በማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ላይ የተመሰረተው ክስ ዛሬ ታየ!
ማክሰኞ ሐምሌ 23/2005
የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትና ሌሎች ታሳሪዎች በማረሚያ ቤት አስተዳደር ላይ የመሰረቱት ክስ ዛሬ ታየ፡፡ የማረሚያ ቤቶች አስተዳደር በመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትና በሌሎች ታሳሪ ወንድሞቻችን ላይ እያደረሰ ያለውን በደል በመቃወም መሪዎቻችን የመሰረቱት ክስ በታየበት በዛሬው ችሎት የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴው ሰብሳቢ ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ ታሳሪዎችን በመወከል ፍ/ቤት ቀርቦ ነበር፡፡ ኡስታዝ አቡበከር በወህኒ ቤቱ ሐላፊዎች እየደረሰባቸው ስላለው በደል ለፍ/ቤት ያስረዳ አስረድቷል፡፡ ታሳሪዎች በእስር ቤቱ በአጭር ክፍለ ወሰን በተመደበው የመጠየቂያ ሰዓት ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመገናኘት ካለመቻላቸውም በላይ ለጥየቃ ያንን ያህል ርቀት አቋርጠው የሚሄዱ ቤተሰቦቻቸው እና ወዳጆቻቸውም መጠየቅ እንዳይችሉ ክልከላ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡
እስር ቤቱ ለአቅመ አዳም ያልደረሱ የሕሊና እስረኞቹ ቤተሰብ የሆኑ ሕጻናት ልጆችን የቀበሌ መታወቂያ እንዲያመጡ በመጠየቅ፣ መታወቂያ የያዙትንም የተለያዩ ሰበቦች በመፍጠር ለጥየቃ እንዳይገቡ በመከልከል እንዲሁም የመጠየቂያ ሰአቱን ያለ ቅድመ ማሳወቂያ እንደፈለጉት በመቀየር፣ በእስር ቤቱ ውስጥም መሪዎቻችንን በማሳቀቅ ስራ ላይ መጠመዳቸው እንዲገታና ተገቢውን የእስረኛ መብት ማግኘት እንዲችሉም ነው ክሱ የመሰረቱት፡፡ ፍ/ቤቱም በእስከአሁኖቹ ችሎቶች ሳይቀርቡ ቀርተው ዛሬ የቀረቡትን የማረሚያ ቤት አስተዳደር ተወካዮች ምላሽ እንዲሰጡ ጠይቋል፡፡ የማረሚያ ቤት ተወካዮችም ያሉትን ችግሮች ለማረም ፈቃደኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ፍ/ቤቱም የሚሻሻሉ ነገሮችን ለማየትና መልሶ ለመገምገም ለሐምሌ 30 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ ችሎቱ ተጠናቋል፡፡
አላሁ አክበር!

No comments:
Post a Comment