Wednesday, July 13, 2016

የመብት ጥያቄ ያነሱ ንጹሀን ዜጎችን አሸባሪ ብሎ ታርጋ በመለጠፍ ከመግደል ወደኋላ የማይል ቡድን እንዴት መንግስት ሊባል ይችላል?

ወያኔዎች ሌላ ጨዋታ ቀይሩ አሁን ህዝቡ ነቅቷል። በኦሮሚያ ዉስጥ የቀመሳችሁትን ሽንፈት በአማራውና በሌላውም ብሄር ይደገማል።

ወያኔ የቀድሞውን መንግስት ዲሞክራሲያዊ ባለመሆኑ አፋኝና ጨፍጫፊ ነው ብሎ እንደሚኮንን ይታወቃል ግን ዲሞክራሲያዊ መንግስት ነኝ ያለው ወያኔ ዛሬ ላይ የሚነሱበትን የመብትና የነፃነት ጥያቄዎችን በዲሞክራሲያዊ መንገድ ጥያቄዎቻቸውን ከመመለስ ይልቅ ለቅዋሜያቸው የተለያየ ስም በመስጠት በሀይል ስለምን የመብት ጥያቄዎችን መቀልበስ አስፈለገው?እስከመቼስ እዚም እዚያም የሚነሱበትን አይነተ ብዙ የመብትና የነፃነት ጥያቄዎችን በጉልበት መመለስ ይቻለው ይሆን?መንግስትና ህዝብ እጅና ጓንት ከመሆን ይልቅ አይጥና ድመት እየሆኑ ምን አይነት ኢትዮጵያ ትሆን ወደወፊት የምናየው?መንግስት እንደ መንደር ጎረምሳ ነገሮችን ሁሉ በሀይል ምፍታትን ብቸኛ መፍትሄ አርጎ ከሚያይ ይልቅ ወይም እኔ የምላችሁን ስሙ ከሚል ግትረኛ አቋም ወጥቶ ስህተቴ የቱ ነው ብሎ እራሱን መፈተሽ ስለምን ተሳነው? ሳይቃጠል በቅጠል ነውና ኢህአዴግ እራሱን የሚያይበት ውስጡን በአግባቡ የሚያይበት ትክክለኛ ጊዜ አብቅቶለታል፡፡
ከደርግ የማይማር የደንቆሮ እና ሆዳም ስብስብ ወያኔ ባንተ የሚሸወድ ሞኝ የለም። ጊዜው ያለፈበት ቀልድህን ትተህ ለነፃነት ፈላጊው ህዝብ ሥልጣንህን አስረክነህ በሰላም ብትኖር ይሻልሀል። በሁሉም ቦታ ጉድጓድህ ተዘጋጅቶልሀል።

አሁን ወያኔ አፋኝነት ተባኖበታል። ሕዝብን ያሸነፈ ድሮም የለም፣ ዛሬም የለም፣ ወደፊትም አይኖርም። የሰላም ባስ ቃጠሎ በኦሮሚያ ክልልሉ በአማራ ተደግሟል። ገና ይቀጥላል። በሙስና ያሰባሰባች ሁት ንብረት ሕዝቡ ያወቀዋል። አሸባሪው ማን እንደሆነ ሕዝብ ያውቃል። 99% አሸነፍን ያላችሁት ሽፍንፍፍን ዓመት ሳይሞላው ታይቷል። ትልልቆቹን ብሄሮች ጨፍልቃችሁ መግዛት አይቻልም። ሞት ለወያኔ!!!!

No comments: