እምነቴን ከማስቀመጥ ልጀምር።
1. ሰዎች በብሔረሰባቸውም ሆነ በዘራቸው ምክንያት አድልዎ እና መገለል እንዳይደርስባቸው ጥብቅና እቆማለሁ፣
2. ማንም ኢትዮጵያዊ በሥላሴ አርአያና አምሳል የተፈጠረ ነውና ወንድሜ/እህቴ ነው ብዬ አምናለኹ፣
3. የትኛውንም ቋንቋ ይናገር ኢትዮጵያዊ ሁሉ እኩል ነው ብዬ አምናለኹ፣
4. ኢትዮጵያ የሁሉም ቋንቋ ተናጋሪዎች፣ የሁሉም እምነት ተከታዮች የጋራ ቤታቸው ናት ብዬ አምናለኹ፣
5. ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በፈለገው ክፍለ ሀገርና ክልል የመኖር፣ ንብረት የማፍራት፣ የመሸጥና የመለወጥ ኢትዮጵያዊ መብት አለው ብዬ አምናለኹ። ትግራይ የትግሬዎች ብቻ፣ አማራ የማሮች ብቻ፣ ኦሮሚያ የኦሮሞዎች ብቻ ናት ብዬ አላምንም፤
6. የሁላችን ቋንቋዎች ማደግና መዳበር እንዳለባቸው፣ በየአፍ መፍቻ ቋንቋችን ሳናፍርና ሳንፈራ ሳንሸማቀቅ መነጋገርና መግባባት እንዳለብን አምናለኹ፣
7. ከብሔረሰቦች መካከል የተለየ መብት የሚሰጠው ምርጥና የተለየ “ወርቅ ብሔረሰብ” መኖርን እቃወማለኹ፣
++++++
ይህን ካልኩ ዘንዳ ......

በጦርነት ውስጥ የመጀመሪያዋ ተጠቂ "እውነት ናት" የሚል የቆየና ክፍለ ዘመናትን የተሻገረ ጥንታዊ አባባል አለ። እንደምንመለከተው ከሆነ ደግሞ እውነት ሰለባ የምትሆንበት ሌላው ግንባር የዘር ፖለቲካ የሚባለው አመክንዮ እና እውነትን ፍለጋ የሌለበት የደመነፍስ ድጋፍና የደመነፍስ ተቃውሞ የተመላበት አደገኛ ጨዋታ ነው። አንድ ሰው ብሔረሰቡን ሊቀይር አይችልም። በብሔረሰብ የተቧደነ ፖለቲካ ሲመጣ ከብሔረሰቡ ውጪ እንዲሆን አይጠበቅም። ኅሊና፣ ርእዮት፣ ፍትሕ፣ አቋም የሚባሉትን ነገሮች በሙሉ ይህ የብሔረሰብ ቡድነኝነት ይደፈጥጣቸዋል። ስለዚህ ሰዎች በብሔረሰብ ይደግፋሉ በብሔረሰብ ተቧድነው ይቃወማሉ።
በዚህ ቡድነኛነት ዘመን እውነት ሰለባ ስለሆነች ስለ እውነት መከራከር በሁለቱም በኩል ተሸናፊ ያደርጋል። ቢሆንም ስለ እውነት ከመከራከር ውጪ ምን ምርጫ አለ?

1.
ከሰሞኑ እንዳየነው ሕወሐት የዘራው መርዘኛ የጎሳ ፖለቲካ ፍሬው ጎምርቷል።
2. በርግጥ የጎሳ ፖለቲካ ሁሉ መርዘኛ ነው ብዬ አላምንም፣ ሕወሐት በቲቪና ሬዲዮኑ ኮትኩቶ ያሳደገው ግን መርዘኛውን ነው። ለምግብ የሚውል እንጉዳይ አለ። መርዛማ በመሆኑ ከተመገቡት ወዲያው የሚገድል እንጉዳይ አለ። ልክ እንደዚያ።
3. የትግራይ ሕዝብ በሕወሐት መርዛማ ተግባር ምክንያት ሊጎዳ እንደሚችል ፍንጮች እየታዩ ነው። ሰዉ በየጓዳው የሚያወራውን "እነርሱ" እና "እኛ" የሚለውን ልዩነት እና በውስጡ ቀብሮ ያቆየውን ቂም መግለጽ እየጀመረ ይመስላል። ተጎጂ የሆኑት ሰዎች በርግጥ ጉዳቱ ሊደርስባቸው ይገባል ወይስ አይገባም የሚል የቃላት ስንጠቃ ወደ እውነቱ አያደርሰንም። በርግጥ ፖለቲካዊ ነጥብ ያስቆጥርልን ይችል ይሆናል። በሕወሐት ሰበብ ማንም የትግራይ ሰው ሊጎዳ አይገባውም። ለዚህ ጥብቅና መቆም ይገባናል። ነገር ግን ጉዳቱ ሊመጣ እንደሚችል ግን መዘንጋት አይገባም።
4. ስጋቴ ሁለት ነው። 1ኛ የሕወሐት ግፍ ያንገሸገሻቸው ሰዎች በስመ ትግሬ ሰላማዊውን እንዳይጎዱ ሲሆን ሁለተኛው ግን ሕወሐት ራሱ ሆን ብሎ የትግራይ ሰዎች ላይ ጉዳት በማድረስ "አማራው/ኦሮሞው ነው እንዲህ ያደረገህ" በሚል ሲቪል ጦርነት እንዳይቀሰቅስ ነው።
5. ለዚህ ደግሞ ምራቃቸውን የዋጡ የትግራይ ሰዎች ከተቀረው ኢትዮጵያዊ ጋር የይስሙላ ሳይሆን እውነተኛ ውይይት መጀመር አለባቸው። በተቃውሞ የተሰለፉ የትግራይ ሰዎች ኮሽ ባለ ቁጥር ሕወሐት ጉያ ውስጥ ከመሸጎጥ ድነው ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገናቸው ጋር መቆም አለባቸው። ለዚህ ደግሞ ሌላውን ኢትዮጵያዊም ሊያምኑት ይገባል። ሕወሐት ለትግራይ በጭራሽ ዋስትና ሊሆን አይችልም። ሕወሐት የሕወሐት ሰዎች እንጂ የትግራይ ሕዝብ ዋስትና አይደለም። እንዲያማ ከሆነ ትግራይ ሁሉ ሕወሐት ነው የሚለው የተሳሳተ ስሌት ውስጥ ይከተናል።
5. ከሰሞኑ እንደሰማነው በርግጥ የቀደሙ የኢትዮጵያ መንግሥታት እንኳን ሳይቀሩ ባላደረጉት ነገር ትግራይን ለማጥፋት እንደሞከሩ ሲተነተን ከርሟል። ጨፍጫፊ የሚባለው ደርግ እንኳን በጅምላ የትግራይን ሕዝብ አልጨፈጨፈም። መቀሌን ለቆ ከወጣ በኋላ በአውሮፕላን የጅምላ ጭፍጨፋ ማድረስ ይችል ነበር። አላደረገውም። ምንም ቢሆን ጦሩ የሕዝብ ልጅ እንጂ በዘር የተደራጀ የሰፈር ቡድን አልነበረም።
6. እውነተኛ ውይይት ያስፈልጋል ማለት በሕወሐት ምክንያት የደረሰውን አደጋ፣ የተጎዳውን ሕዝብ ከማወቅና ከመረዳት ይጀምራል። ላለፉት 25 ዓመታት የደረሰውን መከራና ስቃይ ከመረዳት ይጀምራል። የዚህ ሥርዓት ተጠቃሚው መላው የትግራይ ሕዝብ አለመሆኑን ብናውቅም ተጠቃሚ የሆኑት ግን ከትግራይ የመጡ ሕወሐቶች መሆናቸውን መገንዘብ ያስፈልጋል። አሁንም በድህነት ውስጥ ያሉትን ስፍር ቁጥር የሌላቸው የትግራይ ሰዎች በመመልከት ሌላው ኢትዮጵያዊ የሚያነሳውን ሐሳብ ማጣጣል ወደ ውይይቱና ስምምነቱ አያደርሰንም።
7. በሀገራችን ውስጥ "ኢኮኖሚክ ጄኖሳይድ/ economic genocide" (just my coined term)) ተፈጽሟል። ንብረት፡ ሀብትና መሬት ከሌላው ኢትዮጵያዊ ተነጥቆ ወደ ትግራይ ሰዎች እጅ ገብቷል። የመርካቶ ንግድ እና የሚያንቀሳቅሰው ሀብት የነበረው እንዳልነበረ ሆኗል። ከ6ሚሊዮን የትግራይ ሰዎች የዚህ ተጠቃሚው እጅግ በጣም ጥቂት ፐርሰንት ቢሆንም ተጠቃሚዎቹ በሙሉ ትግሬዎች መሆናቸውን መካድ እውነትን መካድ ነው። እውነትን ክዶ ወደ እውነት መድረስ አይቻልም።
8. የመረረም ቢሆን ግን ውይይቱን እንጀምር፡፡ ዘረኝነትን የምንጠየፍ በሙሉ እውነተኛ እና ግልፅ የሆነ ውይይት እናድርግ። ሕወሐት ከትግራይ ወገናችን ነጥሎ ሊያስቀረን መሆኑን እንገዘነብ። አንድ ወገን ነን። ያንን ወገንተኝነት እንዳናጣ ሁሌም ተጎጂ ከሆነችው እውነት ጎን እንቁም። ዘረኛ እንዳንባል ፈርተን ዋና ተጎጂዎች እንዳንሆን።

ኤፍሬም
No comments:
Post a Comment