ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብትን ሊገድብ ይችላል የተባለ መመሪያወጣ
September 26 /2013
ከቅርብ ወራት ወዲህ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የአደባባይ የተቃውሞ ሰልፍ መጥራት መጀመራቸውን ተከትሎ በኢትዮጽያ ሕገመንግስት አንቀጽ 30 መሰረት የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትና አቤቱታ የማቅረብ መብትን ሊገድብ ይችላል የተባለ አዲስ መመሪያ የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ማውጣቱ ተሰማ። አዲሱ መመሪያ ሰላማዊ ሰልፍ የማይደረግባቸው አካባቢዎችንና ጊዜያትን ለይቶ ያስቀምጣል።
በዚሁ መሠረት በሃይማኖት ተቋማት፣ ሰፊ ህዝብ በሚገበያይባቸው የገበያ ቦታዎችና ህብረተሰቡ በብዛትና በስፋት በሚንቀሳቅስባቸው የስራ ቀናት እንዲሁም በስራ መግቢያና መውጫ ስዓታት ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ እንደማይፈቀድ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አካላት ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ህገ መንግስቱ ላይ የሰፈሩትንና ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግናበመሰብሰብ መብት ላይ ያተኮሩትን ሀሳቦች በዝርዘር ማየቱ አስፈላጊ በመሆኑ፤ ህገ መንግስቱን በአግባቡለመተግበር የሚያስችል መመሪያ ማዘጋጀቱን ገልጿል።
በውስጡም ህጉን በዝርዝር ለማስፈፀም የሚያስችሉ መመሪያዎችን ያካተተ ነው ተብሏል።
ሰላማዊ ሰልፉን የጠራው አካል ያሉበትን ሃላፊነቶችና የፀጥታ አካላትን ሚና ምን እንደሆነ በዝርዝር ያስቀመጠ መሆኑ ታውቋል።
የመመሪያው ተልዕኮ በህገ መንግስቱ አንቀፅ 30 ላይ የተቀመጠውን ድንጋጌ ማስፈፀምእንደመሆኑ ሁሉም ዜጋ በቅርቡ እንዲያውቅ ይደረጋል ብለዋል።
በዚሁ አንቀፅ ንዑስ ቁጥር 1 ላይ የሰፈረው ድንጋጌ ደግሞ ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋርበመሆን መሳሪያ ሳይዝ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ እንዳለበት ያስቀምጣል።
የሰላማዊ ሰልፍና የፖለቲካ ስብሰባ አዋጅ
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ይህ መመሪያ መውጣቱን ከአዲስአበባ ፖሊስ መረጃ ካገኘ በኋላ የፖሊስ ከፍተኛ አመራሮችንና የአዲስአበባ አስተዳደር ኃላፊዎችን በጉዳዩ ላይ ለማነጋገር ሞክሮ እንዳልተሳካለት በይፋ መግለጹን በተለይ በግሉ መገናኛ ብዙሃን መዘገቡ ይታወሳል። የፓርቲው አመራሮች መመሪያ የወጣው የተቃዋሚዎችን በተደጋጋሚ ሰልፍ ለመውጣት የመጀመሩትን ጥረት ለማፈን ነው ማለታቸው ይታወሳል።
በጉዳዩ ላይ አስተያየት የጠየቅናቸው አንዳንድ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች መመሪያ ወጥቷል መባሉን ከመስማት ውጪ ኮፒው ስላልደረሳቸው አስተያየት ለመስጠት እንደሚቸገሩ ተናግረዋል። ሆኖም በአንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ያነበቡትና የሰሙት ዓይነት መመሪያ ወጥቶ ከሆነ ሕገመንግስታዊ መብትን የሚገድብ መሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም ብለዋል።
|
No comments:
Post a Comment