Thursday, November 5, 2015

የሰሞኑ የሕወሓት/ኢሕአዴግ ‘ከብስባሴዬ ልሻሻል ነው’ ዲስኩር “የድመት ፈገግታ አይጥን አሳስቃ ለመብላት ነው”


hailemariam Desalegn
ከአሰገደ ገብረሥላሴ
ሰሞኑን የህወሐት/ኢሕአዴግ ስራ አሥፈጻሚ ኮሚቴ የሞት ዋዜማ ኑዛዜ ሢያሠማን ሰንብቷል ::
ከኑዛዜዎቹ ጥቂቶቹ በሙስና ተበላሽተናል; እቺ ሀገራ ችን የምትመራው በደላዮች ነው:: የደላሎዮችና የመንግስት መዋቅሮች ከቤተመንግሥት እስከቀበሌ ተዘርግተዋል:: ህዝባችን ጠልቶናል አማርሮዋል; ባለሀብቶች ልናሠራቸው ኣልቻልንም; ከተሞች የብልሹው አስተዳደር ማእከላት ሆነዋል; ለመንግት የፕሮጀክት ማሥፈጸምያ የተመደበ ባጀት በደላሎችና የመንግሥት ባለስልጣኖች ተወረዋል… ወ ዘ ተ ብለው ሲነግሩን ሠንብተዋል ::
የሚገርመው ነገር ግን የህዝብ መሬትና ቤት መውረስና ማፍረሥ ማውደም በሚመለከት በአድዋ የአንድ ኢንቨስተር መሬትና ብር መዘረፉ ብቻ ሥህተት እንደፈጸሙ ሲያምኑ በትግራይ ክልል ከ200 ሽህ ቤቶች አፍርሰውና ዘርፈው በጎንደር በጎጃም በወሎ በኦሮሞ በአዲስ አበባና አካባቢዋ የፈረሱ ቤቶች የህዝብ መሬት ቀምተው የቸበቸቡ በተጨማሪ በባለሥልጣኖችና በኣጃቢዎቻቸው የተዘረፉ ምርጥ መሬት ዘርፈው ምንጩ ባልታወቀ ገንዘብ ኣድርገው ከኣቅማቸው በላይ ህንጻዎች ላሠሩ ፎጹም ደፍረው ሊያነሱ ኣልደፈሩም ::
በሌላ በኩል ስለ ዲሞክራሢና ሠብኣዊ መብቶች ጥሠትና አፈና ሥለ የፕሬሥ ነጻነት ሥለ የብዙሀን ፓርቲ ነጻነት ስለ ፖለቲካ መሪዎችና ኣባሎቻቸው የጋዜጠኞች በግፍ መታሠር መገረፍ መሠቃየት; በግፍ መገደል; ሥለ በነጻና በህጋዊ መንገድ የተደራጁ ፖለቲከኞች የሥራ እድልና ሁሉም ኣቀፍ መብቶች ማፈን በሚመለከት ለማንሣት ኣልቻሉም ::
ለሁም ህዝብ አግራሞት የፈጠረው ግን የህወሐት/ኢሕአዴግ ሀቀኛ ኣማራጭ ይዘው በፓርቲ ተደራጅተው ለፓርላማ ሊቀርቡ ዋዜማ ኢፍትሃዊ በሆነ መንገድ ሥለማፍረሳቸው በውድድር ለቀረቡም ድምጻቸው በመቀማት 100 % ለራሣቸው በማድረግ ፓርላማው እንቅልፋምና ሕይወት የሌለው የማድረጋቸውን ጉዳቸውን ለማጋለጥ ኣልደፈሩም ::
በእኔ እምነት እነዚህ ጨካኝ ፍጡራን የነገሩን ኣሥመሣይ ንግራቸው የድመት ፈገግታ ኣይጥን አሳስታ ለመብላት ዓይነት አጭበርባሪ አባባል አድርጌ ነው የምረዳው ::
ለመሆኑ እነዚህ መሪዎች ያሁሉ የጭንቀት ዲስኩራ ቸው በዚህቺ ሀገር ከላይ የተጠቀሱ ዝባዝኬ ችግሮች ለመጠራረግ ቆርጠው ተነሥተው ከሆነ በአንገታቸው ገመድ ኣስግብተው እንደመስቀል ይቆጠራል :: እዚህ ላይ ግን አያደርጉትም እንደዚህ አይነት የማታለያ መንገድ ከረጅም ጊዜ ጀምረው ይዘውት የመጡ ከህዝብ ሲነጠሉ ሲከተሉት የነበረ የማረጋጋት ሥልት ነው ::
“የደላላዎች ኔት ወርክ ከታች መዋቅር እስከ ቤተመንግስት ገብቷል” – ሃይለማርያም ደሣለኝ
ጠቅላይ ሚኒስቴር ሃይለማርያም “የሃገራችን መሪዎችና መዋቅራችን እያንዳንዳቸው የየራሣቸው የድለላና የምዝበራ ኔትወርክ አላቸው; የድለላና የሙስና ኔትወርክ እስከ ቤተመንግሥት ሰርገው ገብተዋል” ብለዋል ::
በተለይ በአቶ ደብረጽዮንና በኣባይ ጸሀየ ለተሠነዘረው አሣፋሪ አስተያየት ባልተለመደ ድፍረት በማሣየት; የበላይነትን በማሣየት የበላይነትን ማረጋገጣቸው ለብዙ ዜጎች አግራሞትን ፈጥሯል ::
በሌላ በኩል ሁሉም የህወሐት/ኢሕአዴግ ሥራ ኣሥፈጻሚ ኮሚቴ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር አባላትና ጋዜጦኞች በኢህአዴግ ባለሥልጣናትና ደላሎቻቸው ዘር ማንዘራቸው የፈጸሙት ወንጀልና ግፍ ሕዝብ እንዲያውቃቸው በማጋለጣቸው አሸባሪዎች; ነውጠኞች; ጠባቦች; ትምክህቶኞች; ዘረኞች እየተባሉ በግልጽና ህቡእ እስር ቤት; ወህኒ ቤት በስቃይ የተወረወሩበት; ቤተሰቦቻቸው የተሠቃዩበት በሙሉ በነዚህ የዘመናችን ግራዝያኒ መሰል ፉጡራን እንደወንጀል ሳይሆን እንደ ተራ ንግግር ሲደሠኩሩበት ታዩ::
እኔ የሚገርመኝ እነዚህ ፍጡራን የ24 ኣመት የግፍ ዘመን አገዛዛቸውና ምዝበራቸው ተቃዋሚ ፓርቲዎችና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ባለሀብቶች; ጦማርያን; ጋዜጦኞች እንደዚሁም ዲሞክራት አገሮች የዓለም ባንክና አይኤምኤፍ የሚለጉሱሏቸው ምክርና አሥተያየትን እያሥፈነጠሩ ቆይተው ኣሁን በ 11 ኛው ሰዓት ጉዳቸውን ማጋለጣቸው በእውነት ችግራቸው ጨክነው ለመፍታት ወይ ለመቅረፍ ነው? ወይስ ድራማ እየሠሩ ናቸው?
በእኔ እምነት ይሀ ጉዳይ ድራማ እየተሠራ ነው ያለው ነው የምለው :: ምክንያቱም እነዚህ ሰውች ከከፍተኛው የኢህአዴግ አመራር እስከ የጎጥ መዋቅራቸውና በስተጀርባቸው ያሉ ደላሎች ተጠቃሚ ሙሰኞች የበሰበሱና የላሸቁ በመሆናቸው ለዚህ ሁሉ የበሠበሠውን ጋንግሪን እንቆርጣለን ብለው ለማጥራት ከሞከሩ ህወሓት ኢህአዴግ ከነንግዱ ይጠራረጋል :: በመሆኑም አይጨኩኑም – ይህም የሚነግሩን ያሉ ሁሉ ድራማ መሆኑን ያረጋግጣል :: ምክንያቱም በኣሁኑ ጊዜ ሁሉም የህብረተ ሰብ ክፍል ሥለጠላቸወና ሥለናቃቸው የህዝቡን ሥሜት ለማብረድ የሚሠሩት ያሉት ድራማ ነው እንጅ አንዳች ለውጥ አያመጡም:: ከላይ እንደገለጽኩት እንደገለጥኩት የድመቷን ፈገግታ አይጧን አለሣልሶ ወይ አታሎ ለመብላት ይሠራ ያለው ድራማ ነው::
ሥለዚህ የኢትዮጱያ ህዝብ በሙሉ! እነዚህ ፍጡራን እያሉን ያለው ሁሉ ውሸት ነው:: ቅንጣትም ታህል በተግባር አትታይም :: የምናልባት ለጠላቸው ህዝብ ለማሥመሠል ጥቂት ወንድሞቻቸው ይገነድሱ ይሆናሉ::
የሀይለማርያም ደሣለኝ መድፈርም ፋይዳ የለውም:: ራሣቸው የሙስናና የደላሎቸ መዋቅር ኔት ወርክ ከቀበ ሌ እስከ ቤተመንግሥ ገብተዋል እያሉን ታድያ ማን መቺ? ማን ተመቺ ሊሆን ነው? ይሉቅንስ የኢትየጱያ ህዝብ ከሠላማዊ ትግልህ አትቦዝን : :ኢህአደግ እንደሆነ እንደዚህ ድራማ መሥራት ከረጅም ጊዜ ይዞት የመጣ የተካነ የሥራ ልምድ ነው ::
Source: Zehabesha

No comments: