በደቡብ ክልል በየም ወረዳ የሚገኙ የፍርድ ቤትና የ‹ፀጥታ› አባላት ሰራተኞች የደኢህዴን አባላት መሆናቸውን ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ የላኳቸው ሰነዶች አጋለጡ፡፡ በወረዳው ፍርድ ቤቶች ከጥበቃና ፅዳት ሰራተኞች ጀምሮ እስከ አቃቤ ህጎች የደኢህዴን አባላት መሆናቸውን የ‹‹መንግስት ሰራተኛ አባላት ንኡስ ኦርኔል›› ላይ የሰፈረው የሰራተኞቹ መረጃ ያመለክታል፡፡
በተመሳሳይ በክልሉ የ‹ፀጥታ አካላትም›› የደኢህዴን አባላት እንደሆኑ መረጃው ያመለከተ ሲሆን የፀጥታ አስተዳደርና ሚሊሻዎች የድርጅት አባል መሆናቸውን ደኢህዴን የመንግስት ሰራተኞችን አባልነት የሚያስሞላበት ቅጽ ያሳያል፡፡
የፍርድ ቤት ሰራተኞቹ እና የ‹ፀጥታ አካላት›› ከ1987 ዓ.ም ጀምሮ 2005 ዓ.ም ድረስ የደኢህዴን አባል በሆኑበት ቅፅ የ‹‹ቢ እና ሲ›› የአባልነት ደረጃን እንደተሰጣቸው በሰነዱ ላይ ሰፍሯል፡፡
No comments:
Post a Comment