ፕሬዝደንት ግርማ ወ/ግዮርጊስ በወር 400,000 ብር የሚከፈልበት የመኖሪያ
ጉድ በል ጎንደር!!!! ፕሬዝደንት ግርማ ወ/ግዮርጊስ በወር 400,000 ብር የሚከፈልበት የመኖሪያ ቤት ውል እንደተፈራረሙ ሰማን። በሀይሌ ገ/ስላሴ ጎዳና ከአክሱም ሆቴል ጀርባ የሚገኝ የመዋኛ ገንዳ ጨምሮ ባለ ሁለት ፎቅ ህንፃ የሆነ ነው::
ህንፃው ለፕሬዘዳንቱ ከመተላለፉ በፊት ዳን ቴክኖክራፍት በተባለ ድርጅት 1.6 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ሊፍት እየተገጠመለት ነው፡:
ሀገሪቱ በድህነት በርሀብ በችግር ህዝቡም በኑሮ ውድነት መላወሻ አጥቶ እየተንገላታ እነሱ ይህን ያህል ብር በየወሩ ለቤት ኪራይ?መሪዎቻች ለምን የደሀ ሀገር መሪዎች እንደሆኑ ይረሳሉ :: እስቲ ስለእውነት እንነጋገር ስንት ዜጎች ጎዳና ላይ? ስንት ጠዋሪ ያጡ አረጋውያን? ስንት ወላጅ አልባ ህፃናት? ስንቱ በህመም የአልጋ ቁራኛ? ሆኖ በሚኖሩባት ሀገር ይታያችሁ በወር 400.000 አራት መቶ ሺ ብር፤፤በወር 400,000 በአመት 4.8 ሚሊየን ብር በ10 አመት "የሚኖሩ ከሆነ"480 ሚሊየን ብር ማለት ነዉ።ስንት ስራአጥ ወጣቶችን ሂወት ይቀይራል ? ስንት የህክምና ተቋም ይሰራል? በ እኔ እምነት የኢትዮጵያን ህዝብ ከመናቅና ምን ያመጣል ከሚል ስሜት የመጣ ነው::አረ እባካችሁ ለተቸገሩት እንዘንላቸው፡፡
ጸረ ሙስና ኮሚሽን ስራው ምንድን ነው የፕሬዘደንቱ የገንዘብ ምንጭ ምንድ ነው :: ለህዝብ ሊገለጽ ይገባል::
ዘሪቸስት.ኮም (www.therichest.com) በ2013 ባወጣው የሀብታም ፕሬዝደንቶች ስም ዝርዝር ውስጥ የኛ ፕሬዝደንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ በ 1.5 ሚሊዮን ዶላር ከአለም ሶስተኛ ፕሬዝደንት እንደሆኑ አስነብብዋላ:: በቀን አንዴ እንኳን ጠግቦ ለመብላት ያልታደለውን ህዝብ ከግምት ውስጥ ያላስገባ የተጋነነ ወጪ ፡፡ከአንድ ሀገር መሪ (ርእሰብሄር) ትልቅ ሰው ያማይጠበቅ አሳፋሪ ተግባር ነው፡:
ንጉስ ክፍሌ::
No comments:
Post a Comment