Thursday, July 25, 2013

እስከመቹ በዚህም 1ኛ ሆነን እንቀጥል?

እስከመቹ በዚህም 1ኛ ሆነን እንቀጥል?
በአገራችን ስለሚከሰት የመኪና አደጋ ሳንሰማ የምንውልበት ቀን እየናፈቀን ነው። ምንድነው ጉዱ?እስከመቼስ ነው በትራፊክ አደጋ ከዓለም 1ኛ እያልን እየፎከርን የምንቀጥለው? “ዕድገቱ”በዚሁ ከቀጠለ ውሎ መግባት ብርቅ የሚሆንበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም።የምሬን ነው የምላችሁ፦”መንገድ ተሠርቷል” የተባለው ለመንከባለያ እስኪመስል ድረስ ከሌሎች አገሮች ጋር ሲነፃፀር ብዙም ተሽከርካሪዎች በሌሉባት አገራችን ውስጥ - ይህን ያህል የአደጋ “ዕድገት” ምንድነው የሚባለው?
እናም… መንግስትና የሚመለከታችሁ የዘርፉ ሃላፊዎች ሆይ! “አሽከርክር ረጋ ብለህ” የሚል ሙዚቃን በማሳተም ብቻ የትራፊክ አደጋን መከላከል እንደማይቻል ደጋግማችሁ በማጤን በየቀኑ እየተቀጠፉ ያሉ ህይወቶችንና እየወደሙ ያሉ ንብረቶችን ለመታደግ ጠንካራና የተቀናጀ አሠራር ነድፋችሁ ተግባራዊ ታደርጉ ዘንድ ትጠየቃላችሁ! የማትችሉ ከሆነ፣ ከሰው ህይወት የሚበልጥ ነገር የለምና ስልጣናችሁን ልቀቁ!
እንኳን የአንድ ሰው ህይወት፣ የአንድ ሰው አካል በሚሊዮን ብሮች የማይተመን ታልቅ ሀብትና ፀጋ ነው። ክብርና ጥበቃ ለሰው ልጆች ህይወት!

No comments: