"ይህ ያየዝነው ሣምንት የረመዷኑ የመጨረሻው ጁምዓ የሚገኝበት ሳምንት
እንደመሆኑ መጠን በአገር አቀፍ ደረጃ ጠንከር ያለና በድጋሜ ቁጥሩ እጅግ በርካታ
የሆነ ሙስሊም ሕዝብ የሚሳተፍበት የተቃውሞ ቀን ሆኖ ይውላል፡፡ ቀጣዮቹን
ተቃውሞዎች የምናካሄደው ከዚህ ቀደም ይቀርቡ የነበሩ ጥያቄዎችን ዳግም
ለማንሳትና የሚመለከተው አካል ምላሽ እንዲሰጠን ለመጠየቅ ነው፡፡
የአራተኛው ሳምንት የጁምዓ ተቃውሞ ‹‹የዒባዳና የነፃነት ሳምንት›› በሚል
መሪ ቃል በአዲስ አበባና በክልል ከተሞችና በተለመዱ መስጂዶች ተካሂዶ
እንደሚውል ይጠበቃል፡፡ የዚህን ሳምንት የተቃውሞ መርሐ ግብር ሳምንቱ
የረመዷን የመጨረ አስር ቀናት የሚገኙበት በመሆኑ ከወትሮው ለየት ያለ ነው፡፡
በዚህ ሳምንት የጁምዓ ተቃውሞ በልዩ ሁኔታ ጠንከር ያለ ተቃውሞ ማድረጋችን
እንደተጠበቀ ሆኖ ለዚህ ተቃውሞ ከምናወጣው ጉልበት፣ ጊዜና ገንዘብ
ባልተናነሰ በግላችንም ሆነ በጀመዓ በመሆን ሁላችንም ፊታችንን ወደ አላሁ
ሱብሐነሁ ወተዓላ በማዞር እጆቻችንን ከፍ በማድረግ ለአገራችን ሠላም፣ለእምነት
ነጻነት መከበር፣ ለፍትህ እና ለህግ የበላይነት መረጋገጥ ለምናደርጋቸው
ፍፁም ሠላማዊ ትግል መሳካት ፈጣሪያችንን መለመን ይኖርብናል፡፡ ብዙዎቻችን
በርካታ ወንጀሎች ቢኖሩብንም ከመካከላችን ያሉ ደጋግ (ሷሊህ) አሉና እንደ ሰው
ያልሆነው ፈጣሪያችን በነኚህ ሰዎች ዱዓ ሰሰብ እርዳታውን ያቀርብልናልና በጌታችን
ተስፋ አንቆርጥም፡፡ ከዚህ በተጓዳኝ ከቁርኣን ጋር ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ትስስር
በመፍጠር በርካታ የቁርኣን አንቀፆችን ማንበብ፣ ሰደቃ (ምፅዋት) መስጠት፣
የቲሞችን ማስታወስ፣ ባጠቃላይ ኸይር ስራዎችን መስራት ይጠበቅብናል፡፡"
No comments:
Post a Comment