Thursday, November 19, 2015

አሁንም እስረኞች ነን - ከዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች የተሰጠ መግለጫ



ከሚያዝያ 17 2006 ጀምሮ በፓሊስ ቁጥጥር ስርውለን የነበርነው 3 ጋዜጠኞችና እና 6 የዞን9 ጦማርያን ከአንድአመት ከሁለት ወር እና ከአንድ አመት 5 ወር የእስር ቆይታ በኋላ ሁላችንም ከእስር አንደተፈታን ይታወሳል፡፡ በሃምሌ ወር መጀመሪያሶስት ጋዜጠኞች እና ሁለት ጦማርያን አቃቤ ህግ ክስ አቋርጦ፣ በማስከተል አራት ጦማርያን ደግሞ ነጻ ተብለው ከእስር መለቀቃችንየሚታወስ ሲሆን ጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ በዋስትና ላይ ሆኖ የቀረበበትንአመጽ የማነሳሳት ክስእንዲከላከል መባሉም ይታወቃል፡፡

ይሁን አንጂ የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ከተፈታን ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ነጻ አለመውጣታችንን የሚያሳዩ ተደጋጋሚ ተግዳሮቶች በመኖራቸውእና ሊቀየሩም ባለመቻላቸው ይህንን መግለጫ ለማውጣት ተገደናል፡፡

1.     የኢፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀጽ32 በሚደነግገው መሰረትማንኛውም ኢትዮጲያዊበፈለገው ጊዜ ከአገር መውጣት ነጻነትንበሚጻረር መልኩየመንቀሳቀስ መብታችንአሁንም ተገድቧል፡፡ ለምሳሌ ጦማሪ ዘላለም ክብረት ህዳር 7/2008 በፈረንሳይ አገር በሪፓርተርስ ሳንስ ፍሮንቲየርስ (ድንበርየለሽ ጋዜጠኞች ድርጅት) ለዞን 9 ጦማር የተበረከተውን 2015 የሲቲዝንጆርናሊዝም ሽልማት የዞን9 ጦማርን ወክሎ ለመገኘት ህዳር 6/2008 ቦሌ አየር ማረፊያ ቢገኝም ባልታወቀ ምክንያት ከአገር መውጣት ተከልክሎ ፓስፓርቱንምተቀምቷል፡፡ በዚህም የተነሳ የሚቀጥለው ሳምንት በሚከናወነው በአለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተከላካይ የሆነ የሲፒጄ የፕሬስ ነጻነት ሽልማት ላይ መገኘቱን እድልም በጣም አጥብቦታል ፡፡

2.    ጦማሪ አቤል ዋበላ (የኢትዮጵያአየር መንገድ ኢንጂነር) ጦማሪ ዘላለም ክብረት (የአምቦ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህር) ጦማሪት ማህሌት ፋንታሁን( የጤና ጥበቃሚኒስትር የዳታ ኦፌሰር) እና ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ (በፕላን ኢንተርናሽናል የኮምኒኬሽን እና ኖውሌጅ ማኔጅመንት ሰራተኛ) ወደስራገበታችን መመለስ አልቻልንም ፡፡ ከእኛ ቁጥጥር ውጪ በሆነው መንገድ ተገደን ከአንድ አመት በላይ እስር ቤት መቆየታችን የእኛ ጥፋትአንደሆነ ተቆጥሮ ከስራ ተባረናል ፡፡ሌሎቻችንም በግል እንሰራቸው የነበሩ ስራዎችንም መቀጠል አልቻልንም ፡፡

3.    ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከክሳችሁሙሉ ለሙሉ ነጻ ወጥታችኋል ብሎ የበየነልን ሶስት ጦማርያን ስንያዝማአከላዊምርመራ የተወሰደብን ፓስፓርታችን እና ሌሎች እቃዎቻችንእንዲመለሱልን ብንጠይቅምአቃቤ ህግ ይግባኝ ጠይቆባችኋልበሚል ሰበብ እስካሁን አልተመለሱልንም፡፡

4.    ቢቢሲ አንደዘገበው የኢፌዴሪጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ አሁንምታስረው የነበሩት ጋዜጠኞች እና ጦማርያን የእውነት ጋዜጠኞች አይደሉም ከሽብርጋር ግንኙነት አላቸውበማለታቸው እንዲሁም የተለያዬ የመንግስት ባለስልጣናት የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ላይ የሚሰጡት አስተያየት ፍርድቤቱ ያወጀልንን ነጻነታችንን - ህገመንግስታዊ በሆነ መንገድ እየናደው ነው ፡፡

በእነዚህእና በሌሎች ጫናዎች ምክንያት ራሳችንን ሳንሱር አንድናደርግ እና ሁሉም ጉዳያችን በእንጥልጥል ላይ ያለ የቁም እስረኞች የሆንንእንዲመስለን እየተደረገ ነው ፡፡ ስለሆነም
-      ህግ መንግስታዊ መብታችን የሆነውእና ምንም ህጋዊ ገደብ ያልተቀመጠበት በነጻነት የመንቀሳቀስ መብት መብታችን እንዲመለስልን
-      በኢግዚቢት ስም በማእከላዊምርምራ የሚገኙት እና ካለምንም ህጋዊ ምክንያት የተያዙት ፓስፓርት እና ሌሎች የግል እቃዎቻችን እንዲመለሱልን
-      መንግሰት የራሱን ፍርድ ቤትውሳኔ አክብሮ አሁንም ወንጀለኛ ስያሜ የሚሰጠንን ስም ማጥፋት እና የእጅ አዙር ጫና አንዲያቆምልን
-      የፓለቲካ ታማኝነትን ለማሳየትያለህግ አግባብ ወደስራ ገበታችን አንዳንመለስ ያደረጉን አካላት ውሳኔያቸውን መለስ ብለው እንዲያዩልን እንጠይቃለን፡፡

ሕገ መንግስቱ ይከበር

ዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች


No comments: