Friday, March 6, 2015

በደህንነት ቢሮ ለሊቱን ያጋመሰ ግምገማ መካሄዱ ተሰማ:: አለመተማመኑ እና ክፍተቱ እየሰፋ መምጣቱን በገሃድ ያሳየ ግምገማ መሆኑ ታውቋል::

በደህንነት ቢሮ ለሊቱን ያጋመሰ ግምገማ መካሄዱ ተሰማ::
አለመተማመኑ እና ክፍተቱ እየሰፋ መምጣቱን በገሃድ ያሳየ ግምገማ መሆኑ ታውቋል:: Minilik Salsawi
የሕወሓት የደህንነት አባላት በተለየ ሁኔታ አዳማጭ የሆኑበት ትላንትና የተጀመረው በአዲስ አበባ ውስጥ የተሰማሩ የፌዴራሉ ደህንነት አባላት ግምገማ እጅግ በተካረረ እሰጥ አገባ ለሊቱ አጋማሽ ድረስ ቢደረግም በማጉረምረም እና ባለመስማማት መበተኑ ታውቋል::በአንድ ብሄር የበላይነት የተከሄደው እና በተያያዘ የአንድን ብሄር በተለየ ሁኔታ ያልነካው ይህ ግምገማ በገዛ አገራችን እንደ እንጀራ ልጅ እና እንደ ባይታዋራ ነገሩን ሁሉ በሌሎች ላይ ለምን ይላከካል የሚል ጥያቄ አስነስቷል::
መገምገም ካለበት ትእዛዝ ከሚሰጡ የበላይ ሃላፊዎች ጀምሮ ነው እንጂ ሁሉም እኩል የሰራውን ስራ የትግራይ ተወላጆችን ለይቶ አስቀምጦ አዳምጭ አድርጎ እኛን ለይታችሁ የምትገመግሙበት ምክንያቱ ምንድነው? ሁላችንም አንድ የጋራ ስራ እስከሰራን ድረስ በጋራ ልንገመገም ይገባል ግደሉ ስንባል ገለናል ዝረፉ ስንባል ዘርፈናል ተካፈሉ ስንባል ተካፍለናል::ይህንንም ስራ የትግራይ ተወላጆች አብረውን ፈጽመዋል::ብሄር የለየ እና ያማከለ ግምገማ የዜግነት መብታችንን ይጋፋል እንዴት እንዲህ እንቀጥላለን::ሁሉም በጋራ ሊገመገም ይገባል::አንዱን የቤት ልጅ ሌላውን የጎዳና ዱርዬ አድርጎ መገምገሙ ለምን አስፈለገ የሚሉ አስተያየቶች የተደመጡ ሲሆን:ሃላፊዎቻችን በቡድን በቡድን አደራጅተው በግል ትእዛዝ መንግስታዊ ያልሆኑ ስራዎችን መስራታችን እየታወቀ ከነሱ በወረደ ትእዛዝ ለሰራነው ስራ ልንጠየቅም ሆን ልንገመገም አይገባም ሲሉ ተደምጠዋል::በየክልሉ እየተገደሉ የሚጣሉ ግለሰቦችንም ኖን የሚዘረፉ ንብረቶችን የሚጠየቁ ገንዘቦችን አስመልክቶ ሃላፊዎቻችን ወርደው ሊገመገሙ ሲገባ እንዲሁም በማናለብኝነት ለሚፈጸሙ ወንጀሎች የሕወሓት የደህንነት አባላት መጠየቅ ሲገባቸው እነሱን ከዚህ ሁሉ ድርጊቶች አግለሎ እኛን መኮነኑ የማያዋጣ የግምገማ ሂደት ስለሆነ ሊታረም ይገባል ሲሉ ተገምጋሚዎቹ በአንድ ድምጽ ተናግረዋል::
በግምገማው ላይ ከተነሱት ጉዳዮች ሌላው ትግሪኛ ተናጋሪ ደህንነቶችን በአዲስ አበባ ዙሪያ ማእረግ እና ሃላፊነት በመስጠት በፖሊስ ሰራዊት እና በመከላከያ ቢሮ ውስጥ ሲመደቡ የሌላው ብሄር ተወላጆች ወደ በረሃ በመወርወር በተዘዋዋሪ እየበደሉ እነ በክትትል እያሰቃዩ እስከ ሞት የደረሱ እንዳሉ የተጠቀሰ ሲሆን ይህ ጉዳይ ሊታይ ይገባዋል::መልቀቂያ የጠየቁ የደህንነት አባላት የሚጠብቃቸው እስር መሆኑን እያየን ነው:: የተሰደዱ አባላት በርካቶች ናቸው::የመንግስትን ይሁን የፓርቲ መረጃ የሚሸጡት የሕወሓት አባላት የሆኑ ደህንነቶች መሆናቸው ይታወቃል:; እነሱን አትንኩብን ማለት ነገ ለሚፈጠረው ችግር ተተያቂው ማነው? በሚል ጉዳይ ዙሪይ ጥያቄዎች ቢነሱም በማያረኩ ምላሾች ጉዳዮቹ ሳይገመገሙ አልፈዋል::ለሊት አጋማሽ ድረስ የዘለቀው ግምገማ ቀጣይ ሁኔታዎች ተጠንተው ድጋሚ ሌላ ግምገማ ይጠራል በሚል የበላይ ሃላፊዎች የተረጋጋ አንደበት ስብሰባው መዘጋቱን ምንጮቹ የገለጹ ሲሆን በደህንነት ክፍሉ ውስጥ አለመተማመኑ እና ክፍተት እየሰፋ መምጣቱን የስርአቱን መበስበስ ያመለክታል

No comments: