Monday, July 25, 2016

በጎንደር አሁንም ውጥረቱ እንዳለ ነው

ወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጋር በተያያዘ በጎንደርና አካባቢው የተነሳውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ ውጥረቱ አሁንም እንዳለ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ትናንት እሁድ የተቃውሞ ሰልፍ ይደረጋል በሚል አንዳንድ እንቅስቃሴዎች የነበሩ ቢሆንም፣ የአካባቢው ባለስልጣናት እስከ ሃምሌ 25 ቀን ጊዜ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸው ታውቋል።
ህዝቡ የታሰሩ የኮሚቴው አባላት እንዲፈቱ እንዲሁም በማረሚያ ቤት ውስጥ የሚገኙትና የህዝባዊ አመጹ ማእከል የሆኑት / ደመቀ ዘውዴ እንዲፈቱ በተቃውሞ ሰልፍ ይጠይቃል።
የመንግስት ባለስልጣናት ህዝቡ ተቃውሞ ሰልፉን እንዳያደርግ እየተለማመጡ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰአት ደፍረው ሰልፉን ለመከልከል የማይችሉበት ሁኔታ በመፈጠሬ ሰልፉ ሊካሄድ እንደሚችል ነዋሪዎች እምነታቸውን ገልጸዋል።
የተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በጎንደር የታዬውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ ምን እርምጃ እንደሚወስዱ መቸገራቸውን ምንጮች ይገልጻሉ። / ደመቀ በትግራይ ክልል ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ የሚፈልጉት ህወሃቶች በአንድ በኩል፣ በአዲስ አበባ በፌደራል መንግስት ደረጃ እንዲታይ የሚፈልጉ ሃይሎች በሌላ በኩል እንዲሁም ጉዳዩ በአማራ ክልል እንዲታይና ኮሎኔሉን ከክልሉ ማስወጣት ሞት መጋበዝ ነው ብለው የሚከራከሩ ወገኖች ለውሳኔ ተቸገርው እንደሚገኙ ታውቋል።
በሌላ በኩል የትግራይ ክልል በወልቃይት ጠገዴ የአማራ መንነት የኮሚቴ አባላት ላይ ክስ መክፈታቸው ታውቋል።
ክሱ አቶ አሻግረው ገዛኸኝ ላቀው  አሊጋዝ አየለ አበበ ግዛቸው ደረሰ ኃይሉ  ሰሎሞን ግዛቴ እንየው  ኃይሉ አለማው ጸገዴ  አቶ ሰጠኝ ደረስ አድማሴ፣ ሰረበ ሙሉ መሰለ  ጀጃው በሪሁን መልኬ ሊላይ ብርሃኔ በየነ  ተክላይ ኃይሉ ግርማይ  እቁባይ /ስላሴ /ሚካኤል ብርሃኑ መርሻ ባየ እና ቄስ አዱኛ ዋሲሁን /እግዚአብሄር  ላይ የተከፈተ ነው።

ክሱተከሳሾች  ከወርሀ ታህሳስ 2008 ዓም ጀምሮ በዳንሻ ከተማ በተለያዩ ጊዚያት ቀድሞ የተመለሰውን የማንነት ጥያቄ አሁን ያለ በማስመሰልና ሕገ መንግሥታዊ የመብት ጥያቄ ሽፋን በማድረግ ሕገ መንግሥቱን በሚቃረን መልኩ የሕዝቡን አንድነት በሚያፈርስ አኳኋን፣ ሕዝቦች እርስበርስ እንዲጋጩ በማሰብ ሕጋዊ የሕዝብ ዉክልና ሳይኖራቸው፣ ከሕግ ዉጭ የማንነት ጥያቄ አለን፤ የወልቃይት ጠገዴ መሬት ተከዜ ምላሽ ነው፤ አሁን የቆምንበት መሬት የአማራ መሬት ነው፤ ለዚህም ለሕዝብ የማንከፍለው መስዋእትነት የለም እያሉ ከሕግ ዉጭ ሕዝብን እያደራጁ፣ የተለያዩ ቀስቃሽ ጽሑፎችን ፓምፍሌት፣ በጋዜጣ፣ በኮምፒተር ጽሑፍ እየበተኑ የቅስቀሳ ተግባር ሲፈጽሙ ቆይተዋል።ይላል።
9 ተከሳሽ እንደታፈነ አስመስለው ሕዝቡን ለአመጻ በማነሳሳት ከቀን 11/07/08ዓም እስከ ቀን 12/07/08 ዓም ሕገወጥ አመጽና አድማ በማስነሳትና በመምራት፣ ከዳንሻ ጸገዴ ጎንደር መገናኛ አስፋልት መንገድ በድንጋይ እንዲዘጋ፣ ከሁመራ ወደ ዳንሻ መናሀርያ የሚገቡ መኪኖች አስፋልት መንገዱ በድንጋይና በግንድ ዘግተው ሕዝቡ ለአመጽና አድማ እንዲነሳ ማድረጋቸውም በክሱ ላይ ሰፍሯል።

ሁለተኛውን ክስ ደግሞ1 እስከ 9 ያሉ ተከሳሾች የወንጀል ዓይነት የኢፈድሪ ወንጀል መቅጫ ሕግ አንቀጽ 321− 257// የተደነገገዉን በመተላለፍ መገፋፋትና ግዙፍ የሆነ የመሰናዳት ተግባር ወንጀል ወልቃይት ጠገዴ የትግራይ አካል ሳይሆን አማራ ነው፤ ትግሬዎች የምንፈልገው መሬታቹን እንጂ እናንተን አደለም እያሉን ነው። ወልቃይት ጸገዴ ቋንቋውን ባህሉን እንዳያሳድግ ተከልክሎሏል እያሉ ትክክለኛ ያልሆነና ጥላቻ የተሞላ የሕዝብ አቋም በሚያፈርስ መልኩ በተለያዩ ሕዝባዊ መድረኮች በመናገር ይንቀሳቀሱ ስለነበር በፈጸሙት ወንጀል ተከሰዋል።ይላል።
ሶስተኛው ክስ ደግሞማዛጋጃ ቤት በነበረውን የወጣቶች መልካም አስተዳደር ስብሰባ ይመራ ለነበረ ጠዓመ ለምለም የመልካም አስተዳደር ችግር አለብን፤ ስልጣን አልተሰጠንም፤ የእርሻ መሬትና የመኖሪያ መሬት አልተሰጠንም፤ ስለዚህ አንተ ልትመራን አትችልም ዉጣልን ብለው በማወክ ስብሰባው እንዲበተን በማድረግ በፈጸሙት ወንጀል ተከሰዋል።ይላል።
/ ደመቀንም ሆነ ሌሎች የኮሚቴውን አባላት ወደ ትግራይ ለመውሰድ አልታሰበም፣ የተላኩትም የፌደራል ፖሊስ አባላት ናቸውበሚል መግለጫ የሰጠ ቢሆንም፣ ክሱ በትግራይ ክልል መከፈቱ ገዢው ፓርቲ በቴሌቪዥን ከሰጠው መግለጫ ጋር ሙሉ በሙሉ የሚጣረስ ሆኗል። የኮሚቴው አባላት ክስ የተሰመረተባቸው ትግራይ ውስጥ መሆኑንና  ከፌደራል መንግስቱ ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር እንደሌለ የክሱ ሁኔታና በምስክርነት የቀረቡት የተከሳሾች ዝርዝር አድራሻ ያመለክታል።


No comments: