ኢህአዴግ ስለምን ደነገጠ?
=================
በአንድነት ፓርቲ “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” በሚል መሪቃል እያካሄደ ያለው
ህዝባዊ ንቅናቄ በኢህአዴግ ቤት ውጥረት መፍጠሩን የሚያሳብቁ ተግባራትን
እያከናወነ ነው፡፡ የስርአቱ ቁንጮ ባለስልጣናት በአንድነት ፓርቲ ጉዳይ በየጊዜው
እየተሰበሰቡ መዶለታቸውን ምንጮች ለተለያዩ ሚዲያዎች ሹክ ማለታቸውም
ይታወሳል፡፡
በቅርቡ ሰላማዊ ሰልፍ በደረገባቸው በጎንደርና በደሴ ከተሞች የሚገኙ ባለስልጣናትን
በግምገማ ከማጣደፍ ባለፈም የተወሰኑትን ከሀላፊነት አንስቷል፡፡
የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት በብዕር ስም የመንግስታቸውን አቋም
የሚያሰፍሩበት አይጋ ፎረም የተባለው ድረገፅም የገዢውን ፓርቲ ድንጋጤ
የሚያሳብቅ ፅሁፍ በሁለት ክፍል አስነብቧል፡፡ “ኢብሳ ነመራ” በሚል ስም የሰፈረው
የኢህአዴጋውያኑ ጽሁፍ አንድነት ፓርቲ በስኬት እያካሄደ ያለውን ህዝባዊ ንቅናቄ
ለማጣጣል ሞክሯል፡፡ አንድነት ፓርቲ እያደረገ ያለው ሰላማዊና ህጋዊ ህዝባዊ
ንቅናቄ “መንግስት የመለወጥ” አጀንዳ እንዳለው ገምቷል፡፡ ኢህአዴግ ሰው ሰብሰብ
ባለቁጥር የሚያባንነው ይህ ህዝብን የመፍራት አባዜው የት ያደርሰው ይሆን?
No comments:
Post a Comment