Sunday, July 31, 2016

በቃ እመኑ!

+25 ዓመት ስልጣን ላይ ተቀመጣችሁ፣ ኢትዮጵያን የምታክል ታላቅ ህዝብ ያላት ሀገር በድንግዝግዝ ዕይታ እና በቤተ-ሙከራነት ለመምራት ደፋ ቀና አላችሁ።
መለስ ከአቅሙ በላይ፣ ሁሉንም ስልጣን ልጠቅልል ብሎ 'ኤጎ አምቢሽን' ሀሳቡ አይሎ ሞት ጠቀለለው። ከእሱ ሞት በኋላም ቅጥ አምባሩ ጠፋባችሁ፤ እውቀት-አልባ ትምክህታችሁም አየለና 100% "ፓርላማ" ወንበር ጠቀለላችሁ።
በወቅቱ እጅግ አዝነን ተናደድን። ወራት ሳይቆይ በኦሮሚያ መዓት መጣባችሁ፤ የማታ ማታም እጅ ሰጣችሁ። በሀገሪቷ አራቱም አቅጣጫዎች ህዝባዊ ቁጣ ነደደ። ይኽው ዛሬ በጎንደር የኢትዮጵያ ህዝብ የአንድነት መንፈስ፣ በጨዋነትና በተግባር ደምቆ ታየ።
የዘንድሮ ህዝባዊ መዓት መግቢያና መውጪያ አሳጥቷችሁ አርዷችኋል፣ ዛሬ ፍርሃት እግራችሁ ስር ይገኛል!
በቃ እመኑ! ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ በሃሳብ ልቋችሁ ከሄደ ሰነበተ። እንደመዥገር የተጣበቃችሁበት ስልጣንም ይብቃችሁ፤ አጉል ድርቅናና ትምክህት ከህዝብ ሀይል አይበልጥምና። ከገባችሁ ዛሬ የማንቂያ ደወል ተደዉሎላችኋል። አሊያ፣ አምቢ ካላችሁም ህዝብ አይቀጡ ቅጣት በተግባር ይቀጣችኋል።
የዛሬ ገዥዎች ሆይ! ለዛሬዋ ኢትዮጵያ ዕድገትና ብልጽግና የምር ብቁ አይደላችሁም! እውነተኛ ነጻነት፣ ዴሞክራሲ፣ እኩልነት፣ ፍትህ ...እውነተኛ መሻቶቻችንን ናቸውና በሰላም ገለል በሉልን!
አትመጥኑንም፣ በቃችሁ!


No comments: