ከህዝባዊ ስብሰባው የተማርኩት
Abraha Desta
ባለፈው ሳምንት (እሁድ ሓምሌ 14, 2005 ዓም) ዓረና-መድረክ በመቐለ ከተማ ህዝባዊ ስብሰባ መጥራቱ ይታወሳል።
ባለስልጣናቱ ስብሰባውን ፈቅደው ሲያበቁ ስለስብሰባው ቅስቀሳ ማድረግ ግን ከለከሉ። ቅስቀሳ ሲያደርጉ የተገኙ ሁለት የዓረና
ትግራይ ፓርቲ አባላትና (ስልጣኑ ሕሸና ይርጋ ገብሩ) እንዲሁም የአንድነት አባል የሆነው ክብሮም ብርሃነ ታሰሩ።
የህወሓት አባላት ህዝብ በስብሰባው እንዳይሳተፍ እንዲያስጠነቅቁ ከበላይ ሓላፊዎቻቸው ትእዛዝ ደረሳቸው። ሰው ወደ አደራሹ
እንዳይገባ ጥረት ተደረገ። ካድሬዎች ወደ አደራሹ የሚገባ ሰው ፎቶ ማንሳትና ቪድዮ መቅረፅ ጀመሩ። የትግራይ ክልል የንግድና
ኢንዳስትሪ ሰራተኞች በስብሰባው የተሳተፈ ነጋዴ ለመለየት እንዲችሉ ተሰማሩ።
ይሄን ሁሉ ሰብሮ ህዝቡ አደራሽ ዉስጥ ገባ። አደራሹ ሞላ። ካድሬዎቹ ግራ ተጋቡ፣ ደነገጡ፣ ተስፋ ቆርጠው ተበተኑ። ስብሰባው
ተአምረኛ ነበር። (ስለ ስብሰባው ይዘት ሌላ ግዜ እመለስበታለሁ)። እኔ ግን ስለ መቐለ ህዝብ ስሜት የተሳሳተ ግምት ነበረኝ።
የትግራይ ህዝብ ህወሓት እንደማይደግፍ ባውቅም ሓሳቡ ለመግለፅ ግን የሚፈራ ይመስለኝ ነበር። ከስብሰባው በኋላ ግን
የትግራይ ህዝብ በድፍረት መናገር መቻሉና ህወሓት ከ አሁን በኋላ በማስፈራራት መግዛት እንደማይችል ተገነዘብኩ። የመቐለ
ህዝብ ድፍረት አበራታች ነው።
ሌላው አስገራሚ ነገር ደግሞ የህወሓት ደጋፊዎችና አባላት የህወሓት ባለስልጣናት ስብሰባው ለማሰናከል ባደረጉት ሙከራ
በጣም ማዘናቸው ነው። አብዛኞቹ የህወሓት አባላት ህወሓት ህዝብ በስብሰባው እንዳይሳተፍ ማስጠንቀቃቸው አሳዝኗቸዋል።
ብዙዎቹ (የህወሓት አባላት) ለውጥ ፈላጊ፣ እንዲሁም ለዓረና ፓርቲ መጥፎ አመለካከት እንደሌላቸው ለመገንዘብ ችያለሁ።
የመቐለ ህዝብ ለውጥ እንደሚፈልግ አረጋግጧል። በስብሰባው የተሰጡ አስተያየቶች ስገመግም በፌስቡኬ ከምፅፋቸው
የተቃውሞ ሓሳቦች እጅግ በጣም እንደሚሻሉና እንደሚጠነክሩ ላረጋግጥላቹ እወዳለ
No comments:
Post a Comment