Sunday, July 3, 2016

የስብሃት ነጋ የክብር ዶክትሬት እና ቅለቱ



‹‹አሁን ታሪክ የሚያበላሸው ኣቦይ ስብሓት ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ነበር፡፡. . .የአውራጃ፣ የወረዳ፣ የጎጥ ምንጭ አቶ ስብሓት ነጋ ናቸው፤›› አቶ ኣስገደ፡፡
ግሩም ነው:: ስብሃት ነጋ የክብር ዶክትሬት ተበረከተላቸው:: በመጀመርያ ስሰማ ማመን አቅቶኝ ነበር:: ሳቄም መጥቶ ነበር:: በኋላ ግን ምክንያቱን ለማንበብ ጓጓሁ:: ለመሆኑ ለስብሃት የክብር ዶክትሬት የተሰጠበትን ምክንያት ምንድነው ብዬ ብዙ ድረ ገጾችን አሰስኩ:: ሆርን አፌርስ ብቻ ምክንያቱን አስቀምጦታል::
"Sibhat has made a historic move in the smooth, democratic and peaceful political power transfer to young and capable successors by becoming exemplary in handing over his power to his successors enthusiastically and purposefully."
ከጽሁፉ መረዳት እንደሚቻለው ስብሃት ነጋን ዲሞክራሲያዊ : ሰላማዊና ወዘተ አይነት ባህርይ ስላላቸውና ስልጣንንም በሰላም አሳልፈው ስለሰጡ የክብር ዶክትሬት ይገባቸዋል ነው የሴኔቱ ውሳኔ::http://hornaffairs.com/…/sebhat-nega-honorary-doctorate-ax…/
እውነት ግን ስብሃት ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ነበሩን? የሰሩትስ ሥራ ለክብር ዶክትሬት ያበቃቸዋልን? በፍጹም:: እንደ እኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ መጠየቅ ከሚገባቸው ሰው አንዱ አሳቸው ናቸው:: 
ለምን? ለምክያቶቼ የምጠቅሰው የቀድሞ ህወሀት ኮማንደር የነበሩትን አረጋዊ በርሄን የዶክትሬት ቴሲስ ነው:: መጽሃፉን እዚህ ሊንክ ላይ ታገኙታላችሁ:: http://www.harep.org/Africa/7219.pdf
1. ትግራይን የመገንጠል እቅድ የስብሃት ነጋ ነበር
ተሀት( ተጋድሎ ሀርነት ትግራይም) ሆነ ሀወሀት ( ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት) ወደ በረሃ ሲወርዱ ( መጀመርያ) የነበራቸው ዓላማ " ትግራይን መገንጠል " የሚል አልነበረም:: ሁሉም በኢትዮጵያዊነታቸው ያምኑ የነበሩ እንደነበሩ ነገር ግን ስብሃት ነጋና መለስ ድርጅቱን ከተቀላቀሉ ጀምሮ ይሄ ነገር እንደመጣና የዚህም እብድ ሀሳብ ዋና አፍላቂ ስብሃት እንደነበሩ : አረጋዊ በርሄ በዶክትሬት ማሟያ ጽሁፋቸው እንዲህ ይገልጹታል
In June 1975 already, Sibhat had gone as far as characterizing the Tigraian demand for self-determination in the context of a ‘colonial question’, similar to that of the Eritreans.73 Together, they then proceeded to draft the Manifesto 68, and gave it to Seyoum to print in the Sudan. ( ገጽ 211)
ስብሃት ነጋ የትግራይ ጥያቄ የኮሎኒያል ጥያቄ ነው እስከማለት ደርሰው ነበር:: ይሄንንም የጻፈው የቀድሞው የድርጅቱ ኮማንደር መሆኑንን አይርሱ:: እንዴትም ይሄ ሀሳብ እንደተሳ እንዲህ ይተርኩታል ::
It was on one such occasion, while a group that included Asfaha, Yemane, Sibhat and Aregawi were ascending through the cliffs of Hirmi to go to Kelakil, that the aim of the Tigrai struggle was raised by Sibhat, in a joking manner. Known for his jokes, he propounded that it could be regarded as a ‘colonial question’, like that of the Eritreans. Some of them ridiculed Sibhat’s overture, asking ‘…where on earth are you going to cook up the history and politics to justify it’. All laughed but not Sibhat, who felt insulted. Nobody took what seemed to have come up in informal jest as a serious position. This was a mistake, for the same position would appear in different forms later during the struggle, and was to have a disruptive impact not only in the Tigraian movement for selfdetermination but also later in Ethiopian power politics in general.
2. ስብሃት ፍጹም ዲሞክራሲያዊም አልነበሩምም
ምንም እንኳን የአክሱም ሴኔት ለስብሃት የክብር ዲግሪ መስጠት ምክንያት የሆነው " ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ የስልጣን ሽግግር በማድረጋቸው " ቢልም - ይሄም ውሸት ነው:: አሁንም የቀድሞው የህወሀት ኮማንደር የነበሩትን የአረጋዊ የዶክትሬት ቴሲስ ልጥቀስ:: የስብሃትን ባህርይ እንዲህ ያስቀምጡታል
In the TPLF, Sibhat Nega and Meles Zenawi, without the consent of the leadership, took the lead in encouraging the fighters to take immediate measures against the TLF. They also accused the TPLF leadership of engaging the organization in a process of unity with bandits of the criminal type. They even coined a slogan that ran: ‘It is better to unite with Hawelti Aksum (i.e. the Aksum stelae, an inanimate object) than with such reactionaries’ ( ገጽ 100 )
እንኳን በዲሞክራሲያዊ ውይይት ሊያምኑ ቀርቶ ተመሳሳይ ዓላማ ይዘው ከወጡ ታጋዮች ጋር እንኳን መግባባት አቅቷቸው " ተሀት ( ተጋድሎ ሀርነት ትግራይ) ጋር አንድ ከመሆን ከአክሱም ድንጋይ ጋር አንድ መሆን ይሻላል" እስከማለት የደረሱ ሰው በምን ሂሳብ ነው ዲሞክራሲያዊ የሚባሉት:: ይህ ብቻ አይደለም ሀሳብን ማቻቻል አልችል ብለው ብዙ ሰውም እንደጨረሱ ዶክተር አርጋዊ እንዲህ ጽፈውታል::
3. ስብሃት ነጋ ብዙ ሰው ፈጅተዋል
ህወሀት ተሀትን አጥፍታ እንደገና ራሷ ታመሰች:: የውስጥ ክፍፍል ተነሳ:: ይሄንንም እንዲያጠኑና ውሳኔ እንዲሰጡ ሀላፊነት የተሰጣቸው ስብሃት ነበሩ:: ስብሃት እንደሚባለው በማሳመንና የተለየ ሀሳብን በዲሞክራሲያዊ መንገድ ከመፍታት ይልቅ ; እጅግ በጭካኔ ብዙ ሰው እንደጨረሱና እንዳስጨረሱ ዶክተር አረጋዊ አሁንም እንዲህ ገልጸውታል:: (ገጽ 141)
The hardest and most sensitive part of the Hinfishfish was the manner in which it was resolved. Although the entire membership of the leadership had a similar stand on the Hinfishfish, it was Sibhat Nega who was in charge of the investigation and the verdicts that followed. Those who were exposed in their units to be the main detractors were sent to prison. After months of interrogation, many others who did not wish to do so had a sad ending; regrettably they were killed for their dissent by people who claimed to fight the Dergue, an enemy of dissent. Only a handful of CC members who were stationed in the base areas knew about these harsh, irreversible measures
4. የኦርቶዶክስን ቤተ ክርስትያን የከፈሉት እሳቸው ናቸው
ስብሃት ነጋ በፖለቲካው ብቻ ሳይሆን በሃይማኖትም እጅግ የሚያስቆጣ ስራ የሰሩ ሰው ናቸው:: ገዳማት ውስጥ ካድሬ እየላኩ በሃሰት በማመንኮስና በኋላም ስልጣኝ ይዘው ቤተ ክርስትያን ውስጥ የፖለቲካ ስራ እንዲሰሩ ምልመላ : ስምሪትና ትዛዝ የሚሰጡት እሳቸው እንደነበሩ - አሁንም በግልጽ ተጽፏል:: ( ገጽ 302)ዓላማቸውም " ቤተ ክርስትያንን ማድከምና ማምከን " የሚል እንደነበረ ተጽፏል:: እንዲህ ይላል
This process involved the mobilization of parish priests and ordinary Christians to isolate them from the church’s national hierarchy. To weaken church authority, an intelligence group was formed under Sibhat Nega to infiltrate the well-established monasteries in Tigrai, such as Debre Damo, by planting TPLF members camouflaged as monks and influencing church activities in the interests of the TPLF.
አሁንም የሁለቱ ሲኖዶሶች እርቅ ላይ " እርቅ የሚለውን ቄስ መስቀል ነው" እስከማለት የደረሱ "ድንቅ" ፖለቲከኛ ናቸው:: http://andadirgen.blogspot.com/2013/03/blog-post_10.html…ያኔ ከብዙ ደጋፊዎቻቸው የተሰጠው መልስ " አቦይ ስብሃት ተሳስተዋል:: ግን የመንግስት አካል ስላይደሉ ተረጋጉ" አይነት ነበር:; ዛሬ ደግሞ ሁሉ ተረስቶ ክብር ይገባቸዋል:: ያውም ዶክትሬት ::
እርቅ የሚል ካህንን መስቀል ነው የሚል ሰውን ዴሞክራሲያዊ ማለት ፌዝ ነው ወይስ ቀልድ? ይደንቃል!
የስብሃት ቅድስና በቅድስቲቱ ከተማ
------------------------------------
የታቦተ ጽዮን ማረፊያ የሆነችው አክሱም ቅድስት ከተማ ናት:: ስብሃት ሊያደክሟትና ቅኝ ሊገዟት ስንት ሴራ ያሴሩባት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን - አክሱምን የምታየት እንደ ቅድስት ቦታ ነው:: አክሱም ለኦርቶዶክሳውያን ቅድስት ናት:: በዚህች የኦርቶዶክስ መዲና በሆነችው ከተማ : ቤተ ክርስትቲያኒቱን ሊያጠፋ ስንት ያሴረን ፖለቲከኛ :"የክብር" ዶክትሬት መስጠቱ ያስቃል::
ሲቪል ሰርቪስ ቢሆን ብዙም አልደነቅም ነበር:; ከቦታ ተመርጦ አክሱም መሆኑ ግን ውስጠ ወይራ ነው::
የአክሱም ዩንቨርስቲ ሴኔትን ትዝብት ውስጥ ይጥለዋል እንጂ ... ትልቅ ስም ይዞ እንዲህ ማሰብ ግን ያሳፍራል::


No comments: