Friday, October 9, 2015

አቶ አለነ ማህፀንቱ ለጥቅምት 8 ተቀጠረ

አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም በተጠራው ሰልፍ ሰበብ የታሰረው የቀድሞው አንድነት የማህበራዊ ጉዳይ ኃላፊ አቶ አለነ ማህፀንቱ ዛሬ መስከረም 28/2008 ዓ.ም አራዳ ፍርድ ቤት 6ኛ ወንጀል ችሎት ቀርቦ ለጥቅምት 8/2008 ዓ.ም ተቀጥሮበታል፡፡
አቶ አለነ ለዛሬ የተቀጠረው መከላከያ ምስክሮችን ለማሰማት ቢሆንም አቃቤ ህግ የለም በሚል የመከላከያ ምስክሮቹን ሳያሰማ ቀርቷል፡፡ የአቶ አለነ ጠበቃ ደንበኛቸው ለብይን ለብዙ ጊዜ የተቀጠረና ታስሮ የሚገኝ በመሆኑ አቃቤ ህግ በሌለበት ምስክሮቹ እንዲሰሙላቸው ቢጠይቁም ፍርድ ቤቱ ሳይፈቅድ ቀርቷል፡፡
አቶ አለነ ማህፀንቱ በተመሳሳይ ክስ በሌላ ፍርድ ቤት እንዲለቀቅ ተወስኖለት እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ የዋስትና መብት ተፈቅዶለት የነበር ቢሆንም በይግባኝ እንደታገደበትም ጠበቃው ገልጸዋል፡፡ አቶ አለነ ማህፀንቱ በሚቀጥለው ቀጠሮ አቶ በላይ ፈቃዱን፣ አቶ ተክሌ በቀለን፣ አቶ ስዩም መንገሻን እና አቶ አስራት አብርሃምን በመከላከያ ምስክርነት እንደሚያቀርብ ይጠበቃል፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ

No comments: