Tuesday, June 23, 2015

እነ ወይንሸት ሞላ ከእስር እንደተለቀቁ ታፈነው ታሰሩ

መንግስት አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰበብ ታስረው ሰኔ 15/2007 ዓ.ም በቄራ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት እንዲፈቱ የተወሰነላቸው ወንይሸት ሞላ፣ ኤርሚያስ ፀጋዬ፣ ዳንኤል ተስፋዬና ቤትሄልየም አካለ ወርቅ ዛሬ ሰኔ 16/2007 ከእስር ተፈትተው ሲወጡ በፖሊስና ደህንነቶች ታፍነው ታስረዋል፡፡
ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ታስረው የነበሩት ኤርሚያስ ፀጋዬና ዳንኤል ተስፋዬ ከእስር ከተፈቱ በኋላ የ6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ፖሊሶች ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በር ላይ ጠብቀው ያፈኗቸው ሲሆን ፖሊሶቹ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዳልያዙ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተመሳሳይ የ6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ፖሊሶች ወይንሸት ሞላንና ቤትሄልየም አካለ ወርቅ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት አፍነው መልሰው እንዳሰሯቸው ታውቋል፡፡
የቄራ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በትናንትናው ዕለት ወይንሸት ሞላ፣ ዳንኤል ተስፋዬና ቤትሄልየም አካለ ወርቅ ላይ የሁለት ወር እስር ፈርዶ፤ ከሚያዝያ 14/ 2007 ጀምሮ ሁለት ወር ከአንድ ቀን የታሰሩ በመሆኑ ከእስር እንዲፈቱ ወስኖ ነበር፡፡ ኤርሚያስ ፀጋዬንም በነፃ እንዲለቀቅ ወስኖለት ነበር፡፡ ይሁንና ፖሊስና ደህንነቶች የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመጣስ አፍነው እንደገና አስረዋቸዋል፡፡

No comments: