Thursday, July 25, 2013

ነገ ጁምዓ ሙስሊም ኢትዮያውን ልዩ ተቃውሞ ያሰማሉ


ነገ ጁምዓ ሙስሊም ኢትዮያውን ልዩ ተቃውሞ ያሰማሉ


600540_589521871099173_1142193440_nነገ ጁምዓ ሙስሊም ኢትዮያውን ልዩ ተቃውሞ ያሰማሉ
ድምጻችን ይሰማ ከሚለው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን የፌስ ቡክ ፔጅ የኮረጅኩት መረጃ እንደሚመለክተው፤ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የነገውን ጁምዓ በመላው ሀገሪቱ እና በመላው አለም ለሰማዩ አላህ እና ለምድራዊ አስተዳዳሪዎች በአንድነት “አቤት” ሊሉ ቀጠሮ ይዘዋል፡፡ የቦታዎቹን ዝርዝር ከድምፃችን ይሰማ ፌስ ቡክ ገፅ ቀድቼዋለሁ እንደወረደ ሲቀርብ የሚከተለውን ይመስላል፤
.አዲስ አበባ ከተማ በታላቁ ኑር መስጂድእንዲሁም፤
በክልል ከተሞች ማለትም፤ -ጅማ፣  አጋሮ፣  መቱ፣ ዶዶላ፣  በደሌ፣ አሳሳ፣  ኢሊባቡር.፣ ሻሸመኔ፣  ወልቂጤ፣ -ወራቤወዘተ ……… ሲሆኑ ከሃገር ውጪ ደግሞ ድምፃችን ይሰማ በጠራው በዕለተ ጁምዓ በአንድ አንደበት ተመሳሳይ የሆነና በድምፅየታጀበ በርካቶችን ያሚያሳትፍ የአደባባይ ተቃውሞ ላይ ለመሳተፍ ዝግጅታቸውን ያጠናቀቁት ሃገሮች የሚከተሉት ናቸው፡፡ 
በአሜሪካ፡-  በዋሺንግተን ዲሲ ዋይት ሃውስ ፊት ለፊት እና  በሲያትል ከተማ ፕራት ፓርክ መነሻውን አድርጎ ሲያትልፌደራል ህንጻ መድረሻውን ያደርጋል
2. 
ደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ኒውተን አደባባይ
3.
በካናዳ ቶሮንቶ
4.
በአውስራሊያ ሜልቦርን ፓርላሜን ሃውስ ፊት ለፊት 
የጋራ የኢፍጣር ፕሮግራም በማዘጋጀት የድምፃችን ይሰማ የአለም አቀፉ የተቃውሞ መርሃ ግብር አካል የሆኑት ሃገሮችየሚከተሉት ናቸው:- 
1. 
በጀርመን
በስዊድን፣
3.
በዩናይትድ ኪንግደም፣ ሎንዶን አሪሳላ መስጂድ N7 OLP
4.
በሆላንድ፣
5.
በኖርዌይ፣ ኦስሎ ኑር መስጂድ
3.
በስዊድን እንዲሁም
7
በቤልጂየም የጋራ የኢፍጣር ፕሮግራሞች በማዘጋጀት በአለም አቀፉ የተቃውሞ መርሃግብር ስር ተካተው ይካሄዳሉተብሏል፡፡
እኔም ድምፃችን ይሰማ ዎች ይሰሙ ዘንድ፤ ተሰምተውም መፍትሄ ይበጅላቸው ዘንድ ምኞቴን እገልፃለሁ!

No comments: