ደሴ በጎዳና ላይ ጽሁፎች (ግራፊቲ) አሸብርቃ አደረች!
ሰኞ ነሐሴ 27/2005
አውራ ጎዳናዎች ዋነኛ ትኩረት ነበሩ!
የደሴ ከተማ በጎዳና ላይ (ግራፊቲ) መፈክሮች ደምቃ አደረች፡፡ በደቡብ ወሎ ዞን
በምትገኘዋ የደሴ ከተማ ሌሊቱን ተጽፈፈወ ባደሩ የተለያዩ መብትን የሚጠይቁ
መፈክሮች ተጽፈውባት አድራለች፡፡ ድምጻችን ይሰማ፣ መሪዎቻችን ይፈቱ፣
መንግስታዊ ሽብር ይቁም የሚሉና መሰል ይዘት ያላቸው መፈክሮች የታዩ ሲሆን
የመንግስት መስሪያ ቤት አጥሮችና አውራ ጎዳናዎች ዋነኛ ትኩረት ነበሩ፡፡ በነጭ
ቀለምና በስፕሬይ በመጠቀም በትላልቁ የተጻፉት መልእክቶች የበርካታ የከተማዋን
ነዋሪ ቀልብ ስበው ውለዋል፡፡ ግራፊቲዎቹ ከንጋት በኋላ የከተማው አስተዳደር
ካድሬዎችን በማሰማራት በሌላ ቀለም ሲያስጠፉ መዋሉ ተዘግቧል፡፡
የግራፊቲ ስራ ተቃውሞን ይገልጻሉ ተብለው ከሚታሰቡ ሰላማዊ የትግል ስልቶች
አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከዚህ ቀደም መሰል ጭብጥ የያዙ የግራፊቲ ጽሁፎች
በአዲስ አበባ የተለያ አካባቢዎች በተለይም በካዛንቺስ፣ 22፣ መገናኛ፣ ጦር ሀይሎች
እና ኮልፌ አካባቢዎች የተሰሩ ሲሆን በክልል ደረጃም በሻሸመኔ፣ በጅማ፣ በአዳማና
በደብረዘይት ከተሞች መሰራታቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፡፡ መሰል አይነት
ጭብጥ ያላቸው የጎዳና ላይ ጽሁፎች በሌሎች ክክሎችና ከተሞች በስፋት ይቀጥላሉ
ተብሎ ይጠበቃል፡፡
አላሁ አክበር!
No comments:
Post a Comment