
በጣም አሣዛኙ ጉዳይ በወያነ መርማሪዎች ድብደባ እየደረሠበት ያለውን ሠይፈ አዘነ ጉዳይ ስለሠብዓዊ መብት ጥሠት ያገባናል የሚሉ ኢትዮጵያዊያን ዝምታ ነው በተለይም ሻለቃ አክሊሉ መዘነ የኢትዮጵያ አየር ሃይልን ከድቶ ግንቦት 7ን ሲቀላቀል ከፍተኛ መነጋገሪያ እንዲፈጠር አድረገው የነበሩት የግንቦት 7 አመራሮች ለጉዳዩ ትኩረት አለመስጠትን ለተመለከተ ሠው በጣም የሚያሣዝን ነው ይህንን ስል በሠይፈ ላይ እየደረሠ ያለው ጉዳይ የተለየ ሆኖ ለሠይፈ ብቻ እንጩህ ማለቴ ሳይሆን ቢያንስ ወንድሙ ግንቦት 7ን ስለተቀላቀለ በገዢው ፓርቲ ደህንነቶች በቤተሠቡ ላይ እየደረሠበት ያለውን ጉዳይ ለመላው የሐገራችን ህዝብ እናሳውቅ በሚል ነው፡፡ ይህ ጉዳይ ምንአልባት ነገ ግንቦት 7ን ለመቀላቀል ላሠቡ ግለሠብ ፍራች ይፈጥራል የሚል ከሠብዓዊነት በታች የወረደ ፖለቲካዊ አስተሳሰብ ያለው ሠው ካለ በጣም የሚያሳፍር የወረደ አስተሳሰብ ይመስለኛል፡፡
ፍትህ ለኢትዮጵያዊያን
ፍትህ ለሻለቃ አክሊሉ መዘነ ቤተሠቦች
#ሁኔአቢሲኒያ
No comments:
Post a Comment