Wednesday, July 13, 2016

የጎንደር ውጥረት ወደሌላ አካባቢ ሊዛመት መሆኑ እየተነገረ ነው።

ለመላው አማራ ተወላጆች ጥሪ እየተበተነ ይገኛል በማለት ከአካባቢው እየተነገረ ነው 
በጎጃም ደብረማርቆስ ባህርዳር ውጥረቱ ሊፈነዳ መሆኑ ተሰምቷል በደሴ እንዲሁ የወጣቶች ቁጣ በስጋት ተወጥሯል ሁለተኛው ቀኑን የያዘው የጎንደር ሕዝባዊ ንቅናቄ በአዲስ አበባ ሳይቀር ነዋሪው በትኩረት እየተከታተለ የሚገኝ አስደንጋጭ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል።
ጎንደር የመንግስት ተቋም አሁን አብቅቶለታል በተቆጣው ሕዝብ መውደሙ ቀጥሏል አሁን እንደከዚ ቀደም ጎንደር አይገኝም መንግስት አልባ ሆኗል ሕዝቡ ወደቤት መሄድ አይታሰብም በማለት አደባባዩን ዘግቶ እዛው ሊያድር ወስኗል የህወሓት ሰዎች መኖሪያ እና የንግድ ማዕከሎች በሙሉ በየስፍራው እየተቃጠለ መሆኑ ሁኔታ ወደከፋ ደረጃ ተዳርሷል።
በዚህ ሰዓት ጎንደር በሕዝብ ተቃውሞ ምክንያት ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ ይገኛል ከፍተኛ ቁጭትና እልህ የተሞላው የጎንደር ወጣት ስሜቱ ያስደነገጣቸው የህወሓት ሰዎች የብአዴን አመራር ቤታቸውን ጥለው ወደ ባህርዳር እንዲሁም ወደትግራይ ክልል በድንጋጤ እየወጡ ይገኛል ጎንደር በሕዝብ ስር ወደቀች።

No comments: