Monday, March 30, 2015

አይ ወያኔ ድንቄም ለወጥ አምጪ

 ሆድን በጎመን ቢደልሉት ጉልበት በዳገት ይለግም ይባላል የሀገሬ ሰው ሲተርት መቼም ነገርን ነገር አይደል የሚያነሳው ለዚህ ገፅ አንባቢዎች በሙሉ የከበረ ሰላምታዬን አቀርባለሁ ከላይ ያነሳሁትን አባባል እንዳነሳ ያደረገኝ አንድ ሌላ ጥሩ የማውቀው አንድ የራሴ ታሪክ ላጫውታቹና ወደዋናው ሀሳቤ ልግባ ፡፡

የማውቃትን የቅርብ የአክስቴን ልጅ የቤት ስራዋን ለሰው ታሰራና እራሷ እንደሰራች አድርጋ ለእናቷ ታሳይ ነበር እናቷም በልጇ ጉብዝና እየተመካች ለጎረቤትና ለዘመድ በኩራት ትናገር ነበር እየቆየች ግን እውነት መውጣት ትጀምርና ትንሿ የአክስቴ ልጅ ጉብዝናው የእሷ አለመሆኑ እናቷን ያጠራጥራት ጀመር እነቷም ይህን ለማረጋገጥ የራሷን ዘዴ መጠቀም ትጀምርና ልጄ የኔ ፍቅር አሁን የምገዛልሽን ስጦታ የምገዛው አሁን እኔ የምሰጥሽን የቤት ስራ አጠገቤ ቁጭ ብለሽ ስትሰሪ ብቻ ነው ትላታለች ልጅም ብልጣብልጥ ነበረችና ማም እስከዛሬ የገዛሽልኝ ስጦታ ከቤት ስራ በ%Eላ ነበር የአሁኑ ግን ቅድሚያ ቢሆንስ በማለት እናቷን ፈትናታለች እናም አክስቴ ልጇን አጥፊነት ወይም እራሷን አታላይ መሆን ሳይሆን የልጇን ብልጠት እንዳችበት የማስታውሰው ታሪክ ነው፡፡

መቼም የእናትና የልጅ ታሪክ ሆነ እንጂ በእኛ ወይም በእኛ ዙሪያ እንዲህ ያለ ታሪክ ዙሪያችን ቢኖር እንመለከተው ይሆን?

ትላንት ለውጥ ፈላጊ ሆነው በሀገራችን ላይ የራሳቸው በሆነ መሬት ላይ የእናንተ ዲሞክራሲና መብት ተብለው ለውጥ ፍለጋ መንግስት አለን ብለው የብሶታቸውን ድምፅ ሊገልፁ ባሉ ወጣቶች ላይ የራሳችን መንግስት የምንለው ወንድሞቻችን ላይ የማስደንገጥ ወይም ሰልፍ የማባረር ሙከራ ሳይሆን ሆን ተብሎ ግንባር ግንባራቸው ላይ እንደጠላት በየመንገዱ የተደፉት ወንድሞቻችን እንዲሁም የቦንብ መጥረጊያ የሆኑ ወንድና ሴት ወገኖቻችን ታሪክ ለማዳፈን ወያኔ ዛሬ የሚያደርገው ማለባበስ ምን ይባል ይሆን? የኢትዮጵያ ህዝብ በዘርና በሀይማኖት ለያይቶ የራሱን ዕርዮት አለም ካልተቀበለ በዚህች ሀገር መብት የሌለው ስንቱ ይሆን ወገኔ ዘመን አልፎ ዘመን ሲተካ ሁሉም የራሱ የሆነ ነገር ይዞ የሚመጣው ነገር ይኖራል ወያኔ ግን ዙፋኑ ላይ እንደተቀመጠ ከነበረው ስርዓት ብዙም የተለየ ነገር አልነበረውም የአንዱ ጎሳ የበላይነት ነጣጥሎ የመግዛት ስርዓት ሲጠቀም ቆይቶ ዛሬ እንደ ህፃን ልጅ የኢትዮጵያን ህዝብ ለመደለል የራሱ ርዕት አለም አቀንቃኝ የሆኑትን ሰዎች ይበልጥ ሀብታም በማድረግ ኢኮኖሚ አሳደኩ እያለ በአዲስ አበባ ቋንቋ እንደሚባለው ፉገራ ወይም ሆድን በጎመን እንደመደለል ያለ ጨዋታ ብዙ አያዋጣም፡፡ ቻይናን በገፍ አስገብቶ የፉገራ ቴክኖሎጂ የሀገርን ህዝብ ያታልለዋል ባይታለልም አማራጭ የለውም፡፡ የቻይና ሸቀጥ ማራገፊያ አንተ የሰጠህው ድምፅ ብልጫ ሳይሆን እኔ የማወጣው መርህ ግብር ይገዛሀል ተብሎ የፓርቲ አባል ካልሆንክ ኢትዮጵያዊነትህ ብቻውን ትርጉም የለውም ተብሎ አፈና እና ብዝበዛ ችሎ ያለው ህዝባችን እንደዛች ትንሽ ለልጅ ያለ ብልጠት ከዚህ ፉገራ ነፃ ያወጣው ይሆን ወይስ ሁሌ ታሪክና እውነትን የሚፈርድ የኢትዮጵያ አምላክ ሁሉን አዲስ አድጎ በብሔር ማንነት ሳይሆን በኢትዮጵያዊነት የሚኮራበት ኢትዮጵያዊ ስለሆነ ብቻ የሀገሩ መንግስት ዘብ የሚቆምለት ጊዜ ይመጣ ይሆን?

ያለፈ ታሪክ ያለፈ ቢሆንም ዛሬ የሚደረገው ነገር
ካለፈው ካልተማረ ይቅር እንበለው እንዳንል ዛሬም ያኑኑ የአንባገነንነቱንና እኔ ብቻ አዋቂ ነኝ ባይነቱን አገዛዝ እያስከፋው ይታያል እናም በዚህና በዚያ መደለሉ ቀርቶ ለሀገር እድገት የሚሻለውን አዳዲስ ሀሳብ ከአዲስ ሰው ለአዲስ ትውልድ በመቀበል ያረጀና እጅጅ ያለውን የወያኔ አገዛዝ ለመቀየር ወገን እንነሳ፡፡

ክብር ለኢትዮጵያ

ምንትዋብ

ጎህ መፅሔት

No comments: