Saturday, July 2, 2016

ዘላለማዊ ክብርን አጥቶና ዉርደትን ታቅፎ ከመኖር መሞት ይሻላል

በአዲስ አበባ ከተማና አካባቢው ዜጎችን ከቤት ንብረታቸው የማፈናቀል ድርጊት
ዜጎች ለረጅም ዓመታት በይዞታነት ግብር ሲከፍሉበት ከቆዩበት ቦታህገወጥ ናችሁብሎ ማፈናቀል ምን እሚሉት ድርጊት ነው
በሃገር ሉአላዊነት ላይ ድርድር በማያዉቅ ህብረተሰብ ዉስጥ እየኖሩ እንደዚህ አይነት አሳፋሪ እና ከአንድ ሰብአዊ ፍጡር የማይጠበቅ ድርጊት መፈፀሙ በግልፅ የሚያሳየዉ ገዥ ነኝ የሚለዉን ፓርቲ ባዶ ቀፎነት ነዉ። ይህ በመደረጉ የኢትዮጽያ ነፃነት እንዲሁ ተገፎ ይቀራል ብሎ ማሰብም አይቻልም። እነ አፄ ምንሊክ ከአዲስ አበባ በፈረስ አድዋ ድረስ መጥተዉ በጣሊያን ዘመናዊ ወራሪ ላይ ዘምተዉ ነፃነቷን ያስከበሩላትን ሃገር ወያኔ እግሩን ዘርግቶ ካቲካላ እየጠጣ ነፃነቷን ሊነፈጋት አይችልም። በርግጥ ብዙ ንፁሃን ሃገር ወዳድ ዜጎች ይንገላታሉ፣ ይደበደባሉ፣ ይሰቃያሉ፣ ወዘተ። ይሁን እንጅ ዘላለማዊ ክብርን አጥቶና ዉርደትን ታቅፎ ከመኖር ይህ ምርጫ ይሻላል።
ዜጎቻችን በየአቅጣጫዉ ከሃገር ዉስጥም ከሃገር ዉጭም ምን እየተደረጉ እንዳሉ እንኳን ለኢትዮጽያዊያን ለአለም ህዝብም ስዉር ሚስጥር መሆኑ ከቀረ ዉሎ አድሯል። እዉነታዉ ይህ ሆኖ እያለ ገዥዉ ቡድን በግዳጅ እኔን ምረጡ በማለት የሃገሪቱን ሃብትና ንብረት ያለአግባብ ዜጎችን ለማፈን፣ ለማሰቃየት፣ ለመከፋፈል፣ የሚያዉለዉ ሃገሪቱ ሰዉ ስለሌላት ሳይሆን ከጫካ በወጣ አስተሳሰቡ ህዝብን ባፈሙዝ በማስፈራራትና እንቢ ካለም በመግደል የወረራ አድማሱን ለማስፋትና ለማቆየት በማሰብ ነዉ። በዚህ ዘመን እንድህ አይነት አስተሳሰብ በሃገራችን ላይ
ሰፍኖ በመገኘቱ ልናዝን ይገባል እንጅ ትግላችን ለደቂቃም ቢሆን ሊገታ አይችልም፣ ሌላ ምርጫም የለንም። ስለዚህ ለነፃነት ስትሉ በዚሁ ቡድን ታስራችሁ እየተሰቃያችሁ ያላችሁ ዉድ ኢትዮጽያዊያን እግዚያብሄር የአዳምና የሄዋንን ዘር ለማዳን ሲል በአደባባይ በመስቀል እንደተቸነከረ ሁሉ እናንተም ለሃገራችሁ ነፃነት ስትሉ እየተሰቃያችሁ እንዳላችሁ ይገባኛል። ኢግዚያብሄር ከእናንተ ጋር ይሁን። ሊነጋ ሲል ይጨልማል እንደተባለዉ ሃገራችን በአሁኑ ስአት ጨለማ ዉስጥ እንዳለች ሁሉም ያዉቃል። ምንአልባት ሊነጋ ቢሆንስ?
ኢትዮጽያ ለዘላለም ትኑር።

No comments: