ሐብታሙ አያሌው የሚባል ግለሰብን በአካል አላውቀውም። ስለ እሱ ብዙ የማውቀው ነገር የለም። ሆኖም ግን፣ ቢያንስ ስለ ሐብታሙ ሁለት ነገሮችን በእርግጠኝነት አውቃለሁ። 1ኛ፡- እሱም እንደ እኔ ሰው ነው፡- ሐብታሙና እኔ ሰብዓዊ ፍጡራን ነን። ሁለታችንም ጤናማ ሕይወት የመኖር ጉጉት፣ ታምሞ የመዳን ተስፋ አለን። እንደ ሰብዓዊ ፍጡር፣ እኔ ውስጥ ያለው የመኖር ጉጉትና ተስፋ በሐብታሙ ውስጥ እንዳለ ይሰማኛል። በእኔ ላይ እንዲሆን የማልፈልገውን ነገር በእሱ ላይ እንዲሆን አልሻም። 2ኛ) እሱም እንደ እኔ ኢትዮጲያዊ ነው፡- የአንድ ሀገር ዜጎች እንደመሆናችን ሁለታችንም እኩል እድል እንዳለን አምናለሁ። ለእኔ የተፈቀደው የሕክምና እድል ሐብታሙ ሊነፈገው አይገባም። ዛሬ እሱ የተነፈገው የመኖር ዕድል ነገ ላይ የሁላችንም ዕጣ-ፈንታ ይሆናል። ፈጣሪ እኩል የሰጠንን በሕይወት የመኖር መብት፣ ከእሱ ከሰጪው በስተቀር ማንም ሊነፍገን አይገባም። ስለዚህ፣ የሐብታሙ በሕይወት መኖር ተፈጥሯዊ መብት በመንግስት ፍቃድ ሲገደብ የሞት ጥላ በራሴ ላይ እንዳጠላ ይሰማኛል።
በእርግጥ መንግስት አስተዳደራዊ መዋቅር እንጂ ሰብዓዊ ፍጡር አይደለም። ነገር ግን፣ በመንግስታዊ መዋቅሩ ውስጥ በኃላፊነት የሚሰሩት ሰዎች ግን እንደ እኔና ሐብታሙ ሰብዓዊ ፍጥሯን ናቸው። እንደ እኛ ሰብዓዊነት የሚሰማቸው፣ በሕይወት የመኖር ጉጉትና ተስፋ ያላቸው የአንድ ሀገር ልጆች ነን። እነዚህ ሁሉ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ስለ ሐብታሙ መንግስትን የሚማፀኑት ኢትዮጲያዊያን ሰዎች ናቸው። አብዛኞቹ እንደ እኔ ሐብታሙን በአካል አያውቁትም። ነገር ግን፣ ሰብዓዊነትና ዜግነት በአንድነት ለጤንነቱ እንድናስብ አድርጎናል። ነገር ግን፣ የሀገራችን የመንግስት ባለስልጣናትም እንደ እኛ ሰዎች ናቸው፣ የአንድ ሀገር ዜጎች ነን። እንደ እኛ ለእሱ ጤንነት ባያስቡ፣ ባይጨነቁ፣…የእኛ ጩኸት እንዴት አይሰማቸውም? የእኛ ጭንቀት እንዴት አይታያቸውም። የሐብታሙ በሕይወት መኖር ጉጉት እንዴት አይሰማቸውም። የሚስቱና የልጆቹ ጭንቀት እንዴት በእነሱ በሚስቶቻቸውና በልጆቻቸው ፊት ላይ አይታያቸውም።
በዚህ ሁሉ ሰው ልማና ውስጥ የሚታየው ሰብዓዊነት በሀገራችን የመንግስት ባለስልጣናት ልቦና ውስጥ የለምን? በኢትዮጲያ ልጆችና ቤተሰቦች ፊት ላይ የሚታየው ሰብዓዊ ርህራሄ ከባለስልጣናቱ ልጆችና ቤተሰቦች ህሊና ተሟጥጦ አልቋል? እንግዲያውስ፣ እናንተ ሰብዓዊነት ሳይሰማችሁ ሲቀር እኛ ሰው መሆናችሁን እንጠረጥራለን። ዛሬ ለሐብታሙ አያሌው በሕይወት የመኖር ፍቃድ የነፈጋችሁ ባለስልጣናት፣ ነገ ሰብዓዊ ፍጡራን ነን ብትሉ የሚሰማችሁ ሰው እንደማኖር እወቁ። የሰው ልጅ በሕይወት የመኖር ተስፋ ሲጨልም ምንም ያልተሰማችሁ ስሜት አልባ ፍጡራን እንጂ ሰብዓዊ ፍጡራን አይደላችሁም። በእርግጥ ለሰው ልጅ ሕይወት ዋጋ የማይሰጥ ፍጡር ግዑዝ እንጂ ሰው አይባልም። የእኛ ሰብዓዊነት ካልታያችሁ፣ የእናንተ ሰውነት አይታየንም!!!

No comments:
Post a Comment