Monday, July 22, 2013

ፖለቲካዊ ማናለብኝነት እንደ ሥርዓት



ፖለቲካዊ ማናለኝነት እንደ ሥርዓት
ፍጹም ሥልጣን ፍጹም ያባልጋልየሚለውን አነጋገር ኢትዮጵያውያን በተግባር እናውቀዋለን። ዴሞክርሲን የተመኘነውም የመንግሥት ሥልጣን የሚይዙ ቡድኖች እና ደጋፊዎቻቸው መባለጋቸው ባይቀርም ፍጹም እንዳይባልጉብን ያደርግልናል ብለን እንደሆነ የታወቀ ነው። ዴሞክራሲ ይህን ማረጋገጥ ከሚችልበት ደረጃ ከመድረሱ በፊት ከዚያ ብልግና ሊታደገን እንደማይችል በዚህ ምርጫ ታዝበናል።
ኢሕአዴግና የተወሰኑ አባሎቱ ከምርጫው በፊትም ሆነ በኋላ የሚያሳዩት ማናለብኝነት ለደጋፊዎቻቸው ጭምር አሳፋሪና አስጊ ነው።የቀው ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ መለስ ከምርጫው በፊት በፓርላማ ቀርበውከምርጫው በኋላ እናስራችኋለንእያሉ የሚያስፈራሩት፤ ደግሞምህረታች ገደብ ስለሌለው አናስራችሁም አትፍሩእያሉ የሚናገሩት ተተኪዎቻቸው የፍጹም ሥልጣን ባለቤትነት በእጃቸው ስለገባ ብቻ ነው። ስለዚህም ፍጹም ለመባለግ የሚያስችለው ነገር ሁሉ ለእርሳቸውና ለፓርቲያቸው ተመቻችቷል። አንድ መጥፎ ምልክትሁሉም ነገር የኢሕአዴግ እና ለኢሕአዴግ ብቻየሚለው ነው።
የምርጫው ተሞክሮ ለኢሕአዴግ የሚያስተላልፈው ተሞክሮ የተለያየ ነው። ለአቶ ለማ ለፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ ምናልባት ተመሳሳይ በስም ዴሞክራሲያዊ የሚመስሉ በተግባር ግን ያለምንም ጥርጥር የእነርሱን አሸናፊነት የሚያረጋግጡ ተመሳሳይ ምርጫ ድራማዎችእየሠሩ ለረጅም ጊዜ ሥልጣን ላይ መቆየት እንደሚቻል ይሰማቸው ይሆናል። በእነዚህ ድራማዎች ተቃዋሚ ነኝ ለሚለውየማይጠፋበት ግን የማያሻንፍበት፤ የሚኖርበት ነገር ግን የማይጠናከርበትንመድረክ እየፈጠሩ የድራማው ዘላቂ ተዋናይ ማድረግ እንደሚቻል የባለፈ ተሞክሮ አስተምሯቸው ይሆናል። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ሶማልያ እስካልተረጋጋች ድረስ ኢትዮጵያን ማጣት ስለማይፈልግ ቅሬታው በድራማው አተዋወን ላይ እንጂ በጭብጡ ላይ አለመሆኑን እየቆየ የሚረሳውየተቃውሞ፣ የአሳስቦናል…” መልእክት አራጋጋጭ ነው።
ለኢሕአዴግ የበታች ሹማምንት በፓርቲያቸ የተላለፈው መልእክት ደግሞ፣ከፓርቲው ጋራ እስከቀጠላችሁ በየመስኩ የምታገኙት የግል ጥቅም ሳያቋርጥ ይቀጥላል፤ ሌላ ኀይል ከመጣ ግን የጥቅሙ መቆም ብቻ ሳይሆን ሕልውናችሁም ጥያቄ ውስጥ ይገባልየሚል ነው። በዚህ ላይ ደግሞ ብሔረሰብን መሠረት ያደረገው የጥርጣሬ እናመጣብህ ሊበላህ ነውደረስኩልህየሚለው ውስጥ ውስጡን የሚግም እሳት ይጨመርበታል። ይህም የፖለቲካ ልሒቁ በጥቅምና በፍርሃቱ እንዲታሰር ያደርገዋል። እንግዲህ እነዚህ ሹመኞች፣ አቶ በረከትተከለውእንገናኛለንእያሉ ቢዝቱ ምን ይፈረድባቸዋል? ፍርሃታቸውን ያስቀሩ፣ በዚያውም የኢኮኖሚያዊ ጥቅሞቻቸውን ዘላቂነት ያረጋገጡ እየመሰላቸው መብት ቢጥሱ፣ ተቃዋሚዎችን ቢያፍኑ፣ የታዘዙትን ሁሉ ያለማመንታት ቢፈጽሙ ቀጣዩን ዞዋቸውን  የበለጠ ድንቅ አደርጉት ማለት አይደለም?
ሌላው መልእክት በኢሕአዴግ ዙሪያ በመሰባሰብ ላይ የሚገኘው የኢኮኖሚ ፍላጎት ያለው ኀይል ነው። ይህ ኀይል በአድሎ ላይ በተመሠረተ አሠራር የሚያገኘው ጥቅም የሚጠበቅለት ኢሕአዴግ እስካለ ድረስ ብቻ እንደሆነ ወደሚያምንበት ደረጃ ለመድረስ ብዙ ጊዜ አይፈጅበትም። ሚሊዮኖችን እያወጣ ለፓርቲው የሚሰጠውም ይህን ስለሚረዳ ነው። በተቃራኒው ለተቃዋሚዎች በግልጽም ይሁን በስውር ድጋፍ ማድረግ ቅጣት ሊያስከትለበት እንደሚችል ያምናል። የዚህ ድምር ውጤትም የአንድ ፓርቲ ፓለቲካዊ ማንአሎንነት እየሆነ ነው። ማንአለኝነቱ የሚያስከትለውብልግናምን ሊሆን እንደሚችል ያየነው ነው።
በአጠቃልይ ሲታይ የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሽግግር ከማይወጣበት ቅርቃር ውስጥ ገብቷል። አሁን ፈተናው ይህ ሽግግርከተሞከረ ይቻላልየሚል እምነት አሳድሮ የነበረውን እና ኢሕአዴግ በተከታታይ በሚወስዳቸው እርምጃዎች ወደ ተስፋ መቁረጥ እየተገፋ ያለውን በርካታ ዜጋ ማሳመን ጭምር ሆኗል። በዚህም ምክንያት አገር ውስጥ ያሉት ተቃዋሚዎች ፈተናም በብዙ እጥፍ ይጨምራል። የዴሞክራሲያዊ ሽግግር ተስፋ እጅግ እየራቀ ነው። ከእይታችን ፈጽሞ ወደ መሰወር እየቀረበም ነው። ተስፋው ግን አይጠፋም፤ ሊጠፋ አይችልምና።ተሰለጠነና…” አሉ!
ከአንድናት ኢትዮጵያ ብሎግ

ኢትዮጵያ ክብር ለዘላለም ትኑር!

No comments: