Tuesday, July 26, 2016

ፍ/ቤቱ ያለ ይግባኝ የራሱን ትእዛዝ ራሱ ሻረ፤ (ዳንዔል ሺበሽ)

Habtamu 34
ማክሰኞ ሐምሌ 19 ቀን 2008 ዓ.ም፡፡
በሐብታሙ ጉዳይ ላይ ለዛሬ ቀጠሮ ነበር ፤ በዛ መሰረት በሰዓቱ በቦታው የተገኙይ የሐብታሙ ቤተሰቦች እና ጓዶቹ ዛሬም መልስ ሳያገኙ ተመልሰዋል ።
የአቃቤ ህግን በቃል ይከራከራል በተባለው መሰረት ዛሬ ጉዳዩ ለመስማት ፍርድ ቤት ቢቀርብም ችሎቱ በጽሁፍ እንዲቀርብለት ለሐምሌ 22 ዳግመኛ ቀጠሮ ሳቷል።
የአቶ ሐብታሙ በቶሎ ወደ ውጭ ሄዶ አስፈላጊው ህክምና ካላገኘ በሸታው ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንደሚያደርሰው ዶክተሩ የፃፈለት እና ፍርድ ቤቱ በጠየቀው መሰረት የሆስፒታሉ ቦርድ (3 ዶክተሮች ) የፈረሙበት ወረቀት ቢቀርብም ጉዳዩ ምንም ተስፋ ወደሌለው ወደ ዳግም ቀጠሮ መዘዋወሩ አገዛዙ አቶ ሐብታሙ ላይ የሞት ፍርድ እንደፈረደበት እና ቀኑን እየቆጠረለት መሆኑን መቀበል ግድ እየሆነብን መቷል !!
የሰርዓቱ አባላት እና ደጋፊዎች ለሽርሽር እና ለገበያ በዓለም ይዞራሉ ፤ ሃገር ደበረን ብለው ለ2 ሳምንት ከሃገር ይወጣሉ፤ ለተለያየ ህክምና ከመንግስት ድጋፍ በማግኘት ወደ ውጭ እየሄዱ ይታከማሉ ። አቶ ሐብታሙ በህመም እየተሰቃየ ህክምና እንኳን ማግኘት አልቻለም ።
አቶ ሐብታሙ አልሰረቀም ፤ ሰው አልገደለም ፤ ሀገር አልሸጠም ፤ አቶ ሐብታሙ ግብ አንድ ትልቅ ጥፋት አጥፍቷል ። ሐገሬን ፤ ወገኔን ፤ ነፃነቴን ብሏል ። ይህ የሀገር እና የወገን ልክፍት ደግሞ ዛሬ ላለበት ደረጃ ዳርጎታል ።
አቶ ሐብታሙ ለዚህ እየከፈለ ላለው መስዕዋትነት የኢትዮጵያ ህዝብ ውለታውን በምን ይመልስለታል ? ዛሬ ከሐብታሙ ጎን ቆመን ህይወቱን ካላዳንን ፤ ዛሬ የ4 ዓመቷን የህፃን አሜንዳን አባት ካላዳንላት እኛስ በታሪክ ተጠያቂ አንሆንም ? መቼ ነው ግን ለኛ ነፃነት ብለው በየእስር ቤቱ እና በየሆስፒታሉ ለሚማቅቁት ወገኖቻችን በሚሊዮን ከጎናቸው ቆመን የምንታየው ? እኛስ ድርሻችን ምንድነው !!
በበኩሌ ወያኔ በአቶ ሐብታሙን እንዲሞት መፈለጉን ዛሬ አረጋግጫለሁ ! ዳኛ ዳኜ መላኩም ህሊናቸውን ሸጠው በዚህ ጉዳይ ላይ ድርሻቸውን እየተወጡ ነው ከማለት ወደኋላ አልልም ! ከዛሬ ጀምሮ ሌላ አማራጭ ካለ መፈለግ ነው እንጂ በ22 ለሚንነው ምንም አልጠብቅም ።

No comments: