አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ለየመንግስት ባለስልጣናት ሹመት ሰጡ ቢሉ ''ከየት አምጥተው'' ብሎ የሚጠይቅ አይጠፋም። ጥያቄው ተገቢ ነው... እውነት ከየት አምጠተው ነው ሹመት የሚሰጡት ለራሳቸው የተሳናቸው ሆነው ለሌሎች ሹመት የሚሰጡ እንዴት ያሉ ሰው ናቸው፤ በርግጥም ከሌላቸው ላይ የሚሰጡ እነርሱ ተዓምረኞች ናቸው ብለን ከማድነቅ ወደኋላ አንልም።
አቶ ጌታቸው የኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ሆኑ...
ብቻ አቶ ሬድዋን ሁሴን እንኳንም ከፊታችን ገለል አሉልን... እንዲህ የምልበት በቂ ምክንያት አለኝ በተለይ በየ መግለጫዎቹ ሲናገሩ ቃላት በቃላት ላይ እየደራረቡ በ ዩዜን ቦልት ፍጥነት ሲያወሩ አንድም ቀን የአውራምባ ታይምስ ካሜራ እንጂ ማንም ሰው በቅጡ የማይዘው እና የማይረዳው 'ቅም' የሚል ነገር ሲናገሩ ሰምቻቸው ስለማላውቅ ገለል በማለታቸው ደስታዬ ትልቅ ነው። አሁን የተመደቡበት ወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስቴርነት ስለሆነ አይደለም በንግግር በቁምጣም ቢሮጡ እንደ ፍጥርጥራቸው፤
አቶ ጌታቸው ወደ አደባባዩ ስልጣን መምጣታቸውን ስናይ ኢህአዴግ ቤት አንድ እንኳ ሰው ፊት የሚቀርብ ሰው መጥፋቱን እንደናይ አድርጎናል ባይ ነኝ... እኒህ ሰውዬ ቢያንስ በቅርቡ በሁለት እና ሶስት ንግግሮች ተፈትነው ወድቀዋል።
በባለፈው 'የምርጫ'' ክርክር ጊዜ
ሀ...
እኛ ውሃ እየተጠማን ለጅቡቲ ውሃ እንዴት ትሰጣላችሁ.... ተብለው ከተቃዋሚዎች ጥያቄ ተነስቶ ''ለጅቡቲ ወሃ ለምን ተሰጠ ብሎ መጠየቅ ተራ ምቀኝነት ነው'' ብለው እንደ ኢትዮጵያዊ ሳይሆን እንደ አንድ ጁቡቲያዊ (ለዛውም ጀዝባ የሚባል አይነት ጅቡቲያዊ) ሆነው መልሰዋል።
ለ...
ኢህአዴግ ለሱዳን ለሱዳን መሬት ሰጥታለች በባደመ ጉዳይ ላይም ቁማር ተጫውታለች እንዴት እንዲህ ይደረጋል ተብለው ሲጠየቁ.... ''ለቁርጥርጥራጭ መሬት ስንል አንጨቃጨቅም'' አይነት መልስ ሰጥተው አስቀውናልም አሳቀውናልም።
ሐ...
በሀሰብ ጉዳይ ላይ ሲወያዩ ''ጀግናው ኮነሬል መንግስቱ ያልቻለውን እኛ ልናስመልስ አንችልም'' ሲሉ መንግስቱን አወድሰው የገዛ ፓርቲያቸውን አንኳሰዋል... (ይቺ እንኳ ግምገማ ላይም ሳትነሳባቸው አትቀርም)
ታድያ እኒህ ሰውዬ እንዴት ነው መንግስትን ከህዝቡ ኮሚኒኬት ሊያደርጉ ያሰቡት...
ይብላኝ ለራሳቸው እና ለድርጅታቸው እንጂ እኛማ እንኳን እርሳቸውን አቶ ሬድዋንንም ችለን ኖረናል እና... ''ና በለው.... ና!'' ብለን በወኔ እንቀበላቸዋለን... ዋናዎቹ መጥተው እስኪገላግሉን ደረስ!
No comments:
Post a Comment