (ፖለቲካ ሳይንስ አይደለም አላልኳችሁም!)
እኔ የምላችሁ… ባለፈው ረቡዕ ማታ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን በኢቴቪ የሰጠውን መግለጫ ሰምታችኋል? “አገልግሎቴን አሻሽያለሁ” እኮ ነው ያለን! ባለፈው ሳምንት በመብራት መቋረጥ የተነሳ በኢቴቪ የተላለፈውን የፀረ ሽብር ውይይት አልተከታተልንም ለሚሉ ዜጐች ምላሹ ምን ይሆን? እኔማ ለእነዚህ ተበዳዮች የፊርማ ማሰባሰብ ዘመቻ ጀምሬአለሁ - ኤልፓን ለመክሰስ፡፡ (እኔ እንደ “አንድነት” ሚሊዮን ድምጽ አልፈልግም፤ 100 ይበቃኛል!) አንዲት ወዳጄ ስለ “ኤልፓ” ተነስቶ (ስለእሱ ሳይነሱ ውሎ ማደር እኮ አልተቻለም!) ያወጋችኝን ላካፍላችሁ፡፡
“ልጄ አፏን የፈታችው በምን እንደሆነ ታውቃለህ?”
“በምንድነው?”
ያው “አባ፣ እሚ” በሚለው መስሎኝ ነበር፡
“በራ… ጠፋ… በሚሉት ቃላት ነው”
(አይገርምም!)
ገባችሁ አይደል… መብራቱ አስሬ እየጠፋ ሲመጣ “በራ ጠፋ” እያለች አፏን ፈታች ማለቷ እኮ ነው፡፡ ይሄ መቼም አሳዛኝ ክስተት ነው አይደል? ምናልባት ኤልፓ በዚህ መልኩ መገለፁ “ያኮራኛል!” ሊለን ይችላል፡፡ (ይኩራ፤ መብቱ ነው!) ለእኛ ግን “አገልግሎቴን አሻሽያለሁ” የሚለውን “የአንደበት ግልጋሎቱን” (ከሰሞኑ የኢህአዴግ ሹመኛ ንግግር ቃል በቃል የቀዳሁት ነው!) ይተወንና መብራቱን እንደድሮው በፈረቃ ያድርግልን! ሰሞኑን ካመለጠን የፓርቲዎች ውይይት በተጨማሪ በመብራት ድንገተኛ መቋረጥ በየቤታችን የተቃጠለውን ቲቪ፣ ሬዲዮና ሌሎች ቁሳቁሶች “ሆድ ይፍጀው” ብለናል፡፡ (የፒቲሺን ዘመቻው እስኪጠናቀቅ!)
ባለፈው ሳምንት በዚሁ ጋዜጣ ላይ የወጣውን “የኢንጂነር ሃይሉ ሻውልና የኖርዌይ ኤምባሲ ውዝግብ” የተመለከተ ዜና አንብባችኋል? ለብዙ አመታት መኢአድን በሊ/መንበርነት የመሩት ኢንጂነሩ፤ የፓርቲያቸውን የእርስ በርስ ፉክቻ ተገላገልኩ ሲሉ የኤምባሲ ንትርክ ደግሞ ገጠማቸው፡፡ (የአገራቸውን ጉዳይ ሲገላገሉ የቤታቸው ጠበቃቸው!) እኔ ግን ስጠረጥር ኤምባሲው ኢንጂነሩን በደንብ ያወቃቸው አልመሰለኝም፡፡ እንዴ…ያፈነገጡ የመኢአድ አመራሮችን ተጋትረው ሲበቃቸው ሲሉ እኮ ነው ከፖለቲካ ጡረታ የወጡት፡፡ (ውዝግብ ብርቃቸው አይደለም ለማለት ነው!) “በፀባይ ቤቴን ካለቀቁ ከጐን አጥሩን አፍርሼ እገባለሁ” ያሉት ነገር ግን አልተመቸኝም፡፡ ኤምባሲ ማለት አገር ማለት ነው ይባል የለ፡፡ በኋላ የኖርዌይን ግዛት ደፈራችሁ ብንባልስ? (ኢንጂነሩ ለጦቢያ ክብር ሲሉ ቢታገሱ ጥሩ ነው!) በነገራችሁ ላይ የመኢአዱ የቀድሞ ሊ/መንበር ከኖርዌይ ኤምባሲ ጋር ሲወዛገቡ፣ የአንድነት ሊ/መንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ደግሞ ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር ተወዛግበዋል ሲባል ሰምቻለሁ፡፡ (ተቃዋሚዎችንና ኤምባሲዎች የበላቸው ቡዳ አልታወቀም!) ኤምባሲው ለፓርቲው ሊ/መንበርና ለህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ቪዛ ተጠይቆ ለዶ/ር ነጋሶ እንጂ ለህዝብ ግንኙነት ሃላፊው አልሰጥም ማለቱ ነው ውዝግቡን ያስነሳው፡፡ (አሜሪካ ኤምባሲ መኪናና ቪላ ለሌለው ቪዛ አይሰጥም እኮ!)
እኔ የምላችሁ…በነገው ዕለት ሁለት ሰላማዊ ሰልፍ ያዘጋጁ ቡድኖች “እኔ ነኝ የቀደምኩት” በሚል ተፋጠዋል የሚባለው ከምር ነው እንዴ? እኔ እኮ ሰሞነኛ ቀልድ መስሎኝ ነበር፡፡
በጣም እኮ ነው የሚገርመው… (ለቀልድም እኮ አይመችም!) በአገር አመራር ደረጃ የምናስባቸው ወገኖች “እኔ ነኝ የቀደምኩት” የሚል ንትርክ እንዴት ይገጥማሉ? (የልጆች ፉክክር አስመሰሉት እኮ!) በሰላማዊ ሰልፎች የሚቀርቡ ጥያቄዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ፈጣን ምላሽ ቢሰጣቸው እንኳ “እሺ ይሁን” ብለን እናልፈው ነበር፡፡
ግን ደግሞ እውነታው እንዲያ እንዳልሆነ አሳምረን እናውቃለን፡፡ በዚያ ላይ የጊዜ እጥረት እንደሌለብን እንኳን እኛ ነጮቹም ያውቁታል፡፡ (እዚህ አገር ርካሹ ነገር ምን ሆነና?) ታዲያ ለምኑ ነው እልህ መገባባቱ (ጐበዝ አገር በእልህ አትመራም!) እናላችሁ ሰልፉ ዛሬም …ነገም…ሳምንትም…የዛሬ ወርም ቢደረግ ችግሩ ምንድነው? (ወይስ አዋቂ ነግሮአቸው ነው!) በተለይ ደግሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች…የሚያምርባችሁ እንደሰሞኑ የሃሳብ ፍልሚያ ስታደርጉ እንጂ እልህ ስትጋቡ አይደለም፡፡ (ከነገ በኋላ ሰላማዊ ሰልፍ ይታገዳል ተባለ እንዴ?)
እኔ የምለው… በፀረ ሽብር ህጉ ላይ ፓርቲዎች ባደረጉት ክርክር ማን የረታ ይመስላችኋል? አንዳንዶች “ተቃዋሚዎች አስገቡለት” ሲሉ ሰምቻለሁ - ለኢህአዴግ መሆኑ ነው፡፡ ለእኔ ግን ሁለቱም አሸናፊዎች ናቸው፡፡ ቁጭ ብለው መነጋገራቸው በራሱ ባለድል ያደርጋቸዋል፡፡ እኔ የምለው ግን አንድነት ጥይት የሆነ ወጣት ተናጋሪ ከየት አመጣ? ቀድሞ ኢህአዴግ የነበረና “ተገፍቶ” (ፖለቲካዊ በደል ደርሶበት ማለቴ ነው) የተቃዋሚውን ጐራ የተቀላቀለ ወጣት ነው የሚል አሉባልታ ሰምቻለሁ፡፡ እውነት ከሆነ ኢህአዴግ እንዴት እንደሚቃጠል አስቡት! (በራስ ጥይት መመታት እኮ ነው!) ምን ትዝ አለኝ መሰላችሁ… በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እየተገፉ ተሰደው ለሌላ አገር የሚሮጡ አትሌቶቻችን! በየውድድሩ እያሸነፉ የሌላ አገር ባንዲራ ሲያውለበልቡ አልተቆጨንም? (በእጅ ያለ ወርቅ እየሆነብን እኮ ነው!)
በመጨረሻ አንድ ሃሳብ ላቅርብና ልሰናበት (የሚሰማኝ ካለ) በሰሞኑ የፓርቲዎች ውይይት ኢህአዴግ “ፖለቲካዊ ውሳኔ” በሚል ባነሳው ጉዳይ ላይ ሌላ የውይይት ፕሮግራም ቢዘጋጅስ?
(ነገሮች እንዲጠሩ እኮ ነው!) አያችሁ ይሄ የውይይት ባህል ከዳበረ መፍትሔዎች ከውይይት መወለድ ይጀምራሉ፡፡ ኢቴቪም በዚያው አንድ ተወዳጅ ፕሮግራም ፈጠረ ማለት እኮ ነው፡፡ (ይሄም “ፖለቲካዊ ውሳኔ” ይፈልጋል እንዳትሉኝ?)

የህወሀት/ኢህአዴግ መፈረካከስ!!

የህወሀት/ኢህአዴግ መፈረካከስ!!

ህወሀት/ኢህአዴግ ከመለስ ሞት 


በኋላ እየተሰናጠጠቀ እና እየፈራረሰ ነው።

ከመለስ በኋላ የተከሰቱ አበይት ሁነቶችን እስኪ እንመልከት፦

=>የአዲስ አበባ ምክር ቤት አመራር በአሜሪካ ጥገኝነት 


መጠየቅ

=>የጁነዲን ሳዶ ከሀገር መሰደድ

=>የስብሀት ነጋ ከመጋረጃ ጀርባ ወደ ህወሀት አመራር 

መምጣት

=>የመላኩ ፋንታ እና የገብረውሀድ እስር ቤት መግባት

=>የአዲስ አበባ የመሬት አስተዳደር ኃላፊ በሙስና መታሰር

=>የአዜብ መስፍን ከኢፈርት አመራር መነሳት

=>ከጌታቸው አሰፋ ጋር የማይስማሙት የአገር ውስጥ 

የደህንነት መምሪያ ሃላፊው አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል 

በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው መታሰር

.
.
.
.
.ወ.ዘ.ተ

የቀረውን እናንተ ጨምሩበት::


ሀናመታሰቢያ 25/12/05