መንግስት በበኒ መስጂድ ለስለላ ካሰማራቸው መካከል የሆነ አንድ ተላላኪ የኢቲቪን ዘገባ በመተቸቱ ምክንያት በመንግስት ሃላፊዎች በከፍተኛ ደረጃ ተገሰፀ ፡፡
ባለፈው ጁሙዐ የተካሄደውን ግዙፍና ከባድ ሰላማዊ ተቃውሞ ለመሰለል በመንግስት ከተላኩ ሰላዮች መካከል አንዱ በመንግስት መገሰፁ ታወቀ፡፡ ሰውየው ከሪፖርት ተቀባይ አለቆቹ ከባድ ተግሳፅ ያስተናገደው በበኒ መስጂድ የተካሄደውን የጁሙዐ ተቃውሞ የስለላ ሪፖርት ለማቅረብ ቅዳሜ ከጠዋቱ 3 ሰዐት አካባቢ በተሰበሰቡበትና የተቃውሞውን ዉሎ በሰፊው እየተነጋገሩ በነበሩበት ወቅት መሆኑ ታውቋል ፡፡ ነዋሪነቱ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የሆነው ይህ የመንግስት ተላላኪ በሚቀርቡት ሪፖርቶች ላይ ውይይት እየተካሄደ ሳለ እጁን አውጥቶ “በበኩሌ በኢቲቪ ላይ አንድ ቅሬታ አለኝ፣ ኢቲቪ የጁሙዐዉን ተቃውሞ አስመልክቶ የዘገበው አዘጋገብ መንግስትን ይጎዳል ብየ ነው የማምነው፡፡ ምክንያቱም በወቅቱ ኢቲቪ ችግር ተፈጥሮ ነበር ባለበት ቦታና በለቀቀው ተንቀሳቃስ ምስል ላይ ያሳየው አይሱዚ መኪናው በነበረበት አካባቢ ላይ የተፈጠረ ችግር አልነበረም ፡፡ በወቅቱ በቦታው እኔ ነበርኩ ፡፡ምንም ችግር አልተከሰተም ፡፡ ኢቲቪ ግን ችግር እንደነበረ አድርጎ ነው የዘገበው ፡፡ ይህም መንግስትን ውሸታም ሊያስብል ስለሚችል እና ሙስሊሞቹም ፕሮፖጋንዳ ሊሰሩበት ስለሚችሉ ለወደፊቱ እንዲህ አይነት ግልፅ እውነት ላይ ስህተት እንዳይሰራና መንግስትን እንዳያስተች ለኢትዮፕያ ሬዲዮና ቴሌቪዝን ድርጅት መመሪያ ቢተላለፍ ጥሩ ነው ” የሚል አስተያየት ሰጥቷል ፡፡ በወቅቱ በቦታው የነበሩ ምንጮች እንደገለፁት ሰውየው ይህን አስተያየት ከሰጠ በኋላ መድረኩ ላይ የነበሩት የመንግስት ተወካዮች አንተ ፖለቲከኛ ሆነህ ሳለ እንዴት እንዲህ ትላለህ ? ያንተ ስራ ከመንግስት የተሰጠህን የራስህን ስራ መስራት ብቻ ነው ፡፡ እዛ ቦታ (በኢቲቪ) ስለቀረበው ነገር አይመለከትህም ፡፡ ኢቲቪን በተመለከተ ተቋሙን የሚመሩ እና የሚከታተሉ ሰዎችን መንግስት መድቧል ፡፡ ደግሞም ማወቅ ያለብን መንግስት የራሱ አቋም ያልሆነውን ነገር የፈለገ ቢሆን በኢቲቪ አይለቅም፡፡ እናንተ በተለይ እዚህ ቦታ ያላችሁ ለወደፊቱ ይህ አይነቱ ነገር ሊገባችሁ ይገባል፡፡ በተለይ ሃሳብ የሰጠሀው ሰው ይህ ካንተ አይጠበቅም፡፡ አንተ ለራስህ የምትሰራው የራስህ ስራ ከመንግስት ወስደሃል ፡፡ የተሰጠህን ሃላፊነት መወጣት ብቻ ነው በቃ! የሌላው ስራ ላይ ደግሞ የራሱ ተቆጣጣሪ መንግስት ስላለው እነሱ ይጨነቁበት ” የሚል ምላሽ እንደሰጡት ታውቋል ፡፡ ሃሳቡን ያቀረበው ተላላኪም በምላሹ እንዳዘነና በሀፍረትም እንደተሸማቀቀ ምንጮቹ ጨምረው ገልፀዋል፡፡ በውሸት የተገባ መንግስት ላይነሳ መንኮታኮቱ አይቀርም!
ድል ለሙስሊሙ፡፡
አላሁ አክበር

No comments:
Post a Comment