የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች አሁንም ወደ ሳሙኤል ቤተሰቦች እንዳይሄዱ እንደታገዱ ናቸው
በትናንትናው ዕለት ሰኔ 8/2007 ዓ.ም የተገደለውን የሳሙኤል አወቀን ቤተሰቦች ለማስተዛዘን ከአዲስ አበባ ወደ ግንደወይን በሚሄዱበት ወቅት አባይ ድልድይ ላይ ከአዲስ አበባ በመጡ የፌደራል ፖሊሶችና ደህንነቶች ታፍነው ወደ ግንደወይን እንዳይሄዱ የተከለከሉት የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት አሁንም እንዳይንቀሳቀሱ እንደታገዱ ናቸው፡፡ ትናንት ከስምንት ሰዓት ጀምሮ ታስረው የዋሉት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ምሽቱ 2 ሰዓት ተኩል ላይ ቢለቀቁም መኪናውን ጨምሮ ቁሳቁሶቻቸው በሰሜን ሸዋ ዞን ወረጃርሶ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ በመያዙ መንቀሳቀስ አልቻሉም፡፡
የፖሊስ ጣቢያው ኃላፊ ኢንስፔክተር ወጋየሁ ጎንፋ መሬ ‹‹ወደ ገጠር ወጥቻለሁ›› በሚል እንዲሁም ሌሎች አመራሮች ቢሮ ዘግተው በመውጣታቸው ቁሰቁሶቹን መቀበል አልተቻለም፡፡ ይሁንና ኢንስፔክተር ወጋየሁን ጨምሮ ሌሎች አመራሮችም ከተማ ውስጥ እንደሚገኙ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ከእስር ሲለቀቁ ደህንነትና ፖሊሶቹ ነጻ እንደሆኑና እንዳጉላሉዋቸው በመግለጽ ይቅርታ ጠይቀው የነበር ቢሆንም ቁሳቁሶቻቸው ግን ‹‹ለምርመራ›› በሚል ይዘዋቸዋል፡፡ አመራሮቹና አባላቱ ‹‹ነጻ ከሆንን ቁሳቁሶቻችንም የሚያዙበት መንገድ መኖር የለበትም፡፡ ቁሳቁሶቻችን ካልሰጣችሁን አንወጣም›› ቢሉም ፖሊስ መብራቱን በማጥፋት ከግቢ አስወጥቷቸዋል፡፡
No comments:
Post a Comment