አሁን እማወራው ስለ ብርቱው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሳይሆን ስለ ሆደ ባሻዋና ሩህ ሩህዋ እናታችን ነው!!
ከእንቅልፌ ስነሳ ከንጋቱ 12 ሰዓት አልሞላም 70 ዓመት ያለፋት እናታችን የተመስገንን ነገር አሳለፋ ለሰጠችው ቅዱስ ሜካኤል የልጄን ነገር አደራ ልትል ሄዳለች፡፡ እናታችን ተመስገን ከታሰረበት ቀን ጅምሮ በብዙ እጥፍ አርጅታለች ነገሮቿ ሁሉ እህህ ነው መተኛት አቁማለች ሸለብ አደርጓት በነቃች ቁጥር አይ ልጄ እንዴት ሆኖ ይሆን ትላላች እንባ ባቀረዘዙ አይኖቿ እራስጌዋ ላይ የተሰቀሉትን የመድሃኔዓለም እና የቅዱስ ሚካኤል ምስል እየተመለከትች ልጄስ ማለት ከጀመረች ዛሬ 14 ቀኗ ነው ፡፡ ከንጋቱ 12፡45 ሆኗል እናቴ መታለች ነጠላዋን ሳታወልቅ ማታ ሳትተኛ ለተመስገን የሚሄድን ስንቅ የሰራችውን ለማሞቅ እየቀነሰች ነው በመሀል ተመሰገን ፣ አቢዮት .. አንተ ትንሽ ልጅ አለች እናታችን አንዳችንን ለመጥራት የሁላችንም ስም መጥራት ልምዷ ነው መብራት የለም መስልኝ እስቶቩ እንቢ አለኝ አለችኝ፡፡ ቀና ስል መብራት አለ ተነስቼ ሄድኩኝ እስቶቩን አልሰካቸውም ሰሞኑን ከቀልቧ ስላልሆነች አንደዚህ አይነት ነገር እየተደጋገመ ነው፡፡ ከምግቡ ጋር ለተመሰገን የሚሄድ ቡና ለማፍላት ጀበናዋን አንደኛው ምድጃ ላይ እየጣደች ነው ..አሳዘነችኝ.. መሄድ ያለበትን ነገሮች ካስተካካለች በኋላ ነገ ምን እንደሚፈልግ ጠይቁት በመስማማት ራሴን ነቀነኩ ነጠላዋን እያስተካከለች ዛሬ እስጢፋኖስ ይነግሳሉ መኪና ስለማላገኝ አሁን ነው እምሄደው የሱን ነገር እንዳወክ ንግረኝ እዛው ሆኜ እጠብቃለሁ አለችኝ አሰብኩት ከጀሞ እስከ አቢዬት አደባባይ ድረስ እንዴት እንደምትሄድ አብሬሽ ልሄድ ወይ አይሆንም አንተ እሱ ጋር ሂድና እሚሉትን ትነገረኛለህ ለመውጣት ስትዘጋጅ እሺ እነደማትለኝ ባውቅም ቀጠሮው እኮ ገና ከሰዓት ነው ታቦት አውጥተሽ ቤት ብተመለሺ ጥሩ ነው ምሳ በልተሽ አረፍ ትያለሽ የሱን ነገር ሳልሰማ አንዴት እበላለሁ ብላ አየችኝ አንገቴን ደፋው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል ይከተልህ በልልኝ እንዳቀረቀርኩ የድምጿን መለወጥ ስሰማ ቀና ብዬ አየኋት እናቴ እያለቀሰች ነው! ምን ላድርጋት ምንስ ብላት ትፅናናለች እንባዬ መጣ አንዳታየኝ ፊቴን አዙሬ እነግረዋለሁ አልከኝ እናቴ ስትሄድ ይሰማኛል ሁል ጊዜ ቤተክርስቲያን ስትሄድ እምታስረው ነጭ ሻሽ ወንበር ላይ ተቀምጧል ሻሽ አለማሰሯን ልብ አለማለቴ ገርሞኝ ሻሹን ይዤ ስወጣ ለሀዘን ጊዜ ብቻ ካልሆነ የማታስረውን ጥቁር ሻሽ አስራ አንግቷን ደፍታ እየሄደች ሳያት አይኔ ዳር ደርሶ የነበረው አንባዬ ወረደ፡፡ አሁን ከቀኑ 9፡05 ነው ተመስገን ላይ አንባገነኖቹ 3 አመት ከፈረዱበት 5 ደቂቃ አልፏል ለናቴ ምን ብዬ ነው እምነግራት ከጠዋት ጀምሮ ቤተክርስቲያን ተቀምጣ እየጠበቀችኝ ነው ምግብ ከበላች አንድ ቀን አልፏታል ፡፡ አውቃለሁ ተሜ ከቤተሰቡ በላይ ሀገሩን እንደሚያስቀድም! አውቃለሁ ተሜ ብርቱ እንደሆነ! አውቃለሁ ተሜ ጉዞው ቀራኒዬ ድረስ አንደ ሆነ! አውቃለሁ ተሜ ድምፅ ለተነፈጉ ሰዎች ድምፅ እነደሆነ! አውቃለሁ ተሜ የዚህ ትውልድ ወካይ እንደሆነ!፡፡ ታዲያ በስተርጅና ላይ ለምትገኘው እናታችን ይሄን አንዴት ነው እማስረዳት እናታቸን ልጄ ይመጣል እያለች በተስፋ እየጠበቀች ነው….. አሳሪዎቹ ሆይ መጦሪያዋን ለነጠቃቹሀት እርጅናዋን በመከራ ለለወጣቹሁባት ተስፋዋን ላጨለመቹሁባት እናታችን ምን ብዬ አንደምንግራት ትነግሩኛላቹ !? ምስኪኗ እናታችን ሆይ ልጅሽ ለሚወዳት ሀገሩ ሲል መክፈል ያለበትን ነገር እየከፈለ ነው! አትዋሽ ላመንክብት ነገር ሙት ብለሽ ያሳደግሽው ልጅሽ ያልሽውን ነው ያደረገው!፡፡ እናታችን ሆይ በርችልን … አሁን ይሄን ልነግርሽ እየመጣሁ ነውና…
No comments:
Post a Comment