የድሬዳዋ-ጅቡቲ-አዲስ ባቡር ሐዲድ ዝርጋታ ጉዳይ
(ትናንት ዕሁድ ሐምሌ 21/2005 ዓም አዲስ አበባ የታተመው ሪፖርተር ጋዜጣ ይህንን አስነበበ )
(ትናንት ዕሁድ ሐምሌ 21/2005 ዓም አዲስ አበባ የታተመው ሪፖርተር ጋዜጣ ይህንን አስነበበ )
''የኢጣሊያ ኩባንያ ከጅምሩ ለሥራው ብቁ እንዳልነበረ እየታወቀና በተለያዩ ጊዜያት ኃላፊነት ያለባቸው የምድር ባቡር የማኔጅመንት አባላት፣ የፋይናንስ ሚኒስቴር ተወካይ፣ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ተወካይ እንደዚሁም ኮንሰልታንት የነበረው ኢኔኮ የተባለው ስፔናዊ ተቆጣጣሪ ድርጅት ጭምር ባልሳሳት በየጊዜው የተሠራውንና የተደረሰበትን ለመገምገም ድሬዳዋ እየተገናኙ ይነጋገሩ ነበር፡፡ ሆኖም ጠብ ያለ ሥራ ሳይሠራና 30 ኪሎ ሜትር ያህል እንኳን ሐዲድ ሳይዘረጋ ጠያቂም ተጠያቂም ሳይኖር ድርጅቱ (ኮንስታ) ከ1/3ኛ በላይ የሆነ ገንዘብ ካባከነ በኋላ የተጀመረው ሥራ እንዲቆም ተደርጓል፡፡
የሚገርመውና የሚያሳዝነው ደግሞ ምንም እንዳልተሠራና የመስመርና የድልድይ ሐዲዶች ተነስተው ለባሰ ኪሣራና ውድመት ድርጅቱ መዳረጉ እየታወቀ... መስመሩ እንደተሠራና እንዳለቀ ተቆጥሮ ባለፈው አምስት ወር ከፍተኛ ወጪ ወጥቶ ድል ያለ ድግስ ተደግሶ ምረቃ መደረጉ ነው፡፡ ለኮንስታም ድርጅት ሽልማት መስጠቱ እንደዚሁም በድርጅቱ ኃላፊዎችም የትራንስፖርት ሥራው ተጀምሮ በሳምንት አምስት ጊዜ ባቡር እየተመላለሰና ሥራው እንደተጀመረ መግለጫ መሰጠቱ አነጋጋሪ ነው........ በያዝነው ወር ደግሞ የ114ቱ ኪሎ ሜትር 60 ሚሊዮን ዩሮና ለድግሱ ወጪ ብክነት ተጠያቂው ማን እንደሆነ ሳይለይ፣ ከድሬዳዋ ጂቡቲ መስመር ለማስቀጠል የድርጅቱ ኃላፊዎች ከፍተኛ ወጪ በማውጣት የሐዲድ መስመሩን ለመጠጋገን ዘመቻ ጀምረዋል (በቅርቡ አይሻ ላሠራውና ጐርፍ ወስዶት ተጠገነ የተባለውን 2,000,000 ብር ወጪ የሆነውን ሳይጨምር)፡
No comments:
Post a Comment