Tuesday, July 23, 2013

ቅርንጫፍ እንጂ ግንድ አይገነጠልም!!


       ቅርንጫፍ እንጂ ግንድ አይገነጠልም!!

ዛሬ ዛሬ ተቀዋሚው ኃይል የወያኔን ዘረኛ አገዛዝ ከመታግል ይልቅ እርስ በርስ 

የሚያደርገው ትግል ጎልቶ ይታያል። አንዳንድ በስም እንጂ በተግባር ከወያኔ 

የማይሻሉ ተቃዋሚዎች አውቀውም ይሁን ሳያውቁት የኢትዮጵያን ሕዝብ በዘርና 

በሐይማኖት መከፋፈሉን ሥራዬ ብለው ተያይዘውታል። በተለይ ሰፊውን የኦሮሞ 

ሕዝብ የሚወክሉ ተቃዋሚ ኃይሎች 40 ዓመት ሙሉ ሞክረው ያልተሳካላቸውን 

የመገንጠል አጀንዳ ማራገብ መጀመራቸው የፖለቲካ ትግሉን አቅጣጫ 

ቀይሮታል።ይህ ደግሞ ጠቀሜታው ለወያኔ ብቻ በመሆኑ፤የኢትዮጵያን ሕዝብ 

የስቃይና የመከራ ዘመን ያራዝማል።ሰፊውን የኦሮሞ ሕዝብ የሚወክሉ የፖለቲካ 

ተቃዋሚ ኃይሎች ከ40 ዓመት የትግል ተሞክሯቸው ቅርንጫፍ እንጂ ግንድ 

የማይገነጠል መሆኑን ያረጋገጡ ይመስለኛል። ስለዚህ ሁላችንም እርስ በርስ 

የምናደርገውን ትግል ትተን የጋራ ጠላታችን የሆነውን የወያኔ ዘረኛ አገዛዝ በማስወገድ 

የኢትዮጵያን ሕዝብ የሥልጣን ምንጭና ባለቤት ማድረግ ይጠበቅብናል።

No comments: