በደሴ ከተማ በሼህ ኑሩ ግድያ በተያያዘ በማዕከላዊ እስር ቤት በስቃይ ላይ የሚገኙት ሙስሊሞች ለመስከረም 25 ተቀጠሩ::
በደሴ ከተማ በሼህ ኑሩ ግድያ በተያያዘ በማዕከላዊ እስር ቤት በስቃይ ላይ የሚገኙት ሙስሊሞች ለመስከረም 25 ተቀጠሩ::
በታላቁ የረመዳን ወር የመጀመሪያ ቀናቶች ውስጥ በደሴ ከተማ ሼህ ኑሩ የተባሉ መንግስትታዊውን እስልምና አራማጅ በመሆናቸው የሚነገርላቸውን ግለሰብ በመንግስት መገደላቸው ይታወሳል፡፡
ይህንንም ግድያተከትሎ በርካታ ወጣቶች በፌድራል ፖሊሶች እና በደህንነቶች ተይዘው ወደ አዲስ አበባው የሰው ልጅ ኢ ሰብአዊ ድርጊት ወደሚፈፀምበት ማዕከላዊ እስር ቤት ተወርውረዋል፡፤ በማዕከላዊ የምርመራ ቆይታቸውም እጅግ ዘግናኝ የሆኑ ድብደባዎችን እና ስቃዬችን ማስተናገዳቸው የሚታወስ ነው፡፡ ለረጅም ጊዜያት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ እና ቤተሰብ እንዳያገኛቸው ከተደረገ ቡሃላ ለጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት በማቅረብ በሽብርተኛነት ስልተጠረጠሩ በህጉ መሰረት የ28 ቀን የምርመራ ጊዜ ፖሊስ ጠይቆ ለጳጉሜ 2 ተቀጥረው ነበር፡፡
በሽብርተኛነት የተጠረጠሩት ሙስሊሞች በሼህ ኑሩ ግድያ ጋር ተጠርጥራቹሃል ተብለው የታሰሩ ቢሆንም 3ቱን ሙስሊሚች ብቻ በወንጀሉ የተከሰሱ ሲሆን የተቀሩት ግን በደሴ ከተማ ሲካሄድ የነበረውን ተቃወሞ ስታስተባብሩ ነበር በማለት መከሰሳቸው ተሰምቷል፡፤ ከታሳሪዎቹ መካከል ሁለት ሙስሊሞች እስካሁን በምን ጉዳይ እንደታሰሩ እንኳን እንዳልተገለጸላቸው ምንጮች አስታውቀዋል፡፡
በቀነ ቀጠሯቸው መሰረት ለሁለተኛ ጊዜ ጳጉሜ 2 ልደታ ፍረድ ቤት ቀርበው የነበረ ሲሆን ፖሊስ ተጨማሪ 28 ቀን ቀነ ቀጠሮ ለፍርድ ቤቱ በመጠየቁ ለመስከረም 25 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰቷቸው ወደማሳቃው ማዕከላዊ መመለሳቸውን ምንጮች ዘግበዋል፡፤
ታሳሪዎቹን ከቤተሰባቸው አንድ ሰው ብቻ በአስራ አምስት ቀን አንድ ጊዜ ብቻ እንዲጠይቃቸው የተደረገ ሲሆን በሌላው ጊዜያቶች ውስጥ ግን ምግብ እና ልብስ ብቻ ማቀበል እንደሚችሉ ተገልፆል::
አላህ ይድረስላቸው!!!
ብርታቱን እና ፅናቱን ይስጣቸው!!!
ድል ለኢትዬጲያ ለሙስሊም!!!
No comments:
Post a Comment