Thursday, September 12, 2013

ሰበር ዜና

የመንግስት የደህንነት ሃይሎች ከተለያየ ቦታ በጥቆማ እና ተከታትሎ በመያዝ ያሰሩዋቸውን ሙስሊሞች በማስገደድ በፌስቡክ የስለላ ስራ እያሰሩዋቸው እንደሚገኙ ተጋለጠ:;
ከተለያዩ ቦታዎች በመንግስት የደህንነት ሃይሎች ታፍነው የታሰሩ ሙስሊሞችን በከፍተኛ ደረጃ ድብደባ በመፈጸም የፌስቡክ አድራሻቸውን በመቀበል በፌስቡክ ጥሩ የሚንቀሳቀሱ ልጆችን ምንም እንዳልተፈጠረ ነገር አስመስለው በማናገር መረጃ እንዲያቀብሉዋቸው እና አንዲሰልሉላቸው እያደረጉ መሆኑ ተረጋግቷጧል፡፡

በፌስቡክ ላይ እና በአካል የሚያውቋቸውን ሰዎች ተደብቀው እንደሚገኙ በመንገር መረጃ አንዲሰበስቡ እያደረጉ ይገኛሉ፡፤ከሁሉም የከፋው ግን በሰላማዊ ትግሉ ላይ ጥሩ አስተዋፅኦ እያበረከቱ የሚገኙ ወንድሞችን እና እህቶችን በአካል እንገናኝ በማለት በማሳሳት እያሳሰሩ ይገኛሉ፡፤ እስካሁን ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሙስሊሞች በዚህ ድራማ ምክንያት በደህንነቶች ተይዘው ማእከላዊ አስር ቤት ታስረዋል፡፡

ይህን መሰሉ ስራ በአሁኑ ሰአት በደህንነት ሃይሎች ተጠናክሮ እየተሰራ ሲሆን ታሳሪዎቹንም ደህንነቶቹ የሚሄዱበት ቦታ ሳይቀር ይዘዋቸው እንደሚሄዱ ለማወቅ ተችሏል፡ከሁሉም የሚያስገርመው ግን ሙስሊሞቹን ቤተ ክርስቲያን ድረስ ይዘዋቸው አንድሚሄዱ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፤

በመሆኑም ይህን ዜና ያነበብን ሙስሊሞች ላልሰማው በማዳረስ የሚከተለውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለብን አናሳስባለን፡-

በተለይ ይህ ማሳሰቢያ በፉስቡክ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ለምትገኙ ሙስሊሞች ጠቃሚ ነው፡-

1.በአሁኑ ጊዜ ለትንሽ ቀናት በፌስቡክ ጠፍቶ የተመለሰን ሰው ተደብቄ ነበር ቢለን በምንም አይነት መልኩ ምንም አይነት መረጃ ከዛ ሰው ጋር አለመለዋወጥ

2.ታስሬ ነበር አሁን ተፈትቼ ነው ከሚሉን ሙስሊም ውንድሞቻችን እና እህቶቻችን ጋር በፌስቡክ ምንም አይነት መረጃ አለመለዋወጥ

3.በፌስቡክ የምናውቀውን እና የምናምንበት ሰው ቢሆን እንኳን በአካል እንገናኝ ቢለን በፍፁም መቀበል አይኖርብንም

4. በትግሉ ላይ ጥሩ የሚንቀሳቀሱ ሙስሊሞች በፌስቡክ አካውንታቸው ከወትሮ የተለየ ተደጋጋሚ ጥያቄ ከቀረበላቹ መጠርጠር ይኖርባቹሃል

5. ባጠቃላይ ስለግልሰቦች ማንነት ጥያቄ በፌስቡክ ለሚቀርብላቹ ማንም ይሁን ማን አለመናገር፡፤

6.ስል ግል ማንነታችሁ ለሚቀርብላችሁ ማንገኛው ጥያቄ ከማንም አካል ቢመጣ ምላሽ አለመስጠት

7.በፌስቡክ የምናውቀው ሰውም ሆነ በአካል የምናውቀው ሰው በስልክ እንድናወራ ቢጠይቀን ጥያቄውን መቀበል አይኖርብንም

8..ሰላማዊ ትግሉን በተመለከተ ስልምታውቁት መረጃዎች ቅርብ ከሆኑ ሰዎች ጋር በአካል በምትገናኙ ሰአት ብቻ መረጃ መለዋወጥ ያለባችሁ ሲሆን በፉስቡክ ግን በአሁኑ ሰአት መተማመን ባለመቻሉ ለጥንቃቄ ሲባል ብናስቀር የተሻለ ነው፡፤

ከላይ የተቀመጡትን ነጥቦች እና ተጨማሪ ጥንቃቄዎችን በመውሰድ እራሳችንን ከጠላት ወጥመድ እንጠብቅ፡፡

ተገደው በዚህ ተግባር ላይ የተሰማሩትን ሙስሊሞች አላህ ነጃ ያውጣቸው!!!

አላህ ከሸረኞች ወጥመድ ይጠብቀን፡፡

ድል ለኢትዬጲያ ሙስሊም!!!

No comments: