አየር መንገድ የድርጅት የአባልነት ፎርም ያልሞሉ 75
ተቀጣሪዎችን በፌደራል አባረረ
አየር መንገድ የድርጅት የአባልነት ፎርም ያልሞሉ 75 ተቀጣሪዎችን በፌደራል
አባረረ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በተለያየ የስራ መስክ በኮንትራት ሰራተኝነት
ተቀጥረው ከዛሬ አራት አመታት በፊት ሲሰሩ የነበሩ 75 ኢትዮጵያዊያን በቅርቡ
በአስተዳደሩ ‹‹የኢህአዴግ አባል የሚያደርጋቸው ፎርም እንዲሞሉ ተጠይቀው
የሚበዙት የእንጀራ ገመዳቸው እንዳይበጠስ በመስጋት ፎርሙን በመሙላት
የታዘዙትን ያደርጋሉ፡፡
ስራ በብቃት እንጂ የአባልነት መመዘኛ መሆን እንደማይገባው አቋም የያዙት
ጥቂት ህሊና አደር ሰራተኞች ቂም ተቋጥሮባቸው እድገትና የደሞዝ ጭማሪ
ተከልክለው በመስራትና ባለ መስራት ለወራት ከቆዮ በኋላ ዛሬ ማለዳ በስራ
ገበታቸው እንደተገኙ የፌደራል የደንብ ልብስ የለበሱ ሰዎች 75ቱን በመምረጥ
ልናነጋግራችሁ እንፈልጋለን ይሏቸውና ወደ አንድ ቢሮ ይወስዷቸዋል
‹‹ማንነታችሁን አጣርተናል ስለዚህ ከአሁን ወዲህ የዚህ ድርጅት ሰራተኞች
ባለመሆናችሁ ግቢውን ለቃችሁ ውጡ››ይሏቸዋል፡፡
በገዛ አገራቸው የድርጅት አባል ባለመሆናቸው ብቻ ለህገ ወጥ ስንብት
የተዳረጉት ኢትዮጵያዊያኑ ግቢውን አንለቅም ቢሉ ምን እንደሚከተላቸው
በመረዳታቸው የተባሉትን ተቀብለው ግቢውን ለቀዋል፡፡ ከዚህ ቀደም በአየር
መንገዱ ተቀጥረው ይሰሩ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን በተመሳሳይ መልኩ ከፎረምና
ከሊግ በመጡ ወጣቶች እንዲተኩ መደረጋቸው አይዘነጋም፡፡
የጉድ አገር ያለችው ማን ነበረች?

No comments:
Post a Comment