ጎንደር ከተማ ዛሬም ከህወሃት ከቁጥጥር ስር ዉጭ መሆንዋን ከስፍራው በስልክ ያነጋገርናቸው እማኞች ገልጸዋል። እንደ እማኞቹ ከሆነ ከተማዋ የጦርነት ቀጠና መስላለች። የገዥው ፓርቲ ልዩ ሃይል በከባድ መሰርያ የተጀበ ተኩስ በህዝቡ ላይ ቢያወርድበትም፣ ይህንን ለመመከት ከገጠር ወደ ከተማ የሚጎርፈውን የአርማጨሆ ህዝብ ሊያግደው አልቻለም።
የከተሜው ህዝብ በበኩሉ የወያኔ ነብረት ናቸው ያለቸውን ሱቆች የንግድ ድርጅቶች ማጋየቱን ተያይዞታል። ገዥው ፓርቲ ችግሩን በመግባባት ከመፍታት ይልቅ የሃይል እርምጃ ለመውሰድ መምረጡ ነው የህዝቡን ቁጣ ያባባሰው። በትላንትናው እለት የወልቃይት ሕዝብ የማንነት ጥያቄ የኮሚቴ አባላት ታፍነው መወሰዳቸው ይታወሳል።
ከአባላቱ አንዱ ኮሎኔል ደመቀ ዘዉዱ ሲሆኑ እሳቸው “እጄን አልሰጥም” በማለት ከህወሃት ወታደሮች ጋር መታኮሳቸው ተደምጧል። ኮሎኔል ደመቀ እስከአሁን በሕዝብ እየተጠበቁ ይገኛሉ።
ከስፍራው በስልክ ያነጋገርናቸው እማኞች እንደገለጹት በዛሬው እለተ-እሮብም በህዝቡ እና ከውጭ በመጡ ልዩ የህወሃት ወታደሮች መሃል ከፍተኛ ውግያ እየተካሄደ ይገኛል።
No comments:
Post a Comment