በከፍተኛ የመንግስት አካላት ጭንቀት እና ውጥረት የተካሄደው ሰልፍ
ተጠናቀቀ:;
ጅምሩም መጨረሻውም በውል ያልተለየው የዛሬው ሰልፍ ከፍተኛ ውጥረት የነገሰበት ነበር፡፤ህብረተሰቡ አክራሪነትን
ለመቃወም ሙሉ እምነት እና ሞራሉ ያለው ቢሆንም በደረሰበት ግዳጅ እና ማስፈራሪያ በዝናብ ከቤቱ ተገዶ በመውጣቱ
በተሳታፊው ላይ ድብርትን እና መሰላቸን አስከትሏል፡፤ተፈጥሯዊው የሆነውም ዝናብ ሰልፉ አንዲቀዛቀዝ እና ህዝቡ በሰልፉ
ላይ ተገዶ መሰለፉን በውስጡ አንዲያማርር ከፍተኛውን ድርሻ ወስዷል፡::
ሰልፉ የተጠራበት አጀንዳ ታላቅ እና አገራዊ አጀንዳ ቢሆንም ህብረተሰቡ ላይ በተፈፀመበት የማስገደድ ተግባር ሰልፉ ላይ ውሃ
ሊከልስበት ችሏል፡፡ ህዝበ ሙስሊሙም ጉዳዩ ከማንም በፊት ይመለከተኛል በማለት በሰልፉ ላይ ተገኝቶ አክራሪነትን
ለመቃወም ቢያስብም አብዛኛውን ሙስሊም ማህበረሰብ መንገድ በመዝጋት እንዳይካፈል አድርገውታል፡፡ የተካፈሉትንም
ሙስሊሞች ህገ ወጡ የመጅሊስ ሹመኛ ንግግር ሲያቀርቡ ጆሯቸውን በመያዛቸው ካሉበት በደህንነቶች እየታፈኑ ተወስደዋል፡፤
እስካሁን ቁጥራቸው ከ 50 የሚበልጡ ሙስሊሞች ከህዝብ መሃል ታፍነው ተወስደዋል፡፤
ሰልፉ በመንግስት እንደሚካሄድ ከታወጀበት ቀን አንስቶ ከባድ ቅሰቀሳ በሚዲያዎች እና ቤት ለቤት ቅስቀሳ ቢካሄድም በዛሬው
|ዕለት ግን ሚዲያዎች የቀጥታ ስርጭት እንኳን ሳይሰጡት ቀርተዋል፡፡ፕሮግራሙ ስለመጠናቀቁ ከማብሰር ውጪ ሌላ ያሉት
ነገር የለም፡፤ይህ የሚያሳው ሙስሊሙ ማህበረሰብ አክራሪነትን ለመቃወም በነቂስ እንደሚወጣ ጥሪ በመደረጉ በመንግስት
በኩል ከፍተኛ ድንጋጤ በመፈጠሩ ነው፡፤
ሰላማዊ ሰልፍ ተብሎ በአካባቢው ግን የጦር አወድማ እስኪመስል በወታደር እና በጦርመሳሪያ አካባቢውን መጨናነቁ
በመንግስት በኩል የተፈጠረውን መሸማቀቅ እና ፍርሃት ቁልጭ እርጎ ያሳየ ነበር፡፤ ህዝበ ሙስሊሙ በሰልፉ ላይ የሚሳተፍበትን
ምክንያት ጥርት ባለ መልኩ ማስቀመጡ የሚታወስ ቢሆን ሰላም ወዳዱን ሙስሊም ማህበረሰብ በሰልፉ ላይ እሳተፋለው
በማለቱ ብቻ ለማሸማቀቅ ተሞክሯል፡፤
የሰልፉ ስነ ስርአት መጀመሩ ከተነገረ ቡሃላ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተገዶ ተሰላፊዎች ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ሰልፉን
በመተው ወደመጡበት ሲመለሱ ነበር፡፤ሰልፉም ከተተናቀቀ ቡሃላም በሰልፉ ላይ ተሳተፉ ሙስሊሞችን የማደኑን ስራ በከፍተኛ
ሁኔታ ተጧጡፎ ቀጥሏል፡፡
ህዝበ ሙስሊሙ አክራሪነትን ከማንም በፊት እኛም እንቃወማለን በማለት በነቂስ ለመውጣት ለመሳተፍ መወሰናቸውን
ከተገለጸ ቡሃላ በመንግስት ላ|ይ በተፈጠረበት ጭንቀት ብዙ የተደከመለት ሰልፍ ተሰላፊዎችንም አሰላችቶ በብርድ እና በዝናብ
አስደብድቦ ያለምንም ትርፍ ተጠናቋል፡፤
ህብረተሰቡ አክራሪነትን ለመቃወም ሰልፍ ሲወጣ ይዞት ሊመለስ የሚችለውን ግንዛቤ በሙሉ በተፈጸመበት የማስገደድ እና
የማስፈራራት እርምጃ ዜሮ አስገብቶታል፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ እና ህዝበ ክርስቲያኑ መቼም ቢሆን በማንም ሴራ ሊለያዩ እና
ሊከፋፈሉ እንደማይችሉ በዛሬው በትካዜ እና በቁዘማ መልክ በተካሄደው ሰልፍ ላይ አሳይተዋል፡፤
በመንግስት ብዙ የተዘፈነለት፣ብዙ ገንዘብ የተፈሰሰለት፣ብዙ የመንግስት ስራዎች ተበድለው ለዚህ ሰልፍ ቅስቀሳ በዋሉለት
የተቃውሞ ሰልፍም ለመንግስት እራስ ምታት እና ውጥረት ብቻ ፈጥሮ ሚዲያዎቹም ከዚህ ቀደም ሲፎክሩበት የነበረውን ወኔ
አጥተው ሰልፉ እንደደበዘዘ ተጠናቋል፡፤

No comments:
Post a Comment