“በቅርቡ ከአቶ ኩማ ደመቅሳ ላይ የአዲስ አበባ ከንቲባነትን የተረከቡት ከንቲባ ድሪባ ኩማ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ሐምሌ 28 ቀን 2005 ዓ.ም በመብራት ኃይል የሚያካሂደውን ሕዝባዊ ስብሰባ ፈቀዱ።”
“የአራት ፓርቲዎች ግንባር የሆነው መድረክ በማኒፌስቶውና በሌሎች የሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ለማድረግ በተደጋጋሚ ጊዜአት ጥያቄ ቀርቦ ውድቅ ሲደረግ መቆየቱን የተናገሩት የመድረክ ሊቀመንበር አቶ ጥላሁን እንደሻው ናቸው። እንደ ሊቀመንበሩ ገለፃ መድረክ ሐምሌ 7 ቀን 2005 ዓ.ም መነሻውን 6 ኪሎ ያደረገ፣ መድረሻውን ደግሞ ድላችን ሐውልት ያደረገ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የእውቅና ጥያቄ ቢቀርብም በከተማዋ በርካታ የኮንስትራክሽን ስራዎች እየተካሄዱ በመሆኑ ሰልፍ ማካሄድ አትችሉም የሚል ሐምሌ 1 ቀን 2005 ዓ.ም ከከንቲባው ጽ/ቤት በተፃፈ ደብዳቤ መከልከሉን አስታውሰዋል።”
ሠንደቅ ጋዜጣ -ሐምሌ24/2005
ከዚህ በፊት የሰማነው ምክንያት የከተማ ፖሊሶች ወይም የፀጥታ ሃይሎች ‹ሌላ ግዳጅ ላይ ስለሆኑ› ወይም ‹ስልጠና ላይ ናቸው› የሚል ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ‹በከተማዋ በርካታ የኮንስትራክሽን ስራዎች እየተካሄዱ በመሆኑ› መባል ተጀመረ፡፡ አዲስ አበባ ተገንብታ እስክታልቅ እንግዲ ደህና ሠላማዊ ሰልፍ መከልከያ ሰበብ አገኙ፡፡
ምናልባትም አዲስ አበባ ከራስ ፀጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ ግንባታ ላይ የመሆኗ ቅኔው ይህ ይሆናል፡፡

No comments:
Post a Comment