ስለ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጋዜጠኛ ኤድመን ተስፋዬ (በኢትዮ – መኅዳር ጋዜጣ ላይ ከፃፈው)
ሰው ማለት ሰው የሆነ ነው ሰው የጠፋለት !
በመንቃት ላይ ባሉ፣
ፍጡራን መሀከል- ህይወት የምንለው፣
እንደ ጥሬ እህል፣ በኑሮ ምጣድ ላይ፣
ቢቆላ ቢማሰል -የበሰለው ያራል ፣ ጥሬው እስኪበስል፡፡ (ኃይሉ ገ /ዩሐንስ)
በመንቃት ላይ ባሉ፣
ፍጡራን መሀከል- ህይወት የምንለው፣
እንደ ጥሬ እህል፣ በኑሮ ምጣድ ላይ፣
ቢቆላ ቢማሰል -የበሰለው ያራል ፣ ጥሬው እስኪበስል፡፡ (ኃይሉ ገ /ዩሐንስ)
አምላክ ለሌሎች ፍጡራኑ ያልሰጠውን ፣ ነገር ግን ለሰው ልጆች ብቻ የሰጠውን የማሰብ ጸጋ ተግባራዊ በማድረጉ የተነሳ ነጻነቱን ለድርድር የማያቀርበው የፈክት መጽሔት ባልደረባዬ የነበረው ተመስገን ደሳለኝ ለኔ ማሰብ የጀመረ ሰው ከምንም በላይ ለነጻነቱ ቅድያ እንደሚሰጥ ማሳያ የሆነ ግለሰብ፡፡
በእኔ እምነት የአባት እዳ ለልጅ እንዲሉ፣ መጠላለፍ እና አሸናፊነትን እና ጸሸናፊነትን ብቻ ፖለቲካዊ ባህሉ ላደረገው እና አሁንም የሀገሪቷ ፖለቲካ ከሚዘውረው የያ ትውልድ የፖለቲካ ባህል ውስጥ ፣ ከመጠላለፍ ውስጥ ህብረትን ፣ ከአሸናፊነት እና ተሸናፊነት ውስጥ አሸናፊነትን እና አሸናነትን ችቻ ያሳየ የአዲሱ ትውልድ አንደበት ነው፡፡
ከጳጳስ እስከ ሼካ፣ ከሼካ እስከ ምሁር ፣ ከምሁር እስከ ኪነጥበብ ባለሙያ ወዘተ ሀገርን እና ህብረተሰብን ወደ ጎን በመተው ፣ ለጓዳው ብቻ በማሰብ ምናገባኝ ባይ በሆነበት ሀገር ውስጥ ከአንባገናዊ ስርዓተ መንግስት በላይ የሚያስጨንቀው እንደ እኔ እምነት አርአያ የሚሆን ግለሰብ ያጣችው እና የሞራልን ዋጋ የናዱ ግለሰቦች የሚፈነጩባት ሀገር እጣ ፈንታ ነው፡፡
እንደ እኔ እምነት፣ ተመስገን ደሳለኝ አርአያ የሚሆን ግሰብ ላጣችው እና የሞራን ዋጋ የናዱ ግለሰቦች መፈንጫ ለሆነችው ሀገሩ ሀገሬ በግለሰቦች የግል ፍላጎት የተነሳ ህልውናዋ አደጋ ላይ ሊወድቅ አይገባም በሚል ብእሩን የግልሰቦች ስብስብ በሆነው ስርዓት እና የስርዓቱ አንቋላጮች ላይ ያነሳ የሀገሩ እጣ ፈንታ ያስጨነቀው ግለሰብ ነው፡፡
እንደ እኔ እምነት፣ ተመስገን ደሳለኝ አርአያ የሚሆን ግሰብ ላጣችው እና የሞራን ዋጋ የናዱ ግለሰቦች መፈንጫ ለሆነችው ሀገሩ ሀገሬ በግለሰቦች የግል ፍላጎት የተነሳ ህልውናዋ አደጋ ላይ ሊወድቅ አይገባም በሚል ብእሩን የግልሰቦች ስብስብ በሆነው ስርዓት እና የስርዓቱ አንቋላጮች ላይ ያነሳ የሀገሩ እጣ ፈንታ ያስጨነቀው ግለሰብ ነው፡፡
ከህዝብ በሚሰበሰብ ቀረጥ የሚከናወነው የልማት እንቅስቃሴ ወደ ግለሰቦች ጓዳ በሚገባበት፣ ከኢህአዲግ አባልነት ውጪ ስራ ማግኘት ከባድ በሆነበት፣ የወጣት ጥቃቅን እና አነስተኛ ማህበራት የፋይናንስ ዋስትና አደጋ ላይ በወደቀበት ባለሀብቱ ዛሬ ደግሞ ምን ሊሉን ይሆን በሚል በነጋ በጠባ በሚጨነቅባት ባል እና እሴቶቻችን ጠፍተው የህዝቡን እና የሀገርን ሀብት የዘረፈ ደረቱን ነፍቶ በአደባባይ በሚሄድበት እና በሚከበርበት ፍትህን ለገንዘብ ብሎ ያዛባ ያሻውን በሚያደርግበት ከዲግሪ እስከ ፒኤች ዲ በዘረፈው ገንዘብ ገዝቶ በማን አለብኝነት በአስተዳዳሪነት በተቀመጠበት በዘመነ ኢህአዴግ ላይ ለአቅመ አዳም የደረሰው ተሜ የአዲሱ ትውል አካል እንደ መሆኑ ለአዲሱም ሆነ ለነባሩ ትውልደ በመረጃ የተደገፈ ሚዛናዊ ሂስ እና ትችት ከፍ ሲልም ማስጠንቀቂያና መፍትሄን ከድፍረትጋር ማቅረብ እንደሚቻ ያሳየ ከመሆኑም በላይ ኢትዮጵያዊነትን ማንም መስጠትም ሆነ መንፈግ እንደማይችል በተግባር ያሳየ ሰላማዊ ባለሞያ ነው ለኔ ፡፡
ለሆዱ አዳሪ የሆነ ማህበረሰብ በበዛበት እና ሀገር አርአያ የሆነ ግለስ ባጣችበት በዚህ ዘመን ኢትዮጵዊ ማንነትን ማንም የሚሰጠውም ሆነ የሚነጥቀው አይደለም የሚለው ጽኑ እምነቱ እንዳ ሆኖ እንዲህ መጻፍህን አቁም አልያም ሀገርህን ለቀህ ውጣ የሚል ማስፈራሪያም ሆነ መደለያ ቀርለት እንኳ አሻፈረኝ ያለው ተመስገን ደሳለኝ ለኔ ከአዲሱ ትውልድ የወጣ የዚህ ትውልድ ፈርጥ ነው፤፤ ማህበረሰቡ ውስጥ ሆኖ የማህበረሰቡን በደል በአደባባይ በማውጣት መንገስትን በሰላ ብእሩ የሚተቸው ተሜ ከምንም በፊት የህዝብ እና የሀገርን ህልውና በማስቀደም የመንግሰትን ገመና በመረጃ እና በአካዳሚካዊ ትንታኔ በአደባባይ ማውጣቱ በእኔ እምነት ተሜን ለጥላቻ እና ጠልፎመጣል ፖለቲካ አራማጆች አዲስ መንገድ ያሳየ ወጣት የሚያደርገው ይመስለኛል፡፡
ተመስገን ደሳለኝ ከፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል እስከ አንባገነናዊ የግለሰቦች ጭቆና በብእሩ መግለጹ በአንድ በኩል እንደ ህዝብ የደረሰበትንም ሆነ ወደፊት ስለሚጠብቀው አደጋ ለህዝቡም በማሳወቅ ረገድ በሌላ በኩል ለጭቆናውም ሆነ ለሌብነቱ መንስኤ ለሆኑት ግለሰቦች በነሱ የተነሳ በህዝቡ እና በሀገሪቷ ላይ ስላደረሰው እና ስለሚያደርሰው ሁነታ ለገዢዎቹ በማሳየት ረገድ ከፍተኛ ሚና ያበረከተ ብቻ ሳይሆን ገና የሚያበረክት ስመሆኑ ሳስብ ፊቴ ላይ ድቅን የሚለው እና የሚያሳስበኝ ተሜ ሰው በጠፋበትሀገር ሰው በመሆኑ የተነሳ በዝዋይ እስር ቤት ታስሮ በጀርባ ህመም የመሰቃየቱ ነገር ነው፡፡
ለዚህ ጽሑፍ መግቢያ ያደረኩትን ድንቅ ግጥም ያበረከተልን የዛ ዘመኑ ታጋይ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ኃይሉ ገብረየሁአንስ በህይወት ኖሮ የተሜን ህመም ቢሰማ ኖሮ ምን ይል ነበር?
በመንቃት ላይ ባሉ፣ ፍጡራን መሀከል
ህይወት የምንለው ፣ እንደ ጥሬ እህል፣
በኑሮ ምጣድ ላይ፣ ቢቆላ ቢማሰል የበሰለው ያራል፣ ጥሬው እስኪበስል፡፡
ህይወት የምንለው ፣ እንደ ጥሬ እህል፣
በኑሮ ምጣድ ላይ፣ ቢቆላ ቢማሰል የበሰለው ያራል፣ ጥሬው እስኪበስል፡፡
Source:: Zehabesha
No comments:
Post a Comment