Tuesday, May 31, 2016

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ የሚደረገው ጫና ተጠናክሮ ቀጥሏል


በቃሊቲ ወህኒ ቤት በሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ በእስር ቤቱ ሃላፊዎች የሚደረገው ጫና ተጠናክሮ መቀጠሉ ታወቀ።
የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት 18 አመት እስራት ተፈርዶበት በወህኒ ቤት የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ካለፈው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ ከቤተሰብ እንዳይገናኝ ተከልክሏል፣ ስንቅ እንዳይገባለትም ዕገዳ ተጥሎበታል።
መስከረም 2003 ዓም ጀምሮ ላለፉት 5 አመታት ያህል በአሸባሪነት ተከሶና ተፈርዶበት በወህኒ ቤት የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ቀደም ሲል መጽሃፍ እንዳይገባለት የተደረገ ሲሆን፣ ማናቸውም ጽሁፍ እንዳይጽፍ ባዶ ወረቀቶችን እንዲሁም ወንበርን ጨምሮ ልዩ ልዩ የጽህፈት ማሳሪያዎችን እንደተወሰደበት መረዳት ተችሏል።
1985 ዓም ጀምሮ በኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ውስጥ ግንባት ቀደም ከነበሩት ጋዜጠኞችና የፕሬስ ባለቤቶች አንዱ ሆኖ የዘለቀው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ቀደም ሲል ለሰባት ጊዜያት ያህል የታሰረ ሲሆን፣ የአሁኑን ጨምሮ ሁሉም ክሶች ሃሳቡን በፁሁፍ ከመግልጹ ጋር የተያየዘ መሆኑን መረዳት ተችሏል።
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከቤተሰብ እንዳይገናኝ፣ ወይንም በቤተሰብ እንዳይጠየቅ ስለተከለከለበት ምክንያት የታወቀ ነገር የለም።


ኢሳት

Ethiopia’s government media continues fooling people with fake pictures.

Since recently, social media activists have revealed tenths of fake pictures used in the news outlets of government media.
Ethiopian Broadcasting Corporation (EBC), Fana Broadcasting Corporation (FBC), Ethiopian News Agency and government communications were some of the media caught red handed using pictures that are taken in the foreign countries to show the development of Ethiopia.
Obviously for political reasons government wants to tell people that it is constructing dams, roads and electric stations which are not on the ground but pictures of different countries are here to convince the audience.
Today, in the same phenomena, Ethiopian News Agency caught red handed using a picture that illustrate Moroccan professor who strive to advance livestock in his country. But Ethiopian News Agency used the livestock picture as it was in Ethiopian Southern part benefiting farmers. Here is the link for the original story. http://www.chicamod.com/2015/06/08/livestock-antibiotics-food-natural-remedy/
The Ethiopian News Agency’s fake news link is here. http://www.ena.gov.et/index.php/economy/item/2947-2016-04-03-14-05-10




 የተለያዩ በሀሰት ዜናዎች ህብረተሰቡን መደለል የለመዱት የመንግስት መገናኛ ብዙሀን ዛሬም እንደገና አስፋሪ ተግባራቸው ተጋለጠ። በሀገር ውስጥ ያልተሰራን ነገር ተሰራ እያሉ የውጭ ሀገራትን ፎቶ ግራፎችና ቪዲዮዎች በመጠቀም የፕሮፖጋንዳ ዜናዎችን ቀንና ማታ የሚፈበርኩት እንዚሁ ሚዲያዎች ፈጽሞ ከማህበራዊ ድረ ገጾች እውነታ ሊያመልጡ አልቻሉም። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከወራት በፊት በሞሮኮዋዊ ፕሮፌሰር የተሰራ የዜና ዘገባን በሀገር ውስጥ እንደሆነ በማስመሰል የደለቡ ከብቶችን ፎቶ በመስረቅ ደቡብ ክልል ውስጥ ገበሬዎች በከብት እርባታ ህይወታቸው ተለወጠ በማለት የሀሰት ዜና መጠቀሚያ አድርገውት ተይዘዋል።

በደቡብ አብዛኛው አርሶአደር የታጠቀው መሳሪያ ከመንግስት ቁጥጥር ውጭ ሲሆን በአማራ ክልል የእዝ ቁጥጥሩ የጠበቀ መሆኑን አንድ ጥናት አመለከተ

ግንቦት ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፰ / ኢሳት ዜና :- የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ወይም ሜቴክ በአገሪቱ ውስጥ ያሉ የጸጥታ ሃይሎችን ለመለየት እንዲያስችል በሚል በደቡብ እና በአማራ ክልሎች 2006 . ያደረገው ጥናት ዝርዝር ለኢሳት የደረሰ ሲሆን ጥናቱ እንደሚያሳዬው በደቡብ ክልል አብዛኛው አርሶአደር የታጠቀው  ዘመናዊ መሳሪያ ክላሽ ሲሆን፣ ይህ የጦር መሳሪያ ከመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ቁጥጥር ውጭ ነው።
የፖሊስና የሚሊሻ ሃይል ከታጠቅው በህብረተሰቡ የታጠቀው የተሻለ በመሆኑ በፀጥታ ሃይሎች ላይ አደጋ አየደረሰ መሆኑንሪፖርቱ አመልክቶ፣ ትጥቅ ለመመዝገብ ቢፈለግም፣ አብዛኛው ህዝብ የማስመዝገብ ፍላጎት እንደሌለው ይገልጻል።
በክልል  ፖሊስ እና የደቡብ ክልል ፈጥኖ ደራሽና ፀረ-ሽምቅ ሃይሎች እጅ  5117 መሳሪያ ሲኖር አጠቃላይ የጸጥታ ሃይሉ ብዛት ግን  11293 ነው። አብዛኛው የጸጥታ ሃይል  በቂ መሳርያ ስለሌለው ጥበቃውን የሚያካሂደው በዱላ መሆኑን ሪፖርቱ ያሳያል።
ወደ ክልሉ የሚገባው መሳሪያም ከደቡብ ሱዳንና ከኬንያ እንደሚመጣ ሪፖርቱ ይጠቁማል።
በአማራ ክልል የትጥቅ እጥረት እንዳለ የሚገልጸው ሪፖርቱ፣ በክልሉ በአጠቃላይ 184 ልዩ ሚሊሺያ፣ከ 20   በላይ ተጠባባቂ ሃይል እንዲሁም 12 ፖሊሶች አሉ።
በክልሉ እስከ 2006 ዓም 158 918 የግል የጦር መሳሪያዎች 92 671 የመንግስት የጦር መሳሪያዎች አሉ። በግለሰብ እና በመንግስት ከተያዙት የጦር መሳሪያዎች መካከል 70 በላይ የሚሆነው ሁዋላ ቀር የሆኑና አገልግሎት የማይሰጡ ናቸው።
መከላከያ ሚኒስቴር ለሜቴክ እንዲሰሩ ወይም እንዲገጣጠሙ የላካቸውን የጦር መሳሪያዎች ዝርዝር በተመለከተም ኢሳት መረጃ የደረሰው ሲሆን፣ መረጃውን በኢሳት ፌስ ቡክ አካውንትና በድረገጹ የሚለቀው ይሆናል። መረጃው መንግስት ያሉትን የታንኮች የመድፎችና ሌሎች መሳሪያዎችን አይነት እንዲሁም በአጠቃላይ የአገሪቱን የመሳሪያ አቅም የሚያሳይ ነው።


page1

Prof. Berhanu Nega “The fight with TPLF is in the heartland, not along the border”

 Prof. Berhanu Nega in Washington D.C. May 29, 2016
(ESAT News)— Chairman of the Patriotic Ginbot 7 Movement for Unity and Democracy, Prof. Berhanu Nega reiterated that armed operations by his Movement is not along the border with Eritrea as the regime in Addis Ababa would like the people to believe, but is inside the heartland as has been seen in the recent fight with regime forces in Arbaminch, south Ethiopia.
Addressing Ethiopians in North America at a meeting held in Washington DC on Sunday, the Chairman of Patriotic Ginbot 7, an armed coalition fighting the tyrannical regime in Ethiopia said the recent attack against regime forces in Arbaminch has proven the regime’s rhetoric wrong – that the armed group would launch an attack from the country’s border with Eritrea.
An attack by the Patriotic Ginbot 7 forces early this month killed at least 20 regime soldiers while 50 others sustained serious injuries.
Prof. Berhanu meanwhile called on Ethiopians in the diaspora to get organized and stay vigilant so as not to fall into the regime’s trap, which would otherwise destroy the fabric of Ethiopian civic and religious institutions in the diaspora.
He said Ethiopians abroad should work to bring officials of the corrupt regime to justice whenever and wherever they see them. He encouraged Ethiopians abroad to use alternative ways when they send money to their country as remittances are a significant source of foreign currency to the corrupt regime. He also urged Ethiopians to establish democratic institutions wherever they are and strengthen the culture of democracy.