ሰማያዊና አንድነት ፓርቲዎች የጠሩዋቸውን ሰልፎች ተከትሎ መንግስት የጎዳና
ላይ ነጋዴዎችን መበተን ጀመረ
መስከረም ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ሁለቱ ፓርቲዎች
የጠሩዋቸውን ሰልፎች ተከትሎ በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የሚገኘው መንግስት
በዛሬው እለት በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የሚገኙ ሊስትሮዎችን፣ በጎዳናዎች
ላይ እቃዎችን የሚሸጡትን በጸጥታ ሀይሎቹ አማካኝነት እንዲሰበሰቡና ወደ
አልታወቀ ስፍራ እየወሰዱዋቸው ነው።
የሚታፈሱት ሰዎች ወዴት እንደሚወስዱ ባይታወቅም ከአንዳንድ ሰዎች ባገኘነው
መረጃ ሰዎቹ ፓርቲዎቹ ያዘጋጁት ሰልፍ እሲከጠናቀቅ ታግተው ይቆያሉ።
ሰማያዊ ፓርቲ በመጪው እሁድ የሚያደርገው የተቃውሞ ሰልፍ በተያዘለት መረሀ
ግብር መሰረት እንደሚካሄድ ፓርቲው ማስታወቁ ይታወሳል። አንድነት ፓርቲም
እንዲሁ መስከረም 17 የተቃውሞ ሰልፉን ያደርጋል።

No comments:
Post a Comment