Tuesday, October 20, 2015

ለየትኛው "ኣባይ"…?

ለ900ሺ ኣስቸኳይ እርዳታ የሚያስፈልገው ህዝብ የእርዳታ እህል የጫኑ መኪኖች ሰሙኑን መቐለ ከተማ ደርሰዋል።
ኣንድ ሚልዮን ለሚጠጋ ተረጂ እስከ 350 መኪኖች እህል ጭነው በቀጥታ ከጅቡቲ ትግራይ ገብተዋል።
መንግስት እንዳለው የጫኑት ኢትዮጵያ ውስጥ የተመረተ ሳይሆን ከውጭ በእርዳታ የገባ መሆኑ ጭነው የመጡት ሹፌሮች ኣውግተውኛል።
" ድርቁ በቁጥጥር ስር ኣውለነዋል " የሚል የትግራይ መንግስት መግልጫ ተደጋግሞ እየተሰማ ባለበት ቅፅበት " ለእርዳታ የመጣው እህል እየተሸጠ ነው " የሚል ወሬ በስፋት እየተሰማ ነው።
እህሉ መቐለ ከተማ ወደሚገኙ የዱቄት ፋብሪካዎች እየተሸጠ መሆኑና ጥያቄ ላነሱ ሹፌሮች ደግሞ " ድርቁ በቀላሉ ስለተቆጣጠርነው ትርፉ ተሽጦ ለኣባይ እንዲሆን ተወስነዋል " ተብሎዋል።
ከኔጋ ሁኖ ጨዋታው ሲያዳምጥ የነበረው ወጣት " … የትኛው ኣባይ ነው? ኣባይ ግድብ፣ ኣባይ ወልዱ፣ ዉይስ ኣባይ ፀሃዬ…" ብሎ ጠይቋል።
የትግራይ ገዢዎች ድርቁም እህሉም በቁጥጥራቸው ስር የዋሉ ይመስላሉ… ¡¡¡¡
ድርቅ ካጠቃው፣ ሂወቱ በኣደጋ ውስጥ ከገባ፣ሂወቱ ለማቆየት የጎረሳት ማቆያምግብ ከጉሮሮው የሚቀሙ ሌቦች እንጠብቀው።
ኤፍ ኤም ፋና ትግርኛ ፕሮግራም ምስጋና ይድረሳቸውና ትንሽ ብትሆንም የድርቁ ሰለባ ወገኖች ድምፅ ኣሰምተውናል።
" ወጣቱ ስደት ከመሄድ ትንሽ ተረጋግቶ ነበር። ኣሁን በድርቁ ምክንያት ፈርሶ ባህር እየገባ ነው……… ተማሪዎች በዚህ ሁኔታ መማር ኣንችልም ብለው ቤት እየዋሉ ነው… ከ8 ሺ በላይ የቀበሌያችን ከብቶች በምግብና ውሃ እጦት ክፉኛ ተደርቀውብናል… መንግስት ተሎ ሊደርስልን ይገባል … " ብለው ሲናገሩ ሰምተናል።
ሬድዮ ፋና የኢህኣዴግ ሚድያ መሆኑ እነ Senait, Fetsum,Sabawi ላስታውሳቹህ እፈልጋለው።
በዚህ ጥረታችን የሰው ሂወት እንጂ የፖለቲካ ትርፍ ማግኘት እንደማንፈልግም ደግሜ ላረጋግጥላቹ እወዳለው።

Amdom Gebreslasie

No comments: