ሰማያዊ ፓርቲ ከትራንስፎርሜሽን ረቅቅ ዕቅድ በፊት ለመሰረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ቅድሚያ ተሰጥቶ ውይይት እንዲደረግ ጠየቀ፡፡ መንግስት መስከረም 28 እና 29/2008 ዓ.ም በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱ ላይ ለመወያየት ከሀገር አቀፍ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ከጠራው የእቅድ ውይይት ላይ እንደማይገኝም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በፃፈው ደብዳቤ ገልፆአል፡፡ ፓርቲው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በፃፈው ደብዳቤም የብዙሃን ፓርቲ ዴሞክራሲ፣ የሰብአዊ መብት አያያዝ፣ የነፃ መገናኛ ብዙሃንና ሲቪክ ማህበራት ከእቅዱ በፊት ቅድሚያ ሊሰጣቸው እንደሚገባ ጠቁሟል፡፡
በእቅዱ ዝርዝር ከመወያየት በፊትም በኢትዮጵያ አንድነትና ብሄራዊ መግባባት አስፈላጊነትና አፈፃፀሙን በተመለከተ ቅድሚያ ሰጥቶ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር መወያየትና መፍትሄ መፈለግ ለኢትዮጵያ ሰላም፣ ዕድገትና ልማት አስፈላጊ መሆኑን ፓርቲው እንደሚምን ገልጾአል፡፡
በመሆኑም ፓርቲው መሰረታዊ ጉዳዮች መፍትሄ ባልተበጀላቸው ሁኔታ በዕቅድ ዝርዝር የአፈፃፀም ሁኔታ ላይ መወያየት ለኢትዮጵያ የሚመኘውን ዕድገትና ብልፅግና ያመጣል ብሎ እንደማምን እና ከትራንስፎርሜሽን እቅዱ ውይይት በፊት መሰረታዊ ጥያቄዎች መፍትሄ እንዲያገኙና የውይይት ቅድሚያ እንዲሰጣቸው ጠይቋል፡፡
መንግስት መስከረም 28ና 29/2008 ዓ.ም በትራንስፎርሜሽን እቅዱ ላይ ውይይት ለማድረግ በኢ.ሲ.ኤ አዳራሽ ሀገራዊ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን የጋበዘ ሲሆን ሰማያዊ ፓርቲ 20 አባላቱን በውይይት እንዲያሳትፍ በደብዳቤ ተጠይቋል፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ
No comments:
Post a Comment