ካንጋሮ ፍርድ ቤቱ አቅለሸለሸን!
የሼህ ኑሩ ይማም ልጅን በመውጋት ጉዳት ያደረሰ ግለሰብ በ6 አመት ጽኑ እስራት
ተቀጣ
አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 16 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የሼህ ኑሩ ይማም ልጅን በመውጋት
ጉዳት ያደረሰ ግለሰብ በ6 አመት ጽኑ እስራት ተቀጣ።
በደሴ ከተማ ሸዋ በር መስጊድ በተካሄደ ሀይማኖታዊ ስብሰባ ላይ የሀይማኖት አባቱ
ሼህ ኑሩ ይማም አዲሱ የእስልምና አስተምህሮት እኛ ከወንድሞቻችን ጋር ተዋደንና
ተከባብረን የምንኖር ሙስሊሞችን አይወክልም በሚል ንግግር ማድረጋቸው
ያልተዋጠለት አንድ የእምነቱ ተከታይ በወቅቱ ሀሳብን በሃሳብ ከመቃወም ይልቅ
ስድብና ዛቻን በሀይማኖት አባቱ ላይ አውርዶባቸዋል።
አባትህ ተሰድበዋል የሚል ዜና የደረሰው የሼህ ኑሩ ይማም ወንድ ልጅም በሰማው
ነገር በመናደድ እንዴት የሀይማኖት አባትህን ትዘልፋለህ ሲል እዚያው መስጊዱ
አካባቢ የነበረውን ይህን ግለሰብ ይጠይቀዋል ፥ ግለሰቡም ከጎኑ ሻጥ አድርጎት
በነበረው ሳንጃ እንደወጋውና ለመገላገል ከመጡ ግለሰቦች መካከልም ወጣት
ሸምሰዲን የተባለውን ግለሰብ በተመሳሳይ በመውጋት መሰወሩን የፖሊስ ማስረጃ
ይገልፃል።
ፖሊስም ከደሴ ባቲ ከባቲ እስከ ቃሎ በደረሰ የክትትል ወጥመድ ወንጀለኛውን በቃሎ አካባቢ በቁጥጥር ስር አውሎታል።
ለደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን የቀረበ ሲሆን ፥ ተከሳሽም ድርጊቱን መፈጸሙን አምኗል።
ፍርድ ቤቱም ሀሳብን በሀሳብ ማሸነፍ ሲቻል በበቀል በመነሳሳት የተፈጸመውን ወንጀል በማውገዝ ተከሳሽ አህመድ ሙስጠፋን በ6 አመት ጽኑ እስራት መቅጣቱን የደሴ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ሀላፊ ኢንስፔክተር የሺወርቅ ላቀው የላኩልን መረጃ ይጠቁማል
No comments:
Post a Comment