ከሚሴ የጦር ቀጠና መስላ ዋለች!!
መንግስት ለዛሬ እሁድ ሐምሌ 21/2005 እራሱ የገደላቸውን የሸህ ኑሩን ሞት አስመልክቶ የከሚሴ ነዋሪዎችን በግዳጅ ሰልፍ እንዲወጡ ለማድረግ ሰሞኑን ጁምዓ ሐምሌ 19/2005 በየቤቱ እየዞረ በግዳጅ ሲያስፈርም እንደነበር “ፈስቢር” ዘግባ ነበር፡፡
ሆኖም፤ ለዚህም ሲባል ዛሬ እሁድ ሐምሌ 21/2005 ከማለዳው ጀምሮ የከተማው ፖሊሶችና የፌደራል ፖሊሶች ከነሙሉ ትጥቃቸው፤ በፖትሮል መኪና እና በእግር ከተማውን በመውረር የጦር ቀጠና አስመስለውት ነበር፡፡ የከተማው ህዝብም ይህን የግዳጅ ሰልፍ አንወጣም በማለቱ፤ እነዚህ የመንግስት ተላላኪዎች በየቤቱ በማንኳኳት “ሰልፍ ውጡ ሰዓቱ አኮ አለፈ!” በማለት ሰላም ሲነሷቸው እንዳረፈዱም ሪፖርተራችን ገልፆልናል፡፡
ሆኖም ግን በዛሬው የግዳጅ ሰልፍ የከተማው ነዋሪዎች ያልታዩና ያልተሳተፉ ቢሆንም፤ ከከተማው ወጣ ብለው ገጠሩ ክፍል ላይ የሚኖሩ ገበሬዎች ግን፤ መንግስት “መሬታችሁን ትቀማላችሁ፤ ማዳበሪያ አታገኙም፤ እንዲሁም ሌሎችን ትብብሮች ከመንግስት አታገኙም” በማለት ስላስፈራራቸው በተወሰነ መልኩ ሰልፉን ሊገኙ ችለዋል፡፡
የዛሬውን የግዳጅ ሰልፍ ሲመሩት የነበሩት፤ የከተማው የመንግስት ካድሬዎች ሲሆኑ፤ የገጠሩ ነዋሪ ግን በግዳጅ የወጣ በመሆኑ አንድም መፈክር አልያዘም ነበር፡፡ መፈክር የያዙት ከፊት ሆነው ሰልፉን የሚመሩት የከተማው ካድሬዎች ነበሩ፡፡
እነዚህ ካድሬዎች የተለያዩ መፈክሮችን ለማስተጋባት የሞከሩ ቢሆንም፤ ከኋላ በግዳጅ እንዲከተል የተገደደው የገጠሩ ገበሬ ግን መፈክሩን ችላ በማለት ዝም ሲል ታይቷል፡፡ በዚህም ጊዜ በተለይ በከተማው በአህባሽ አቀንቃኝነቱ የሚታወቀው ኢብራሂም አርጎባው የተባለው ግለሰብ በሰልፈኞቹ መሃል እየተሽሎከለከ “በሉ እንጂ!” በማት ሲያስገድዳቸው ተስተውሏል፡፡
የአካዳሚክ እውቀታቸው ዝቅተኛ መሆኑን በመጠቀምና፤ በማስፈራሪያና እንዲሁም በጥቅማጥቀም ተገደውና ውስጣቸው ሳይፈልግ የወጡት የገጠሩ ገበሬዎች፤ በካድሬዎቹ አማካኝነት አስፋልት ላይ ትንሽ እንዲቆዩ ከተደረገ በኋላ፤ ቀጥሎ ወደ ኳስ ሜዳ በማምራትና ለሸህ ኑሩ የህሊና ፀሎት አድርጉ ተብለው ኳስ ሜዳ ላይ እንዲቆዩ ተደርገዋል፡፡ በመጨረሻም በዚህ አስቂኝና የመንግስትን መርበትበት በሚያሳይ መልኩ፤ ድራማው ሊጠናቀቅ መቻሉን በከሚሴ የ”ፈስቢር” ሪፖርተር ዘግቧል፡፡
የከሚሴ ከተማ ነዋሪዎች አኮራችሁን!!

No comments:
Post a Comment