Tuesday, October 27, 2015

ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ በሕይወት ይኑሩ አይኑሩ ማረጋገጫ ሊገኝ አልቻለም::



ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የሚወጡ ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት ከካሳንቺሱ የደህንነት ምድር ቤት ከሚገኘው እስር ቤት ወደ ደብረዘይት አየር ሃይል እስር ቤት በሌላ ጊዜ በአሮጌው አይሮፕላን ማረፊያ የማሰቃያ ምድር ቤት ወደ ተለያዩ ቦታዎች ሲያንገላቱት ቆይተው በስተመጨረሻ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት አምጥተውት ከነብሰ ገዳዮች ጋር ያሰሩት እና በእንግሊዝ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች እና በአባቱ የተጎበኘው የነጻነት ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ በሕይወት ይኑር አይኑር ማረጋገጫ የለም ሲሉ ለደህንነት ቢሮ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለዲፕሎማቶች ተናግረዋል::
በወያኔ የማወዛገብ ፖለቲካ ልምዱ ያላቸው የለውጥ ሃይሎች ምናልባት ወያኔ የሃሰት ዜናዎችን በመንዛት የታወቀ ስለሆነ ዲፕሎማቶቹን እና የለውጥ ታጋዮችን ለማሳሳት የፈጠረው ዜና ነው ቢሉም ታጋይ አንዳርጋቸው ከቃሊቲ እስር ቤት በለሊት መወሰዱ እና መመለሱን ከሁለት ሳምንት በፊት ጉዳዩን አይተናል ያሉ ምንጮች ተናግረው ነበር::ሆኖም ከነብሰ ገዳዮች ጋር ያሰሩት ለነብሰ ገዳዮች የሰጡት የግድያ ተልእኮ አስፈጽመውበት እንዳይሆን ያሰጋል የሚሉ ቢኖሩን እስካሁን ግን በሕይወት ይኑር አይኑር አልታወቀም የሚሉ መረጃዎች በርክተዋል::ላለፉት አራት ሳምንታት አንዳርጋቸውን ለመጠየቅ የፈለጉ ዲፕሎማቶችም እንዳልተፈቀደላቸው ምንጮቹ ይናገራሉ::ወያኔ የተቃዋሚዎችን ፕሮፓጋንዳ ለማሳጣት እና በሕዝብ ትዝብት ውስጥ ከቶ አዲስ ዶክመንተሪ ለመስራት ያቀደው እንዳይሆን የሚሉት አስተያየት ሰጪዎች ሁኔታውን በትእግስት መጠበቅ ይሻላል ሲሉ ይናገራሉ::በአንዳርጋቸው ሞቷል የሚል ዜና የማህበራዊ ድህረገጾች በውስጥ መስመር ተወጥረው በገሃድ ሊፈነዱ ደርሰዋል::ለሁሉም በትእግስት መጠበቅ ነው::
Source: mereja

No comments: