ጥቅምት 5/2008 አራቱ የዞን ዘጠኝ አባላት በነፃ እንዲለቀቁ ሲወሰን፣ በወንጀለኛ መቅጫ ህግ 257/ሀ እንዲከላከል የተባለው በፍቃዱ ሀይሉ በ20 ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲለቀቅ ተወሰነ፡፡ ጦማሪና ጋዜጠኛ በፍቃዱ ሀይሉ ጥቅምት 5/2008 ዓ.ም ለልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት የዋስትና መብቱ እንዲከበርለት ጠይቆ በነበረው መሰረት ለዛሬ ጥቅምት 10/2008 ዓ.ም የዋስትናውን ጉዳይ ለማየት ቀጠሮ የሰጠው የልደታ ፍርድ ቤት በ20 ሺህ ብር ዋስ ወጥቶ ጉዳዩን በውጭ ሆኖ እንዲከታተል ወስኗል፡፡
ጥቅምት 5/2008 ዓ.ም አራቱ የዞን ዘጠኝ አባላት መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዲሰናበቱ በተወሰነበት ወቅት ክሱ ከሽብርተኝነት ወጥቶ በማስረጃነት የቀረቡበት ፅሁፎች አመፅ ቀስቃሽ ናቸው በሚል በወንጀለኛ መቅጫ ህግ 257/ሀ እንዲከላከል የተወሰነበት በፍቃዱ ሀይሉ መከላከያ ምስክሮቹን እንዲያሰማ ለህዳር 27/2008 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቶታል፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ
No comments:
Post a Comment