ዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት የሰብዓዊ መብቶች ክንፍ እና የታም ላንቶስ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ኮሚሽን የዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች ደኅንነት ተሟጋቹ ቡድን ሲፒጄ የዘንድሮ ተሸላሚዎችን ምስክርነት አደመጠ። ከተሸላሚዎቹ አንዱ የዞን ዘጠኝ ብሎገሮች ቡድን አባሏ ሶሊያና ሽመልስ ተናግራለች።
ዋሽንግተን ዲሲ—በእንግሊዝኛ ስሙ ምኅፃር ሲፒጄ እየተባለ የሚጠራው ዋና መሥሪያ ቤቱ ኒው ዮርክ ከተማ የሚገኘው ዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች ደኅንነት ተሟጋች ቡድን የዘንድሮ ዓለምአቀፍ የፕሬስ ነፃነት ሽልማት ሎሬቶቹ ለዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት የሰብዓዊ መብቶች ክንፍ እና ለታም ላንቶስ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ኮሚሺን አባላት የእማኝነት ቃላቸውን እንዲሰጡ አድርጓል።
በዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ሬይበር ሕንፃ ተገኝተው ምሥክርነት የሰጡት የሲፒጄ ተሸላሚዎች የማሌዥያው ካርቱኒስት ዙልኪፍል አንዋር፣ የፓራጓይ ጋዜጠኛ ኮንዶሩዌዝና፣ የሦሪያው ቡድን ራቃ፣ የኢትዮጵያው የኢንተርኔት አምደኞች ቡድን - ዞን ዘጠኝ ናቸው።
ተናጋሪዎቹ በየሃገራቸው ያለውን የመናገር፣ የመፃፍ እና የመገናኛ ብዙኃን ነፃነት ይዞታ አስረድተዋል።
ኢትዮጵያን በሚመለከት ምሥክርነቷን ለመስጠት የተገኘችው የዞን ዘጠኝ አባሏ ወ/ት ሶልያና ሺመልስ ዞን ዘጠኝ እንዴት እንደተቋቋመ፣ ስለ ተከሰሱበት ፀረ-ሽብር ሕግ፣ ስለፍርዱ ሂደት በዝርዝር አስረድታለች።
አምስቱ ብሎገሮችና ሦስቱ ጋዜጠኞች በነፃ መሰናበታቸውን፣ አንዱ ጉዳዩ ገና በፍርድ ቤት እየታየ መሆኑን ሶልያና አስረድታለች።
ሶልያና ሺመልስ በሌሎችም የኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ከመስጠቷም በተጨማሪ ለወደፊት መሆን ይኖርበታል ብላ የምታስበውንና ከአሜሪካ መንግሥት ይጠበቃል ያለችውን ሃሣብም አቅርባለች።
ባልደረባችን ጽዮን ግርማ በቦታው ተገኝታ የሚከተለውን ዘግባለች።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
No comments:
Post a Comment